TG Telegram Group & Channel
ፍቅር እና ጠበሳ | United States America (US)
Create: Update:

ያገር ልጅ ህይወቱ ፣ ከ ጽሁፍ ሲጣቀስ
እንዴት ዝቅ ይባላል ፣ ከ ሽንት ቤቱ ጥቅስ?
"Work as a slave live as a king"
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ስራው ማለት ኑሮው ፣ በሆነባት ሃገር
እንደባርያ ስራ ፣ እንደ ንጉሶች ኑር
ይለኛል ገራገር
.
.
ተረግጦ ተረግጦ
ተረግጦ ሲብሰው
እንደ ነገስታት ኑር ፣ ይለኛል  የዋህ ሰው
.
.
የብሶቱን ጽዳጅ
ሊጸዳዳው መጥቶ ፣ ባለ ሽንትቤቱ
ዝቅ በል ይለኛል
ብቸኛ ነው መሰል ፣ ዝቅ ያለው ህይወቱ
.
.
ብቸኛ ነው መሰል ፣ መውረዴን ይመኛል
ከዚህ በላይ ዝቅጠት
ከዚህ በላይ ውርደት ፣ ከወዴት ይገኛል
ፅድድቱን ረስቶ
ሽንት ቤት በጻፈው ፣ ንጉሦ ነኝ ይለኛል
.
.
አላወቀም እንጂ...
ሳር ሳሩ እየታየ ፣ በተማሰ ቅጥር
ጎምበስ ብሎ ሰርቶ ፣  ቀና ማለት ቢጥር
ቁልቁል ነው ሚወረድ ፣ ዝቅ ባለ ቁጥር
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ ዜማ ወጥቷት ዕምባ
መወጣጫ ሲሆን ፣ ያጎንባሽ ሰው ጀርባ
ዝቅ አልኩኝ እያለ ፣ ሰው ገደል ሲገባ
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ እምባ ወጥቷት ዜማ
የለፍቶ አደር መዳፍ ፣ ቀን ተ ቀን ሲደማ
ማለዳ ማለዳ ፣ እሮሮ ስትሰማ
<ምንአረኩ> እያለ ፣
ሰው አምላኩን ሲያማ።
.
.
ወፊቱ በትዝብት ፣ እንዲ አለች አንድ ቀን
<ከፍ ብለን ስናይ ፣ እኛም  ከሰው ልቀን
አይፍጠርህ እንጂ ፣ ከታችኛው መደብ
አንተም ስትረግጥ ነው ፣ ከላይ ምትመደብ>
.
.
አይፍጠር ነው መቼስ

                            [ ቶማስ ትግስቱ ]

@fonkabcha1

ያገር ልጅ ህይወቱ ፣ ከ ጽሁፍ ሲጣቀስ
እንዴት ዝቅ ይባላል ፣ ከ ሽንት ቤቱ ጥቅስ?
"Work as a slave live as a king"
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ስራው ማለት ኑሮው ፣ በሆነባት ሃገር
እንደባርያ ስራ ፣ እንደ ንጉሶች ኑር
ይለኛል ገራገር
.
.
ተረግጦ ተረግጦ
ተረግጦ ሲብሰው
እንደ ነገስታት ኑር ፣ ይለኛል  የዋህ ሰው
.
.
የብሶቱን ጽዳጅ
ሊጸዳዳው መጥቶ ፣ ባለ ሽንትቤቱ
ዝቅ በል ይለኛል
ብቸኛ ነው መሰል ፣ ዝቅ ያለው ህይወቱ
.
.
ብቸኛ ነው መሰል ፣ መውረዴን ይመኛል
ከዚህ በላይ ዝቅጠት
ከዚህ በላይ ውርደት ፣ ከወዴት ይገኛል
ፅድድቱን ረስቶ
ሽንት ቤት በጻፈው ፣ ንጉሦ ነኝ ይለኛል
.
.
አላወቀም እንጂ...
ሳር ሳሩ እየታየ ፣ በተማሰ ቅጥር
ጎምበስ ብሎ ሰርቶ ፣  ቀና ማለት ቢጥር
ቁልቁል ነው ሚወረድ ፣ ዝቅ ባለ ቁጥር
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ ዜማ ወጥቷት ዕምባ
መወጣጫ ሲሆን ፣ ያጎንባሽ ሰው ጀርባ
ዝቅ አልኩኝ እያለ ፣ ሰው ገደል ሲገባ
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ እምባ ወጥቷት ዜማ
የለፍቶ አደር መዳፍ ፣ ቀን ተ ቀን ሲደማ
ማለዳ ማለዳ ፣ እሮሮ ስትሰማ
<ምንአረኩ> እያለ ፣
ሰው አምላኩን ሲያማ።
.
.
ወፊቱ በትዝብት ፣ እንዲ አለች አንድ ቀን
<ከፍ ብለን ስናይ ፣ እኛም  ከሰው ልቀን
አይፍጠርህ እንጂ ፣ ከታችኛው መደብ
አንተም ስትረግጥ ነው ፣ ከላይ ምትመደብ>
.
.
አይፍጠር ነው መቼስ

                            [ ቶማስ ትግስቱ ]

@fonkabcha1


>>Click here to continue<<

ፍቅር እና ጠበሳ




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)