TG Telegram Group & Channel
ግጥም እና ጥበብ | United States America (US)
Create: Update:

#እብደት_ግን_ምን_ነበር ?

ስትሄጂ ለገባሽዉ
ለቃልሽ ተምኜ ቆሜ ከ አደባባይ፣
ማፍቀር የተሳነው
ልበ ድፍን ሁላ ሙድ ሰይዝ በእኔ ላይ፣

ያበደ አፍቃሪ  ነዉ ስለፍቅር የመነነ፣
ለማትመጣ እንስት ዘመኑን ያበከነ፣
በትመጣለች ተስፋ እሷን እጠበቀ፣
እልፍ ጀንበር ነግቶ እልፍ ፀሀይ ጠለቀ።
እያሉ
በድፍረት  ስለ እኔ  ያወራሉ፣
  ለመጣ
       ለሄደው መንገደኛ ሁሉ።

በእንጀራ ፈትፍታ መዳኒት አብልታው ፣
ከእሷ ሌላ እንዳይወድ አንዳች አስነክታዉ ፣
ይኸው ከእሷ ሌላ አለምድም እንዳለ ፣
እሷም ሌላ አገባች እሱም ጨርቁን ጣለ።
ይኸዉ ደስ ይበላት
ላትመጣ ቀጥራዉ  አሳብዳዉ ጠፋች፣
እሱ እሷን ሲጠብቅ እሷ  አዲስ ቤት ሰራች።
እያሉ
  በድፍረት  ስለ አንቺ  ያወራሉ፣
ለመጣ
       ለሄደው መንገደኛ ሁሉ።
እግዜር
የእጇን ይስጣት ይክዳት የሷም መዉደድ፣
እንዳሳበደችዉ
    እሷም በተራዋ ጨርቋን ጥላ ትበድ፣

እያሉ ሲረግሙሽ

አይሆንም በጭራሽ እሷን ክፉ አይንካት፣
ጨርቋን ጥላ አትበድ መዉደዷም አይክዳት፣
እኔ እየጠበኳት ሌላ አዳም ብትለምድም ፣
ትመጣለች ድንገት ጭራሽማ አትቀርም።

ብዬ ስነገሯቸዉ
አብድ ነህ ይሉኛል ነክቶሀል አንዳች ነገር፣
እሲኪ ልጠይቅሽ እብደት ግን ምን ነበር?

የምወዳትን ሰው
የማፈቅራትን ሰዉ
ስትሄድ ለገባችዉ
  ለቃሏ ታምኜ  ሳይጠፋ መዉደዴ፣
ትመጣለች ብዬ
  ቆሜ መጠበቄ እብደት ነበር እንዴ?
 
  #እብደት_ግን_ምን_ነበር....?

✍️Safi Abde

#እብደት_ግን_ምን_ነበር ?

ስትሄጂ ለገባሽዉ
ለቃልሽ ተምኜ ቆሜ ከ አደባባይ፣
ማፍቀር የተሳነው
ልበ ድፍን ሁላ ሙድ ሰይዝ በእኔ ላይ፣

ያበደ አፍቃሪ  ነዉ ስለፍቅር የመነነ፣
ለማትመጣ እንስት ዘመኑን ያበከነ፣
በትመጣለች ተስፋ እሷን እጠበቀ፣
እልፍ ጀንበር ነግቶ እልፍ ፀሀይ ጠለቀ።
እያሉ
በድፍረት  ስለ እኔ  ያወራሉ፣
  ለመጣ
       ለሄደው መንገደኛ ሁሉ።

በእንጀራ ፈትፍታ መዳኒት አብልታው ፣
ከእሷ ሌላ እንዳይወድ አንዳች አስነክታዉ ፣
ይኸው ከእሷ ሌላ አለምድም እንዳለ ፣
እሷም ሌላ አገባች እሱም ጨርቁን ጣለ።
ይኸዉ ደስ ይበላት
ላትመጣ ቀጥራዉ  አሳብዳዉ ጠፋች፣
እሱ እሷን ሲጠብቅ እሷ  አዲስ ቤት ሰራች።
እያሉ
  በድፍረት  ስለ አንቺ  ያወራሉ፣
ለመጣ
       ለሄደው መንገደኛ ሁሉ።
እግዜር
የእጇን ይስጣት ይክዳት የሷም መዉደድ፣
እንዳሳበደችዉ
    እሷም በተራዋ ጨርቋን ጥላ ትበድ፣

እያሉ ሲረግሙሽ

አይሆንም በጭራሽ እሷን ክፉ አይንካት፣
ጨርቋን ጥላ አትበድ መዉደዷም አይክዳት፣
እኔ እየጠበኳት ሌላ አዳም ብትለምድም ፣
ትመጣለች ድንገት ጭራሽማ አትቀርም።

ብዬ ስነገሯቸዉ
አብድ ነህ ይሉኛል ነክቶሀል አንዳች ነገር፣
እሲኪ ልጠይቅሽ እብደት ግን ምን ነበር?

የምወዳትን ሰው
የማፈቅራትን ሰዉ
ስትሄድ ለገባችዉ
  ለቃሏ ታምኜ  ሳይጠፋ መዉደዴ፣
ትመጣለች ብዬ
  ቆሜ መጠበቄ እብደት ነበር እንዴ?
 
  #እብደት_ግን_ምን_ነበር....?

✍️Safi Abde


>>Click here to continue<<

ግጥም እና ጥበብ




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)