TG Telegram Group & Channel
ግጥም ብቻ 📘 | United States America (US)
Create: Update:

ሲያምርብሽ ቀሚስ ጥልፉ
ሲያምርብሽ ነጭ በነጩ
ህፃናቶች ከእግርሽ ስር
ተኮላትፈው የሚንጫጩ
እረበሹሽ ከጸሎትሽ
የዳዊቱን ቦታ አጣሽ?
እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ
ቤተመቅደስ ምን አመጣሽ?
ከመልክሽ ላይ ይታየኛል
የአብ እጁ ልዕልና
በሁዳዴ ቤቱ መጣሽ
ጌታን ልትይ ሆሳዕና?

ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ንጉስ አየን ከድንግል ሴት
ፀሀይ ወጣ ከአርያም

ከቅዳሴው ዜማ ሰማን
መንበር መሃል እጣን ጨሰ
ህዝበ እስራኤል
ጨርቁን ሁሉ
እመሬት ላይ አለበሰ

የምስጋናው ዜማ ጦፈ
መንፈስ ቅዱስ ህዝቡን መላ
በወንጌሉ ክብር አገኘች
የያዘችው ውርንጭላ

ህዝቡ ሞልቷል ከመቅደሱ
ወንዱም ሴቱም ለየብቻ
በነጠላ ተሸፍነሽ
ምትታዪኝ አንቺ ብቻ
ከአጠገብሽ ጎልማሳ ሴት
ሲደገፉሽ ማትከፊ
የደከማት አራስ እናት
ልጇን ይዘሽ የምታቅፊ
በነጠላ የሚያምር ገጽ
ለመንካትም የሚያሳሳ
ጸጉርሽን ሸፍነሻል
ዋናው ነገር ፊትሽሳ?

ላለማየት እጥራለው
ነጣላሽን ስታጣፊ
ወዴት ላርገው ይዤ ቆምኩኝ
የዘንባባ ዝንጣፊ

ምን ላድርገው ዘንባባውን ?
መስቀል ልስራ ለግንባርሽ
ከብልጭልጭ ከወርቅ አልማዝ
መስቀሉ ነው ሚያሳምርሽ

በቢጫዋ ዘምባባስ ግን
አይኔ አይቶ ከመረጣት
ቀለበትን ልስራ ይሆን
ለእጆችሽ ሰልካካ ጣት?

በአራቱም መአዘናት
ተነበበ ወንጌል ለአለም
ምህላችን ይቀጥላል
እስኪመጣ ለዘላለም
አንድ ሳምንት የፆም ስግደት
ህማማቱ ሊጠብቀን
ከበሮውን ሰማይ ሰቅለን
አመስግነን ለአንድ ቀን

ከመድረኩ ነጭ ለብሰው
ከበሮውን እየመቱ
ክብ ሰርተው ሲዘምሩ
እንደያኔው ህፃናቱ
ምን ተሰማሽ በድምቀቱ
አይኔ ካንቺ ተመልክቷል
ጠብታ ውሃ የምታክል
ዘለላ እንባ ከአይንሽ ወቷል
ለምን አዘንሽ በደስታ ቀን
ይታወቃል
የልቦናሽ   ንጽህና
የእግሮችሽን ጣቶች ላንፃ
ፀሎተ ሀሙስ ይድረስና?

አትፈልጊም አውቃለሁኝ
እንኳን ማጠብ እንዲያዩሽም
የኤደን ውስጥ በለስ እንጂ
የዱር ኮሽም አይደለሽም
ታዲያ ያለሙን ጣጣ ረስቶ
ልቤ ሰከን ከሚልበት
እንዲታወክ ቤተ መቅደስ
ባትመጪ ምን አለበት?

ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ንጉስ አየን ከድንግል ሴት
ፀሀይ ወጣ ከአርያም

የገላውን ስጋ ቆርሰው
በቀናት ውስጥ የሚገሉት
ጨርቃቸውን አገላድመው
በእልልታ ተቀበሉት
የኛ ህዝብም ደምቋል ዛሬ
መስቀል ሰርቷል ከመረጠው
ጎልጎታ ላይ እስኪሰቀል
ወዳጅ ስሞ እስኪሸጠው
የኔ ግና ተበጥሷል
የአይኔ ላይ መቀነቻ
ከዚህ ሁሉ ተነጥለሽ
ምትታዪኝ አንቺ ብቻ
ምናለበት ባገለግል
ቤተመቅደስ ሌላ አላጣሽ
እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ
እኔ ደብር ምን አመጣሽ?

