TG Telegram Group & Channel
ከራድዮን | United States America (US)
Create: Update:

የጦርነት ድልን ቤተክርስቲያን ለምን ታከብራለች?
[#አድዋ]

በሐዘን ማቅ ውስጥ ገብታ የምትዳክረው ኢትዮጵያ በርከት ባሉ የትርክትና የፍላጎት ግጭቶች የተሞላውን የአድዋ ድል በዓልን እያከበረች ነው። በአሉ ለኢትዮጵያ ወሳኝ ታሪካዊና ማህበረ ፖለቲካዊ በአል ቢሆንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም በራሷ ሥርዓትና ቀኖና ታቦት አውጥታ ንግስ አንግሳ ታከብረዋለች።

ይህን ማክበሯ መፍቀሬ ሚኒሊክ፣ የነፍጠኞች ዋሻ ፣ ሰሜናዊት እያስባለ በብዙዎች ቢያስተቻትም ዝክረ አድዋን ሳታቋርጥ ቀጥላለች።ለመሆኑ በሁለት ሐገራት መካከል የተደረገን የጦርነት ድል መንፈሳዊት ቤተክርስቲያን ማክበር አለባት?

በቅድስት ቤተክርስቲያን በዓላት የሚከበሩት ከዚህ በታች ባሉ ምክንያቶች ነው።
1. በነገረ ድህነት ወሳኝ ምዕራፍ የተጫወቱ ቀናት /በአብዛኛው የሐዲስ ኪዳን በዓላት እለተ እሁድን ጨምሮ
2. ጠብቆተ እግዚአብሔር የታየባቸው ቀናት /አብዛኛዎቹ ብሉይ ኪዳን ጠቀስ በዓላት ቀዳሚት ሰንበትን ጨምሮ
3. የእግዚአብሔር ቅዱሳን የተወለዱበትና /ወይም ያረፉበት ቀናት
4. እግዘብሔር በቅዱሳኑ ድንቅ ያደረገባቸው ቀናት /ስባረ አፅሙ ለቅዱስ ገዮርጊስ ፣ የህዳር ፅዮን የመላእክት በዓላት .....
5. በአለማቀፋዊቷም ሆነ በሀገራዊቷ ቤተክርስቲያን ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ያረፈባቸው ቀናት /ጰራቅሊጦስ፣ የኒቂያ ቆስጠንጢንያና ኤፌሶን የአለም አቀፍ ጉባኤያት፣ የአርመን ቤተክርስቲያን ጭፍጨፋ፣ የኮብቲክ ቀን፣ በዓለ ሲመቱ ለፓትርያርክ....

እነዚህ በዓላት እንደየክብራቸውና ድርሻቸው መጠን በመላው አለም ወይም በአንድ ሐገር አልያም በአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ስርዓቶች ይከበራሉ።

የአድዋ ድል በዓልን ቤተክርስቲያን ስታከብርም ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ አብዛኛውን ስለሚያሟላ ነው።

የአድዋ በዓል እንደ ጠብቆተ እግዚአብሔር ማሳያ።

እግዚአብሔር የኢትዮጵያም የጣሊያንም አምላክ ነው። ማንንም ለይቶ አይደግፍም ነገር ግን በድንግል ማርያም ፀሎት እንደምናገኘው ብርቱዎችን ያዋርዳል የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ ያደርጋል። በመሆኑም ብርቱ ነኝ ብሎ ምንም ጠብን ባልሻተች ሀገር ላይ የተከፈተን ጦርነት በምንም መልኩ ሚደግፍ አምላክ አይደለም። በመሆኑም ሳይበደል ለመበደል ዘመናዊ ጦርን ታጥቆ የመጣን ሰራዊት ለደካሞችና በአብዛኛው የቤት ቁሳቁስና የግብርና መሳሪያዎችን እንዲሁም አነስተኛ ጦር በታጠቁ ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች እጅ ጥሎታልና ይህ ዕለት የእግዚአብሔር ቀን ነው።

የአድዋ ድል እንደ ቅዱሳን ተራዳኢነት ማሳያ

የአድዋ በአል ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት ጋር የበዛ ቁርኝት አለው። በተለይም እነዚህ ቅዱሳን ለተገፉ ደራሽ ከመሆናቸው ባሻገር በኢትዮጵያ የአሥራትነት ና ገበዝነት ሚና እነደሚራዷቸው ያመኑ ኦርቶዶክሳውያን ኢትዮጵያውያን ታቦታቱን አሰልፈው ምህላ እያስደረሱ በተራሮች መሐል ተዋድቀዋል። ሞተዋል ቆስለዋል ደምተዋል። ከጎናቸው የቅድስት ድንግል ማርያም ረዳትነት የቅዱስ ጊዮርጊስ ጥበቃ አልራቀም ነበር። ፈረንጆቹ እኛን የሚመስል በእነሱ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ይወጋን ነበር እስኪሉ ድረስ ጥበቃው በጠላት ወገን ጭምር የተገለጠ ነበር።

አድዋ እንደ ወሳኝ የቤተክርስቲያን የታሪክ ክፍል

የአድዋ ጦርነት ኬልቄዶናዊ ሀሳብ ተሸርቦባት የነበረች ቤተክርስቲያንን የታደገ ድል ነው። ለበርካታ ዘመናት ከምዕራቡ የአውሮፓ አለም የመጡ ጦሮች አላማቸው ኢትዮጵያን መቀራመት ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ካቶሊክ ማድረግ ቢሆንም የሮም መንበር በነበረባት የጣሊያን ሁለት ወረራዎች ግን በግልጽ አንዲት ቤተክርስቲያን በሌላ ቤተክርስቲያን ላይ የጦር ወረራ ያወጀችበትና መሳሪያ ባርካ ሁሩ ወኢትመሀሩ ያለችበት ወረራ ግን እጅጉን ያፈጠጠ ነበር። ትናንት በሱሲኒዮስ በርካቶችን ለሰማያዊ ርስት የተገቡ ያደረገችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሳሪያ ከመባረክ አልፋ በጦርነቱ ውስጥ አገልጋዮቿን ትጥቅ አስለብሳ እንዲሁም ለቤተክርስቲያን አባቶች መደለያ በመስጠት በሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ያደረገችውን የታጣቂዎች የወንጌል ተልዕኮ ለማስፈፀም አቅዳ የነበረ ቢሆንም አስቀድሞ በአድዋ ድል ኋላም በአምስት አመቱ ጦርነት እንዲጨነግፍ ሆኗል።

እነዚህን ምክንያቶች ማዳመጥ የማይችሉ ምንም እንኳን ስም ቢያወጡላትም ቤተክርስቲያን ግን በዓሉን ማክበሯን የምታስታጉል አይደለችም ያዳናትን ታውቃለችና።

@gitim_menfesawi

>>Click here to continue<<

ከራድዮን

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)