ድንቄም fool day
"""""""""""""""""""""""
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፤
በበደል ላይ መልሶ ግፍ፤
አስደንግጠህ
ልታስቀኝ
ብትሞክር ከሞት አፋፍ!
ለዚሁም አዳሬ
ጭቅ ጥብ ሆኖ ሳቄ ብትጠልቅም፤
ፍርሃት ሆኗል ም ሴ፥
ሞት ሆኗል ትራሴ፥
ስታስደነግጠኝ በዛው ሄጄ ፍግም!
"አልስቅም!"
እንደ'ቻምና አይደለም ይኑሮው ሁኔታ፤
ሳቃችን በሙሉ
በድባቅ ተመትቶ የጭንቀት ፈገግታ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
>>Click here to continue<<