By @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii

ሲያምርብሽ ቀሚስ ጥልፉ
ሲያምርብሽ ነጭ በነጩ
ህፃናቶች ከእግርሽ ስር
ተኮላትፈው የሚንጫጩ
እረበሹሽ ከጸሎትሽ
የዳዊቱን ቦታ አጣሽ?
እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ
ቤተመቅደስ ምን አመጣሽ?
ከመልክሽ ላይ ይታየኛል
የአብ እጁ ልዕልና
በሁዳዴ ቤቱ መጣሽ
ጌታን ልትይ ሆሳዕና?

ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ንጉስ አየን ከድንግል ሴት
ፀሀይ ወጣ ከአርያም

ከቅዳሴው ዜማ ሰማን
መንበር መሃል እጣን ጨሰ
ህዝበ እስራኤል
ጨርቁን ሁሉ
እመሬት ላይ አለበሰ

የምስጋናው ዜማ ጦፈ
መንፈስ ቅዱስ ህዝቡን መላ
በወንጌሉ ክብር አገኘች
የያዘችው ውርንጭላ

ህዝቡ ሞልቷል ከመቅደሱ
ወንዱም ሴቱም ለየብቻ
በነጠላ ተሸፍነሽ
ምትታዪኝ አንቺ ብቻ
ከአጠገብሽ ጎልማሳ ሴት
ሲደገፉሽ ማትከፊ
የደከማት አራስ እናት
ልጇን ይዘሽ የምታቅፊ
በነጠላ የሚያምር ገጽ
ለመንካትም የሚያሳሳ
ጸጉርሽን ሸፍነሻል
ዋናው ነገር ፊትሽሳ?

ላለማየት እጥራለው
ነጣላሽን ስታጣፊ
ወዴት ላርገው ይዤ ቆምኩኝ
የዘንባባ ዝንጣፊ

ምን ላድርገው ዘንባባውን ?
መስቀል ልስራ ለግንባርሽ
ከብልጭልጭ ከወርቅ አልማዝ
መስቀሉ ነው ሚያሳምርሽ

በቢጫዋ ዘምባባስ ግን
አይኔ አይቶ ከመረጣት
ቀለበትን ልስራ ይሆን
ለእጆችሽ ሰልካካ ጣት?

በአራቱም መአዘናት
ተነበበ ወንጌል ለአለም
ምህላችን ይቀጥላል
እስኪመጣ ለዘላለም
አንድ ሳምንት የፆም ስግደት
ህማማቱ ሊጠብቀን
ከበሮውን ሰማይ ሰቅለን
አመስግነን ለአንድ ቀን

ከመድረኩ ነጭ ለብሰው
ከበሮውን እየመቱ
ክብ ሰርተው ሲዘምሩ
እንደያኔው ህፃናቱ
ምን ተሰማሽ በድምቀቱ
አይኔ ካንቺ ተመልክቷል
ጠብታ ውሃ የምታክል
ዘለላ እንባ ከአይንሽ ወቷል
ለምን አዘንሽ በደስታ ቀን
ይታወቃል
የልቦናሽ   ንጽህና
የእግሮችሽን ጣቶች ላንፃ
ፀሎተ ሀሙስ ይድረስና?

አትፈልጊም አውቃለሁኝ
እንኳን ማጠብ እንዲያዩሽም
የኤደን ውስጥ በለስ እንጂ
የዱር ኮሽም አይደለሽም
ታዲያ ያለሙን ጣጣ ረስቶ
ልቤ ሰከን ከሚልበት
እንዲታወክ ቤተ መቅደስ
ባትመጪ ምን አለበት?

ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ንጉስ አየን ከድንግል ሴት
ፀሀይ ወጣ ከአርያም

የገላውን ስጋ ቆርሰው
በቀናት ውስጥ የሚገሉት
ጨርቃቸውን አገላድመው
በእልልታ ተቀበሉት
የኛ ህዝብም ደምቋል ዛሬ
መስቀል ሰርቷል ከመረጠው
ጎልጎታ ላይ እስኪሰቀል
ወዳጅ ስሞ እስኪሸጠው
የኔ ግና ተበጥሷል
የአይኔ ላይ መቀነቻ
ከዚህ ሁሉ ተነጥለሽ
ምትታዪኝ አንቺ ብቻ
ምናለበት ባገለግል
ቤተመቅደስ ሌላ አላጣሽ
እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ
እኔ ደብር ምን አመጣሽ?

By @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii


>>Click here to continue<<

ግጥም ብቻ 📘




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)