TG Telegram Group & Channel
Amazing facts | United States America (US)
Create: Update:

ስልጣኔና አንድምታዎቹ

ስልጣኔ ምንድነዉ?
ስልጣኔ ማለት በአንድ ሀገር ዉስጥ ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በራስ አሟልቶ መገኘት መቻልና ይህንንም መብቆ ለትዉልድ ማስቀጠል መቻል ነዉ። አንድ ማህበረሰብ ከሌላ ማህበረሰብ አንዳች እገዛ ሳያሻዉ በማንነቱ ላይ ተመስርተዉ በራሱ በተዋቀሩ ነገሮች ተጠቅሞ ህይወቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ስልጡን ማህበረሰብ ልንለዉ እንችላለን።
ስልጣኔ በዉስጡ ብዙ ነገሮችን ያካተተ ሲሆን በዋናነት የሚጠቀሱት:- ሰነ-ምህንድስና (ከተማ ግንባታ)፣ ስነ-ትምህርት፣ ስነ-ግብርና፣ ስነ-አልባሳት፣ ስነ-መንግስት፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግንባታ ወዘተ ናቸዉ።

ስልጣኔና የድሮ ማንነታችን
በታሪክ መነፅር እራሳችንን ስንመለከት ከማንም ምንም ሳንፈልግ በራሳችን ቆመን መኖር የምንችል ህዝቦች እንደነበርን እንረዳለን። ቀሪዉ የዓለም ማህበረሰብ ጫካ ለጫካ አዉሬ እያደነ በሚኖርበት ዘመን ቀደምት ኢትዮጵያዊያን የቤት እንስሳት በማላመድ የፈጣሪያቸዉን ህግጋት ጠብቀዉ አርደዉ ይመገባሉ፣ አርሰዉ ይዘራሉ፣ ንብ አንበዉ ማር ያገኛሉ። ቀሪዉ ዓለም ራቁቱን በሚኖሮበት ዘመን ቀደምት ኢትዮጵያዊያን ፈትለዉ ይለብሱ ነበር። ቀሪዉ የዓለም ህዝብ ፖለቲካ የሚለበስ ይሁን የሚጠጣ በማያዉቅበት ዘመን ቀደምት ኢትዮጵያዊያን ከጥንታዊነቱ የተነሳ ከየት እንደተመዘዘ የማይታወቅ የንግስና ስርአት ነበራቸዉ። ያለ አንዳች አከቲቪስት ገፋፊነት ወራሪ ሃይልን በአንድነት ሆ... ብሎ በመመከት እራሱን የማያስደፍርና በችግር ግዜ ወታደር፣ በሰላም ግዜ እርሷደር ህዝብ ያለባት ብቸኛ ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ነበረች። የህክምና ሳይንስ፣ የስነ ፈለክና የፊደላት ቀመሮቿም ተዘርዝረዉ አያልቁም። የሚገርመዉ ነገር ደግሞ እነዚህ ሁሉ ስልጣኔዎች በሙሉእነት ላይ የተመሰረቱ ስልጣኔዎች መሆናቸዉ ነዉ። ማለትም ምንም አይነት Side effect የሌለዉ ስልጣኔ መሆኑ ነዉ።
የኢትዮጵያ ስልጣኔ የአየር ብክለት የማስከትል
የኦዞን መሳሳትን የማያስከትል
የማህበረሰብ ቀዉስ የማያስከትል
ከፈጣሪ ጋር የማያጣላ የመሳሰሉትን ስለጣኔ የነበራት ኢትዮጵያ ብቻ ነበረች።

ስልጣኔና አሁናዊ ማንነታችን
ዛሬ ላይ አንድ ሰዉ በዘመናዊ አልባሳት አጊጦ፣ ዘመናዊ መነጽር አድርጎ ሲታይ ያሰዉ እንደ አንድ የስልጣኔ ቁንጮ ተደርጎና ዘመኑን የዋጀ ተደርጎ ይወሰዳል። እዉነታዉ ግን ይህ ሰዉ የቡቲክ አሻንጉሊት እንጂ ሌላ አይደለም። ዛሬ ላይ በይሁንታ ያጌጠበት የሌላ ማንነት መሄድ የሚችለዉ በተቀደደለት ማንነት ነዉ። ነገ ላይ ወንድ ልጅ መልበስ ያለበት ቀሚስ ነዉ በቃ ግዜ ያመጣዉ ፋሽን ነዉ ተብሎ ከቀሚስ ዉጪ ምንም ባያመርቱ ያሰዉ ገዝቶ ከመልበስ ዉጪ ምንም አማራጭ የለዉም አለበለዚያ ራቁቱን መሄድ። መነጽር አምራች ካምፓኒ ከንግዲህ መነጽል አልሸጥልህም ቢል ነገ በምኑ ሊዘንጥ ነዉ?
የያዝከዉ ሞባይልም ሆነ የምታሽከረክረዉ መኪና ሙሉ በሙሉ በሃገር በቀል እዉቀት ካልተመረተ ገዝቶ መጠቀሙ ብቻ እንዴት ስልጡንነት ሊያስብል አይችልም።

ኢኮኖሚክስ፣ አካዉንቲንግ፣ ቢዝነስ መማራችን የምዕራባዊያንን ሸቀጥ ከማሻሻጥ ዉጪ አንድ የራሳችን የሆነ ነገር እንድንይዝ ካላደረገን ስልጣና አይደለም።
ኮሙኒዝም፣ ሶሻሊዝም፣ ካፒታሊዝም እያልን የባእድ ርእይዮቶችን ማፈራረቃችን ብሄራዊ አንድነታችንን ከማጠንከር ይልቅ እርስ በርስ የሚያባላን ከሆነ ስልጣኔ ይህ አይደለም።
የራሳችንን ሸማ በራሳችን እዉቀት ከማዘመን ይልቅ ጥለነዉ በሰዉ ማንነት ማጌጥ ዉርደት እንጂ ስልጣኔ አይደለም።

ይቀጥላል...

>>Click here to continue<<

Amazing facts

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)