TG Telegram Group & Channel
ፍቅር እና ጠበሳ | United States America (US)
Create: Update:

፨፠፨ 'ትዝብት' ፨፠፨


በተቀመጥኩበት በሃሳብ ተውጬ
የዚህ አለም ነገር ገርሞኝ ተመስጬ
እንዲህ አስብ ነበር በዚህ ምድር ያለ
የሚርመሰመሰው ወዲህ ወዲያ እያለ
ቢሆን ምን አለበት ሁሉ ሰው አንድ አይነት
ተስተካክሎ ፍጥረት ቢኖር በእኩልነት
እንዲህ ምናያቸው ትንሽና ትልቅ
ባይበላለጡ ባይሉ ከፍና ዝቅ
አንዱ ቤት ተራቁቶ ጠፍቶ የሚጎረስ
ሌላው እጅግ ተርፎት ምግብና አልባሳት
አንዱ ቤት ልጅ በዝቶ የሚቀምሰው ጠፍቶ
መሃኑ ለመውለድ አይኑ ተንከራቶ
አገር የሚጠቅመው ታላቁ ሰው ሞቶ
የመንገድ ላይ እብድ እድሜው እጅግ ገፍቶ
እናት አባት ሞተው ሲፈርስ ቤታቸው
ጎዳና ሲወጡ ብዙ ልጆቻቸው
እውቀት ያለው አጥቶ ለስራው መነሻ
ገንዘብ ያለው ሰው አርጎት መንተራሻ
ውሸት በአለም ነግሶ ተሸፍና እውነት
ሰው በአፉ ብቻ በሽንገላ ሲበልጥ
አንደኛው ሲደሰት በሳቅ ተፍለቅልቆ
ጎረቤቱ በሃዘን በለቅሶ ገርጥቶ
አስተዋልኩኝና ሆኖብኝ ድንግርግር
አስገርሞኝ የዚች አለም ነገር
ግና....
ብርሃን ለማየት ጨለማ ግድ ነው
ጨለማ ካልኖረ ብርሃን ምንድነው
ፍቅር ሚታወቀው ጥላቻ ሲኖር ነው
ስለዚ ይጉዋዛሉ አብረው ልዩነቶች
በብዙ ታጅበው በተወዳዳሪዎች
ለሚበልጠው ነገር በፍጥነት በአላማ
ሰውም ይራመዳል በተስፋ ጎዳና


@fonkabcha1
@fonkabcha1

፨፠፨ 'ትዝብት' ፨፠፨


በተቀመጥኩበት በሃሳብ ተውጬ
የዚህ አለም ነገር ገርሞኝ ተመስጬ
እንዲህ አስብ ነበር በዚህ ምድር ያለ
የሚርመሰመሰው ወዲህ ወዲያ እያለ
ቢሆን ምን አለበት ሁሉ ሰው አንድ አይነት
ተስተካክሎ ፍጥረት ቢኖር በእኩልነት
እንዲህ ምናያቸው ትንሽና ትልቅ
ባይበላለጡ ባይሉ ከፍና ዝቅ
አንዱ ቤት ተራቁቶ ጠፍቶ የሚጎረስ
ሌላው እጅግ ተርፎት ምግብና አልባሳት
አንዱ ቤት ልጅ በዝቶ የሚቀምሰው ጠፍቶ
መሃኑ ለመውለድ አይኑ ተንከራቶ
አገር የሚጠቅመው ታላቁ ሰው ሞቶ
የመንገድ ላይ እብድ እድሜው እጅግ ገፍቶ
እናት አባት ሞተው ሲፈርስ ቤታቸው
ጎዳና ሲወጡ ብዙ ልጆቻቸው
እውቀት ያለው አጥቶ ለስራው መነሻ
ገንዘብ ያለው ሰው አርጎት መንተራሻ
ውሸት በአለም ነግሶ ተሸፍና እውነት
ሰው በአፉ ብቻ በሽንገላ ሲበልጥ
አንደኛው ሲደሰት በሳቅ ተፍለቅልቆ
ጎረቤቱ በሃዘን በለቅሶ ገርጥቶ
አስተዋልኩኝና ሆኖብኝ ድንግርግር
አስገርሞኝ የዚች አለም ነገር
ግና....
ብርሃን ለማየት ጨለማ ግድ ነው
ጨለማ ካልኖረ ብርሃን ምንድነው
ፍቅር ሚታወቀው ጥላቻ ሲኖር ነው
ስለዚ ይጉዋዛሉ አብረው ልዩነቶች
በብዙ ታጅበው በተወዳዳሪዎች
ለሚበልጠው ነገር በፍጥነት በአላማ
ሰውም ይራመዳል በተስፋ ጎዳና


@fonkabcha1
@fonkabcha1


>>Click here to continue<<

ፍቅር እና ጠበሳ




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)