TG Telegram Group & Channel
አስታውስ | United States America (US)
Create: Update:

ለነፍስህ እዘንላት ፣ ልብህ በግርግር እንዳትጠፋ ጠብቃት።
አላህ ነፃ አድርጎ ለትልቅ አላማ ከፈጠረህ በኋላ ስለምን የአጀንዳ ተጠቂ ትሆናለህ?
አንተ ቆሻሻ መጣያ አይደለህም ፣ ሚናህን ለይተህ እወቅ የሚመለከትህ ነገር ላይ አተኩር ፣ ማንም በየቀኑ አዳድስ አጀንዳ እየፈጠረ እርጋታህን እንዳይቀማህ።

የተፃፈውን ሁሉ እያነበብክ ነፍስህን እረፍት አትንሳት ፣ timelineህን ስርኣት አስይዘው ማንን መከተል እንዳለብህ በደንብ አስብበት ፣ ለጀሰድህ ምግብ መርጠህ እንደምትመግበው ሁሉ ለሩህህ እየመገብከ ያለውን ነገር አጢነው ፣ የቁርጥራጭ ሀሳቦች ማከማቻ አትሁን ፣ አላህ አክብሮ እንደፈጠረህ ሁሉ ራስህን አክብረው ፣ ልብህ የአላህ ቤት ናት ወደሷ ሚሄደውን ነገር ተቆጣጠር ፣ አቅልህን የአጀንዳ ፈጣሪዎች መደበሪያ አታድርጋት🙏

በተለይ የሰዎችን ድንበር ከመንካት ተቆጠብ ፣ የተላላቆች ክብር ላይ መረማማድንም እንደቀልድ አድርገው እንዳያለማምዱህ እምቢ በላቸው ፣ ህይወት አለብን ፣ የኑሮ ውድነቱ የቤተሰብ ሀላፊነት ጭንቀቱ ፣ ከምትኖርበት ቤት ጀምሮ ምን አልባት ክፍያ ይጠበቅብሃል ፣ ታድያ ስለምን በማይመለከትህ ጉዳይ ከግራ ወደ ቀኝ ስትሮጥ ቀንህ ይመሻል?
ሁሉም ነገር አህል አለው ባለቤቱ ይጨነቅበት ፣ ይመለከተኛል የምትለው ነገር ካለ ደግሞ ስራዬ ብለህ በደንብ ያዘው ፣ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አካላት መረጃ አደራጅ ፣ እርግጠኛ ባልሆንከው ነገር ላይ የሰዎችን ክብር ከማጉደፍ ተጠንቀቅ ፣ karma መጥፎ ነው ነገ ዙሮ ቤትህ ይገባል።

ኣዒሻ ረ.ዐ በውሸት ስሟ የጠፋበት ክስተት ሀዲሰል ኢፍክ ተብሎ በስርኣት ተሰንዶ በቁርኣን ተደግፎ ታሪኩ ለእኛ የተላለፈው እንድንማርበት እንጂ ለመረጃነት ብቻ አይደለም።
ሃሻ በላቸው ፣ ባልተሟላ መረጃ ላይ ተመርኩዘህ የማንንም ሀሳብ አታስተጋባ።
አንተ ክቡር ሰው ነህ ፣ ክቡር ሰው ነሽ። ኢኮኖሚካሊ ባደጉት ሀገራት ላይ የሰዎችን concentration ለማጥፋት ወጣቱ በእርጋታ እንዳያስብ ለማድረግ በጀት የሚመደብበት ዘመን ላይ ነን፣ ኢልሃድን ለማስፋፋት የሚንቀሳቀሱ አካላት የመጀመርያ እርምጃቸው ልቦች ላይ ብዥታን መፍጠር ፣ ስክነትን ከወጣቱ ላይ ማጥፋት ነው ፣ ከዛ ሀይማኖቶች በራሳቸው ጊዜ ፎርሙላ ብቻ ይሆናሉ ፣ እምነት የሚባለው ነገር ይጠፋል ፣ ዝምብለህ አስብ አንዳንዴ ከነፍስህ ጋር ኸልዋ ግባ ከቻልክ በዚህ ዘመን ከማንም የቤት ስራ አትቀበል።

አንተ የምታያቸው ነገሮች ጥርቅም ነህ ፣ ማንነትህ ከአዋዋልህ ይቀዳል ፣ ስርኣትህ ከምታነበው ነገር ይገነባል ፣ ሁሌ ክርክር ፣ ሁሌ ጭቅጭቅ ..
አላህ የሰጠህን energy በማይጠቅምህ ነገር ላይ አታባክን ፣ ልብህን አታድክማት ለነፍስህ እዘንላት።

"እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ ነፍሶቻችሁን አደራ"🙏
ወሰላሙን ዐላ መኒተበዐል ሁዳ
Abas✍️

Forwarded from ሀላል መረዳጃ ዲላ (Abuki)

>>Click here to continue<<

አስታውስ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)