ቤትሽ እየመጡ መንገድ እያስቆሙ
ስለአብሮነታችን ለጠየቁሽ ሁሉ
እንደዚህ አልሽ አሉ
የኔንማ አታንሱ የሱን አታስታውሱ
እኔማ ልጅት ሞኝ ለፍቅር እኮ ስል
ቲማቲም መስዬ ኳ ብዬ እስክበስል
እንደ ቡሄ ዳቦ እሳት ነዶብኛል
ከታችና ከላይ
እናሳ ምን ልሁን እስቲ ከዚህ በላይ
ማለትሽን ሰማሁ አይደበቅ ወሬ
እርግጥ እውነትሽን ነው
አልዋሸሽም ፎቅሬ
ግንስ ከላይ ከታች ያለውን የእሳት ጠል
ወደውስጡ ዘልቆ ዳቦ እንዳይቃጠል
ይለብስ የለ ወይ ሙሉ የኮቦ ቅጠል
ታድያ እኔስ ብሆን አንቺ እንዳትጎጂ
ኮቦሽ እንደነበርኩ ተናገሪ እንጂ
እንዲያውም ፍቅሬ ሆይ አንቺ ታድለሻል
ገማጭ እንዳታጪ በልኩ በስለሻል
እኔ ኮባሽማ ልውል ስለማችል
ከአንድ ጊዜ በላይ ለድፎ ጋገራ
ከአንቺ ላይ ተልጬ ተጥዬልሻለሁ
ከቆሻሻ ጋራ.....
━
@fonkabcha1
@fonkabcha1
>>Click here to continue<<