የጦቢያ ትንሳኤ
ምንድነው ማንባቱ ዕንባህን መዘርገፍ
ጠላትህ ሲጋልብ እንደማለት ዘራፍ
ከቶ አይችልምና መሞቱ ሊያባባህ
ሸልል ፎክር እና ስደደው አርቀህ
ግርማህን አሳየው ዝናርህን ታጥቀህ
ሰማይ ሆይ አድምጠኝ ስማኝ አስተውለህ
ከጷግሜ በኋላ ዝናብ ነው ጠላትህ
ወዝህን ማድረቂያ መርዛማ ነው ዕንባህ።
ፀሀይም አትሞኝ አትበይ አልወጣም
ቀንሽን ብሪበት ድመቂበት በጣም
ባክሽን ጦቢያዬ ልብሽን አይክፋው
አብቅቷል ወጀቡ የፀደይ ነው ተራው።
ደዌውን ሊያጠፋ ፌጦው ተፈትፍቷል
የእናቶችም አንጀት ለፀሎት ተፈቷል
ልጆች ሽክ ብለዋል አምረዋል በእጅጉ
አባቶች ባርከዋል ተሰውቷል በጉ።
ዕድልሽ ይታደል ደስታሽም ይደሰት
ችግርሽ ይቸገር ሞትሽ ቀድሞሽ ይሙት
እንደ አሸዋ ውሀ በኖ ተኖ ይጥፋ
ምድርሽ በአደይ እና በፍቅርሽ ይሰፋ
በአዲስ አመት መንበር በነገ ድልድይ ላይ
የፍቅር አክሊልን ደፍተሽ በላይሽ ላይ
ደምቀሽ ፈክተሽ ይታይ
መአዛሽ ይታወድ ከርቤሽ ያረስርሰን
በአዲስ እኛ አንኑር አሮጌውን ትተን።
ተፃፈ በ ግሩም ነን መቼም(ሮዛ)
የመለያ ቁጥር - ET-068
Like and join @eshidigital
@tibeb_drawing_and_poem
>>Click here to continue<<