TG Telegram Group & Channel
ከራድዮን | United States America (US)
Create: Update:

ደብረዘይት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የተወደደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ደብረዘይት በተናገረበት ድርሳን እንዲህ አለ፦

"የክርስቶስ ተቃዋሚ እንዴት እንደሚመጣ ከነገራቸው በኋላ እርሱ (ጌታ) ራሱም እንዴት እንደሚመጣ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡- “መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይኾናልና፡፡”

መብረቅ አለ! ስለ መብረቅ ብልጭታ ማንም እንዲመሰክር አይፈለግም፡፡ በእልፍኝ ለተቀመጡም፣ በቤት ውስጥ ላሉም፣ በአጠቃላይ በዓለም ኹሉ ላሉት በቅጽበት ይታያልና፡፡ ክርስቶስ ክብሩን እየገለጠ እንዲህ ድንገት ይመጣል፡፡ ሌላ ምልክትም አለው፡፡ በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች እንዲሰበሰቡ ክርስቶስ ሲመጣም አእላፍ መላእክት፣ ቅዱሳን ሰማዕታት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ነቢያት፣ ጻድቃን ኹሉም ይሰበሰባሉ።

ከዚያ በኋላ በጣም አስፈሪ ድንቅ ይፈጸማል፡፡ በክርስቶስ ተቃዋሚ፣ በሐሰተኞች ነቢያት የሚደረገው የማታለል ሥራ ካለቀ በኋላ፣ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን ከለወጡ በኋላ ወዲያው ተፈጥሮ መልኳን ትለውጣለች፤ ፀሐይ ይጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፡፡ በዚያ ቅጽበት በጨለመው ዓለም ፋንታ የክርስቶስ ብርሃነ መለኮት ይተካል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት የለም፡፡ ከዋክብት በተፈጠሩ ጊዜ መላእክት በታላቅ ድምጽ እግዚአብሔርን እንዳመሰገኑ (ኢዮብ.38፡7) የዚያን ጊዜም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በጠፈር ሠልጥነው የነበሩ ፀሐይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ብርሃኗን ስትከለክል፣ ከዋክብት ሲወድቁ አይተው የሰማያት ኃይላት (መላእክት) ይናወጣሉ፤ ይደነቃሉ።

በዚያን ጊዜም የወልደ እጓለ እመ ሕያው ክርስቶስ ምልክቱ፣ አሠረ ቅንዋቱ በሰማይ ይታያል፡፡ በሌላ አገላለጽ መስቀሉ ከፀሐይ ብርሃን ይልቅ ደምቆ ይታያል፡፡ ዳግመኛ ላትታይ ፀሐይ ጨልማለችና ብርሃነ መስቀሉ ይንቦገቦጋል፡፡ ከእናንተ መካከል “ስለ ምን መስቀሉ በዚያ ሰዓት ይታያል?” ቢል ጌታ የሰቀሉትን አይሁድ ይወቅስ ዘንድ ነው ብለን እንመልስለታለን፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ በፍርድ ወንበሩ ይቀመጣል፡፡ የቆሰለውን ቁስል ብቻ ሳይኾን የሞት ተግሣጽንም እያሳየ መጥቶ ይቀመጣል፡፡ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች የሚያምኑበት ሰዓት አይደለምና በወልደ እግዚአብሔር ባለማመናቸው ኹሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፡፡ ሊያከብሩትና ሊታመኑት ሲገባ ሲሳለቁበት ኑረዋልና ላይጠቅማቸው ዋይ ዋይ ብለው ያዝናሉ፡፡ የምድር ወገኖች የራሳቸውን ኃጢአት እያነበቡ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፡፡ በመዋእለ ሥጋዌው ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ላይ ተጭኖ ሲገባ በጌታ ስም የሚመጣ ብሩክ ነው እንዳላሉ አሁን ግን ዋይ ዋይ ይላሉ፡፡

የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ የአዋጅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፡፡ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ሙታን ይሰበስባሉ።

"ወዮ! በዚያች አስፈሪ ቀን ለእኔ ወዮታ አለብኝ! የመለከቱን ድምጽ ስሰማ መደሰት ሲገባኝ ስቃይ ይሰማኛልና ወዮታ አለብኝ፡፡ ስለዚያች ቀን ሳስብ ውስጤ በረዓድ ይመላል፤ አምርሬ አለቅሳለሁ፤ በውስጤም እቃትታለሁ፡፡ 'ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን' ከሚላቸው ከጻድቃን ጋር የሚያስደምር መልካም ሥራ የለኝምና፤ እንደ አምስቱ ሰፎች ቆነጃጅት፣ መክሊቱን እንደቀበረ ታካች ባርያም ኾኛለሁና አለቅሳለሁ፤ ፊቴ በእንባ ይታጠባል፡፡ የማጣውን ክብር፣ የሚቀርብኝን የድል አክሊል፣ ለጊዜው ሳይኾን ለዘለዓለም እንደማጣው ሳስብ አነባለሁ፡፡

ልጆቼ! ይህን የሚሰማን እኔ ብቻ እኾን ወይስ እናንተም ይሰማችኋል? ከማን ወገን ናችሁ? ደስ ከሚላቸው ወይስ ላይጠቅማቸው ዋይ ዋይ ከሚሉቱ ወገን?"

(በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
@gitim_menfesawi

>>Click here to continue<<

ከራድዮን

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)