TG Telegram Group & Channel
Ethio Gym 🇪🇹 | United States America (US)
Create: Update:

#ክብደት_ለመጨመር 12 #ሳይንሳዊ መንገድገዶች ፡🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ክብደት መጨመር ክብደት ለመቀነስ ከሚደረገው ተግባር እኩል ተመሳሳይ ትጋት ይፈልጋል፡፡ ውፍረት ከሽብር አደጋ ባልተናነሰ
የዓለማችን ስጋት በሆነበት ዘመን የተስተካከለ አቋም እንዲኖረን
በርካታ ጥረቶችን እናደርጋለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከልክ በማለፍ
ሁኔታ ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሰዎችም፣ ለበሽታ ሊኖራቸው
የሚችለውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ ለብሰው እንዲያምርባቸውና በሂደቱ ሊከሰትባቸው የሚችለውን ምቾት ማጣት ለማስወገድም
እንዲሁ፣ ተጨማሪ ኪሎ በሰውነታቸው ላይ ለመጨመር
የመፍትሄ በሮችን ሁሉ ያንኳኳሉ፡፡
ባለሙያዎች ታዲያ፣ ከመፍትሄ አቅጣጫዎች የምናገኘው ስብ
ወይስ ጡንቻ የሚለውን ቀድመን መለየት እንዳለብን ያስገነዝቡናል፡፡ አንዳንዶቹ በሰውነታቸው ላይ ስለሚጨምሩት ክብደት ትኩረት አይሰጡም፡፡ ጡንቻ፣ ስብ ወይም የሁለቱ ጥምረት፣ እነዚህ ሰዎች ከብዶና ወፍሮ መታየት ብቻ ስለሆነ ዓላማቸው ወደ ባሰ ሁኔታ ሊሸጋገሩ ይችላሉ፡፡ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች በተሻለ ሁኔታ ክብደት በሰውነታቸው ላይ መጨመር
ስለሚችሉበት መንገድ፣ ከምርምር ውጤቶች የተገኙትን እነዚህ
መመሪያዎች በተቻለ መጠን ለመተግበር እንሞክር፡፡
👉1. #በቀ5-6 #ጊዜ_መመገብ፡-
ክብደት ለመጨመር በቀን ከ5
እስከ 6 ጊዜ መመገብ መጀመር ይኖርብናል፡፡ ታዲያ የመመገቢያ
ሰዓታችን በሚገባ መከፋፈል ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም በአንድ
ጊዜ በምንወስደው ከፍተኛ ምግብ ሳቢያ ጨጓራችንም በስርዓት
መፍጨት እንዳይችልና ሰውነታችን ሁሉንም ካሎሪዎች መቀበል
እንዳይችል ምክንያት ይሆናል፡፡
እርግጥ ነው በየ3 ሰዓታት ልዩነት የምግብ ፍላጎታችን ላይነሳሳ
ይችላል፡፡ ነገር ግን ጫን ብለን መመገባችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ በየዕለቱም የምግብ ፍላጎታችን እያደገ ስለሚመጣ፣ መቸገራችን ይቀንሳል፡፡ በተቻለ መጠን ታዲያ በአመጋገባችን ውስጥ ጤናማ ምግቦችን መምረጣችንን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡
👉2. #ክብደት_የማንሳት_ልምምዶችን በሳምንት ሶስት ጊዜ
ማድረግ ለወንዶች፡-
በክብደቶች በመታገዝ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
ስንጀምር ጡንቻዎቻችንን ማሳደግ እንችላለን፡፡ በሂደትም የክብደቶቹን ሚዛን መጨመር ያስፈልጋል፡፡
ይሄ በተለይ ከሰውነት ክብደታችን ባሻገር ጥንካሬያችንን ማሳደግ እንድንችል የሚረዳን ነው፡፡
👉3. ከ300-500 #ካሎሪዎችን_ማከማቸት
ቀደም ሲል እንደተገለፀው፣ ከ300-500 የካሎሪ መጠን
ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ
የሚያደርገን ከሆነ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ይሄንን የካሎሪ መጠን
ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ
ነው ማግኘት የምንችለው፡፡
👉4. #ሁሉንም_የሰውነት_ክፍል_ማሰራት፡-
በጂም ወይም በቤት ውስጥ ስፖርት የምንሰራ ወይም ክብደት የምናነሳ ከሆነ ሁሉም የሰውነት ክፍላችን በሚገባ እየሰራ መሆኑን ነው በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለብን፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቻችን ትኩረት
