TG Telegram Group & Channel
ግጥም ብቻ 📘 | United States America (US)
Create: Update:

ሀ...ለ...ሐ...መ
ነገር አከተመ

ጥበብ በሁለቱ
በግጥም ስዕሉ
        ስታወናብደኝ
ህይወት ሚሉት ቋንቋ
ካንቺ ስር አዋለኝ።

መልክሽን በስዕል
መልክሽን በግጥም
       አተራመስኩልሽ
ይኸው አበድኩልሽ።

ጥበብና ህይወት...
ካንቺ ጋር አጋብተው ላያኖሩኝ ነገር
ለምን ይሰጣሉ
"ስሜት" ብለው ማፍቀር

አቤት አኳኋንሽ
አቤት አሳሳቅሽ
አቤት አረማመድ
ምንድነው መላመድ?
ለጥበበኛ ሰው መላመድ ትርፍ ነው
አይቶ ማፍቀር ብቻ ጥበብ እያረገው።

አይ ጥበብ አንዳንዴ
ደስ አለሽ ማበዴ!

የማልጨብጣትን ከምናብ አለም ሰው
        በፍቅር ሰቀልሽኝ
       ይኸው አሳበድሽኝ።

ሀ...ለ...ሐ...መ
በቃ ተፈፀመ።

ታሪክ ልስራ ብዬ...ታሪኬን ጨረስኩት
          ኑሮዬን አበድኩት

አይ ጥበብ አንዳንዴ
ደስ አለሽ ማበዴ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem

ሀ...ለ...ሐ...መ
ነገር አከተመ

ጥበብ በሁለቱ
በግጥም ስዕሉ
        ስታወናብደኝ
ህይወት ሚሉት ቋንቋ
ካንቺ ስር አዋለኝ።

መልክሽን በስዕል
መልክሽን በግጥም
       አተራመስኩልሽ
ይኸው አበድኩልሽ።

ጥበብና ህይወት...
ካንቺ ጋር አጋብተው ላያኖሩኝ ነገር
ለምን ይሰጣሉ
"ስሜት" ብለው ማፍቀር

አቤት አኳኋንሽ
አቤት አሳሳቅሽ
አቤት አረማመድ
ምንድነው መላመድ?
ለጥበበኛ ሰው መላመድ ትርፍ ነው
አይቶ ማፍቀር ብቻ ጥበብ እያረገው።

አይ ጥበብ አንዳንዴ
ደስ አለሽ ማበዴ!

የማልጨብጣትን ከምናብ አለም ሰው
        በፍቅር ሰቀልሽኝ
       ይኸው አሳበድሽኝ።

ሀ...ለ...ሐ...መ
በቃ ተፈፀመ።

ታሪክ ልስራ ብዬ...ታሪኬን ጨረስኩት
          ኑሮዬን አበድኩት

አይ ጥበብ አንዳንዴ
ደስ አለሽ ማበዴ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
50🔥9🤩1


>>Click here to continue<<

ግጥም ብቻ 📘




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)