TG Telegram Group & Channel
Ethio One LOVE | United States America (US)
Create: Update:

🔸የፌስቡክ አካውንታችን በቀላሉ እንዲጠለፉ የሚያግዙ ምክንያቶች

▫️የማህበራዊ ትስስር ገጾች በተለይም "የፌስቡክ"(facebook) ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ሊያደርጉት እና ሊወስዱት የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ባለማወቅ እና በመዘናጋት የፌስቡክ አካውንታቸው በመረጃ መንታፊዎች እጅ ሲወድቅ ይስተዋላል፡፡

▫️በሃገራችንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አካውንቴን ተሰረኩኝ የሚል ስሞታ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
በመሆኑም የፊስቡክ ገጽዎ በቀላሉ ለመረጃ መንታፊዎች እንዲጋለጥ ከሚዳርጉ ተጋላጭነቶችን መካከል፦

▫️1 ለፌስቡክ አካውንታችን መግቢያ ቀላል የሆነ የይለፍ-ቃል /password/ መጠቀም
የብዙ ሰዎች የፌስቡክ አካውንታቸው በቀላሉ በጠላፊዎች እንዲወሰድ የሚያደርገው ባለማወቅ እና በመዘናጋት በቀላሉ ሊታወቁ እና ሊገመቱ የሚችሉ የይለፍ-ቃል ዋነኛ ችግር ነው፡፡
በቀላሉ ተገማች የሆኑ ቁጥሮችን መጠቀም ለምሳሌ 123456 ፣ 12121212.፣1112223344፣ በብዛት የተለመዱ ቃላቶችን መጠቀም I Love you, happy birth day, እንዲሁም ስልክ ቁጥርን የይለፍ-ቃል አድርጎ መጠቀም በቀላሉ ሊታወቁ እና በመረጃ ጠላፊዎች አካውንታችን እንዲጠለፍ ያደርጋል፡፡

▫️2 ከማናውቃቸው አካላት በውስጥ መስመር የሚላኩ ሊንኮችን መክፈት የፌስቡክ ተጠቃሚያን ከማያውቁትም ሰው ይሁን ከሚያውቁት ሰው በፌስቡክ የውስጥ መስመር የሚላክላቸውን ምንነቱ ያልታወቀ ሊንክ ለመክፈት መሞከራቸው አካውንታቸው በቀላሉ በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቅ ያደርገዋል፡፡ በተለይም ሊንኩን ተጭነን ለመክፈት ስንሞከር በድጋሚ የይለፍ ቃላችንን ወይንም ፓስወርዳችንን እንድናስገባ ከተጠየቅን እና ካስገባን በቀላሉ አካውንታችን በጠላፊዎች እጅ የመግባቱ እድል ሰፊ ነው፡፡

▫️3 የይለፍ ቃል ለረጅም ጊዜ ሳይቀይሩ መቆየት
አብዛኛዎቹ የፌስ-ቡክ ተጠቃሚዎች የይለፍ-ቃላቸውን ምናልባትም አካውንቱን ከከፈቱበት ቀን ጀምሮ ላይቀይሩት ይችላሉ፡፡ የይለፍ-ቃልን በተወሰኑ ጊዜያት ገደብ አለመቀያየር የመረጃ ጠላፊዎች አካውንታችንን ለመጥለፍ የሚያደርጉትን ሙከራ ላይ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡

▫️4 የፌስቡክ አካውንት የከፈቱበትን ኢ-ሜይል አድራሻ ለሁሉም እንዲታይ ማድረግ
የፌስቡክ አካውንት ለመክፈት ያወጣነውን የኢ-ሜይል አድራሻ ለሁሉም ሰው እንዲታይ (visible to all) ካደረግነው የኛን አካውንት ለመስረቅ ለሚፈልጉ ጠላፊዎች የኢ-ሜይል አድራሻንን በመጠቀም ኢ-ሜይላችንን በመስረቅ በቀላሉ የፌስቡክ አካውንታችንን እንዲጠልፉ ያግዛቸዋል።

? ያልገባችሁን እና ሀሳብ አስተያታችሁን #Comment ከወደዳችሁት #Like
እንድሁም #Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

by:-📌   | -Abelex The Ethiopia- |   📌
.©2022

>>Click here to continue<<

Ethio One LOVE

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)