የምናደርግባቸው ብዙ የጡንቻ ክፍሎች አሉንና፡፡ ስፖርቱን የሚጀምሩ ብዙ ሰዎች በአንገታቸው፣ ደረታቸው ወይም
ማጅራታቸው አካባ ብቻ ትኩረት በመስጠት ልምምድ በማድረግ
ትልቅ ስህተት ይፈጽማሉ፡፡
ይሄ አካሄድ የሰውነታችን ሚዛን
እንዲበላሽ በማድረግ ሰዎች የማይወዱትን ሰውነት እንድንላበስ
ምክንያት ይሆናል፡፡
👉5. #በፕሮቲን_የበለፀጉ_ምግቦችን_ማዘውተር፡-
ቀደም ሲል እንደተገለፀው ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማሳካት የምንችለው፡፡
👉6. #ካሎሪዎች_መጠጣት፡- የተጠየቅነውን ካሎሪ በመብላት ብቻ ሟሟላት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ወተትና የወተት
ተዋፅኦዎችን፣ እንዲሁም አነስተኛ ስኳር ጋር በፕሮቲን የበለፀጉ
መጠጦችን ነው ማዘውተር ያለብን፡፡
👉7. #በፍጥነት_መመገብ፡-
ይሄ ምክር በተቃራኒ ውፍረታቸውን
መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች የሚታዘዝ ነው፡፡ ሰውነታችን በቂ
ምግብ ስለማግኘቱ ምላሽ እንዲሰጠን የተወሰኑ ጊዜዎችን
ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በፍጥነት መመገባችን ከሰውነታችን የጥጋብ
ምልክት ከማግኘታችን አስቀድመን ብዙ እንድንመገብ ያደርገናል፡፡
👉8. #ለማገገሚያ_የተለያዩ #አማራጮችን_መከተል፡-የማፍታቻ እንቅስቃሴዎች፣ ሻወር፣ በካርቦን ሃይድሬት የበለፀጉ ምግቦች፣ ሰውነታችን በፍጥነት እንዲያገግም ይረዳዋል፡፡
ታዲያ የ8፡00 ሰዓት እንቅልፍ እንዳይዘነጋ፡፡
👉9. #በራሳችን_ላይ_ትዕግስት ይኑረን፡-
ጤናማ ባልሆነ አካሄድ
በፍጥነት ተጨማሪ ክብደትን ማግኘት ተጨባጭ አይደለም፡፡
የተቀመጡ መመሪያዎችን በመከተል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ1-2 ኪሎ ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው፡፡
ባለሙያዎች ፈጣን ለውጥ ካላገኘን በቀላሉ ስሜታችን ሊጎዳብን አይገባም ይሉናል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሰው ሰውነት ልዩነት ስላለው፡፡
👉10. #በራስ_መተማመን፡- ክብደት ለመጨመር ያወጣነው ዕቅድ ክብደት የሚለካው ለስኬታማነቱ በራሳችን ላይ ያለን መተማመን ነው፡፡ ከጠንካራ ሥራ በኋላ ለውጥ ማየት ባንችልም፣ ሌላና እጅግ ጠንካራ ወደ ሆነ ልምምድ መግባት ይኖርብናል፡፡
ተጨማሪ ምግብ መመገብ፣ ተጨማሪ ክብደቶችን ማንሳት፣
የውስጥ ጥንካሬን አስጠብቆ መቆት ናቸው፣ ክብደት መጨመር
ከሚፈልግና በራሱ ከሚተማመን ሰው የሚጠበቀው፡፡
👉11. #ረዥም_ርቀት_መሮጥ_ውጤት የለውም፡-
መሮጥ ግዴታ ከሆነ አጫጭር ርቀቶችን እና አቀበቶችን መውጣት ነው ተመራጩ፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የአጭር እና ረዥም ርቀት
ሯጮችን ሰውነት መመልከት ነው፡፡ የትኛውን ነው መሆን የምፈልገው? በማለት ራስን መጠየቅ ደግሞ መሰረታዊ ነው፡፡
👉12. #መተኛት፡-
ከፍተኛ ክብደት ለመጨመር በቀን ቢያንስ 8 እና 9 ሰዓት መተኛት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ ሰውነታችን ምንም ስራ እንዳይሰራ በማድረግ በተኛበት ጡንቻ እንዲገነባ
እናስችለዋለን፡፡ በቀን ውስጥ ከ6 እና ከዚያ በታች እንቅልፍ
እያገኘን ከሆነ፣ በአመጋገባችንና በስፖርት እንቅስቃሴዎች
ያመጣናቸውን ለውጦች ማስጠበቅ አንችልም፡፡
For more join @ethio_gym

>>Click here to continue<<

Ethio Gym 🇪🇹

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)