ለምን
የተረገመ ሂወት የተረገመ ማቅ
ውስጡ ቆሽሾ ጠውልጎ ውጪው እጂግ ደማቅ
መታየት ሰልችቶት መታማት አጥፍቶት እንዲ ለሚባክን
ሰሚ የሌለው ጩኸት እየጮኸ እንዲው ለሚኳትን
እየኖረ ላለ መፈቀር እርቆት ማጣትም በዝቶበት
ለመቅረብ ሳይችል እያገኘ እያጣ ደስታውም ጠፍቶበት
ለምን ቢል ቢሳለቅ እብድም ቢያረገው አቅሉን ቢያሳጣው
በሱሶች ቢደበቅ አለው የሚል አቶ ውድቀቱ ቢከብደው
ለምን ቢል ድጋሚ አምላኩን ቢጠይቅ
እንደሰው ለመቆም ጥፋቱን ለማወቅ
እንዲው መባከኑን ሁሉም እንደራቀው
መንገድ እንደሌለው መኼጃ እንደጠፋው እራሱን እየጠላ በበደል ቢቀጣ
ማነው ሚረዳው ሰላሙን እንዳጣ
የፈጠረው እንኩዋን እንደዘነጋው ሰው እንዲ ሲሆን አይቶ እሱም ፀጥ ካለው
ማን ይሆን ለዚ ሰው አለውልህ ሚለው
እና ይሄ ሰው ለምን ቢል ማን ሊመልስለት
ልቡ እንደቆሰለ ጠጋ ብሎ ማን ጥቂት ሊያይለት
ግን ይሄ ሰው አሁንም በተስፋ ለምን ይላል ቆሞ መልስ እየፈለገ
እየኝ ይላል ደጋግሞ ለሁሉም ጥያቄ መልስ እየፈለገ
መጥቆሩን መክሳቱን ከሰውነት ማረግ እጅጉን መውጣቱን ለምን ቢያስብለው
የሚያየው ፈጣሪ እንደሚያነሳው ተስፋ ስላለው ነው
✍አሚር አደም
@fonkabcha1
@fonkabcha1
>>Click here to continue<<