ቅ ና ት !
(( በአበባው መላኩ))
======©======
.
.
ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ።
~
ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የዕንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የምድር የቀላይ ጥፋት
በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው
ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ ።
…
ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅ
በዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ።
~
ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ
ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ።
.
.
@getem
@getem
>>Click here to continue<<