የአብስራ ሳሙኤል
⁓⁓⁓
ልውደድስ ቢሉ ⁓ እንዴት ተደርጎ ይወደዳል
ደግሞ ልሽሽም ቢሉ ⁓ ከራስ ወዴት ይኬዳል
ብቻ ህያው ነፍሴ ⁓ በሁለት ባላ ተወጥራ
ለፍታ ደክማ ........ጥራ
♡⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯♡
ወዳንቺ ⁓ ትንጠራራለች
በለሆሳስ ⁓ ታወራሻለች
‧₊˚✧
አየሽ አበቦቹን ⁓ በሚወዷቸው ተከበው
ጸድቀው ⁓ ፈክተው ⁓ አብበው
❀ ❀ ❀
የመኖርን ጣዕም ⁓ ሲቀስሙ
በቢራቢሮ ⁓ ሲሳሙ
—⋅☾⋅—
በእኔ ቀጋ ገላ ⁓ ትል ያዣል
እንኳን ለሚወዱት ⁓ ለራስስ ምኑ ያስጎመዣል
⁂
እናም ⁓ ቢሳካልሽ ⁓ ቢሆንልሽ
ጭቃ ⁓ ጠፍጥፈሽ ⁓ በሀብና በአምሳልሽ
◌ ◌ ◌
ብትፈጢርኝ ⁓ መች ይከፋኛል
የአንቺ መሆን ⁓ ያስመኘኛል
⋯♰⋯
ቢሆንም ⁓ ሂጅ ⁓ ግድየለም
አንቺን ⁓ አትነፍግም ⁓ አለም
—⋆—
ህይወት ⁓ ቢረግፍም ⁓ በየመስኩ
ላይችል ⁓ አይሰጥ ⁓ ያለ ልኩ
⸻⸻⸻
እስጥሽ ምንም ⁓ የለኝም
እቸርሽ ⁓ አልሞላልኝም
ከኔ ዘንድ ⁓ አትጠውልጊ
ከፈካው ⁓ አበባ ⁓ ተጠጊ
⁓⁓⁓
@getem
@getem
@getem
>>Click here to continue<<