TG Telegram Group & Channel
ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫ | United States America (US)
Create: Update:

«ተሸክሜህ ነው!»

❖ በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል፤ የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው፤ አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው፤ ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ፤ ጥቂትም እንደተጓዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው፤ ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ፤ በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት እንደ ቀድሞው ሁለት ጥላዎች ሳይሆን አንድ ጥላ ብቻ ቀርቶ ታየው፤ ከዚያ ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላም፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ፤ ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት፤ ለምን ተውከኝ?"

❖ እግዚአብሔርም "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም፤ ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት፤ ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም፤ እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም።

በዲያቆን አቤል ካሳሁን

Forwarded from Meliekte S.

>>Click here to continue<<

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)