TG Telegram Group & Channel
ETHIO-MEREJA® | United States America (US)
Create: Update:

ዜና፡ “እኔ በወልቃየትም ይሁን ጸገዴ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንጂ የማንነት ጥያቄ አለ ብየ አላምንም” - አቶ ጌታቸው ረዳ

“እኔ በወልቃየትም ይሁን ጸገዴ የማንነት ጥያቄ አለ ብየ አላምንም” ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአዲስ ሰታንዳርድ አስታወቁ፤ “የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዳለ አውቃለሁ” ብለዋል።

ትላንት ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በሁመራ የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ባወጣው ሪፖርት “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ተገቢ መኾኑን እናምናለን ብለዋል” ሲል ያወጣው ሪፖርት አስተባብለዋል።

ዛሬ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀትር ላይ በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ ስታንዳርድ የጠየቃቸው አቶ ጌታቸው “ከአውዱ ውጭ የተወሰደ ነው” ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የገለጽኩት “እኔ በወልቃየትም ይሁን ጸገዴ የማንነት ጥያቄ አለ ብየ አላምንም፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዳለ አውቃለሁ፤ ያም ሁኖ ግን የእኔ እምነት እንደተጠበቀ ሁኖ፣ እዚህ ያላችሁ ሰዎች አለ ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ፣ የሆነ ይሁን ጥያቄ በሰላማዊ እና በህጋዊ መንገድ ብቻ ነው መፈታት ያለበት” የሚል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የነበሩት አብዘሃኛዎቹ የአስመላሽ ኮሚቴ መሆናቸው በመግለጽ “ወደ ደጋውም ወጥተን ህዝቡም ጋር ተነጋግረን የህዝቡ ስሜት ምን እንደሆነ በተሟላ መልኩ ለመረዳት እንሞክራለን” ስለ ነግሬያቸዋለሁ ብለዋል።

“ዋናው ነገር ግን ሁሉም ጉዳዮች በሰላም እና በህጋዊ መንገድ መፈታት  እንዳለባቸው ማመናችን ላይ” መሆኑን ትኩረት ያደረገ ገለጻ ነው የሰጠሁት ሲሉ አስታውቀዋል።

  hottg.com/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

>>Click here to continue<<

ETHIO-MEREJA®

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)