TG Telegram Group & Channel
ግጥም ብቻ 📘 | United States America (US)
Create: Update:

ምን ትሆን

አንዷ ሴት
አጎንብሳ ብትቀር ከልብህ መደብ ስር
ለትሁት ትከሻዋ አመቻቸህ ቀንበር
ሌላዋ
ለፍቅር አጎብድዳ ታጥቃ ብትመጣ መቀነቱዋን በዙር
እሱኑ አስፈትተህ ሰራህላት እስር
ወገቡዋ አንዳይቀና ጉልበቱዋ እንዳይኮራ
በሶስተዮሽ ገምደህ በሰራሀው ገመድ
ሶስት ዙር አሰርካት አንዳይቀናት መንገድ
በግድ የገዛሃት ሽባ አርገህ መላዋን ሌላም አለች
ለማየት ንጋቱዋን ተስፋ የቆረጠች
ሰማዩዋን በጣሪያ ፀሐይዋን በደመና የሸፈንከው
ዉብ ወዙዋን ጠጥተህ እንባዋን የላስከው
ከዛ ጀግኒትን አየሃት
ወደድኩሽ ብለህ እግርህ ስር ልጥላት
እንደለመድክ
አደፈጥክ
ግና
እይዛት ብለህ ባጠመድከው ወጥመድ እራስህ ወደክ
እጅ በእጅ ተቀበልካት ግፍ እዳህን
ሰፍራ ሰጠችህ መከራህን ...
እዳህን ለመክፈል ዘመንህ አጠረ
በወንድነትህ ለቀጠፍቀው ፍሬ ስርህ ደርቆ ቀረ
በጋህ አልፎ ዘመንህ ሐምሌ ሆነ
ስላስነባሃቸው እንባዎች አይንህ ደም አቀረረ
ስለፈታሃቸው መቀነቶች ያንተ ወገብ ሰለለ
ስላጨለምካቸው ፀሐዮች ጨረቃም ላይወጣልህ ማለ
ያንድ ሴት ገድል  ስለስንቱ ድል አረገ
እልፍ አንስት ያነባው እንባ ባንድ መዳፍ ተጠረገ
አልገባህ እንጂ አላወከው
ወትሮም ሔዋን የዳነቺው በማርያም ነዉ
አንተ ግን
ምን ትሆን ....

@getem
@getem
@getem

By @Yodan

ምን ትሆን

አንዷ ሴት
አጎንብሳ ብትቀር ከልብህ መደብ ስር
ለትሁት ትከሻዋ አመቻቸህ ቀንበር
ሌላዋ
ለፍቅር አጎብድዳ ታጥቃ ብትመጣ መቀነቱዋን በዙር
እሱኑ አስፈትተህ ሰራህላት እስር
ወገቡዋ አንዳይቀና ጉልበቱዋ እንዳይኮራ
በሶስተዮሽ ገምደህ በሰራሀው ገመድ
ሶስት ዙር አሰርካት አንዳይቀናት መንገድ
በግድ የገዛሃት ሽባ አርገህ መላዋን ሌላም አለች
ለማየት ንጋቱዋን ተስፋ የቆረጠች
ሰማዩዋን በጣሪያ ፀሐይዋን በደመና የሸፈንከው
ዉብ ወዙዋን ጠጥተህ እንባዋን የላስከው
ከዛ ጀግኒትን አየሃት
ወደድኩሽ ብለህ እግርህ ስር ልጥላት
እንደለመድክ
አደፈጥክ
ግና
እይዛት ብለህ ባጠመድከው ወጥመድ እራስህ ወደክ
እጅ በእጅ ተቀበልካት ግፍ እዳህን
ሰፍራ ሰጠችህ መከራህን ...
እዳህን ለመክፈል ዘመንህ አጠረ
በወንድነትህ ለቀጠፍቀው ፍሬ ስርህ ደርቆ ቀረ
በጋህ አልፎ ዘመንህ ሐምሌ ሆነ
ስላስነባሃቸው እንባዎች አይንህ ደም አቀረረ
ስለፈታሃቸው መቀነቶች ያንተ ወገብ ሰለለ
ስላጨለምካቸው ፀሐዮች ጨረቃም ላይወጣልህ ማለ
ያንድ ሴት ገድል  ስለስንቱ ድል አረገ
እልፍ አንስት ያነባው እንባ ባንድ መዳፍ ተጠረገ
አልገባህ እንጂ አላወከው
ወትሮም ሔዋን የዳነቺው በማርያም ነዉ
አንተ ግን
ምን ትሆን ....

@getem
@getem
@getem

By @Yodan


>>Click here to continue<<

ግጥም ብቻ 📘




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)