TG Telegram Group & Channel
Ethio Enlightenment | United States America (US)
Create: Update:

life time lesson.
በቅርቡ አንድ መንፈሳዊ ቦታ ነበርኩኝ በቦታው ላይ ለመቆየት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከመጡት አብዛኞቹ ሠዎች ጋር በጣም ጥሩ የሚባል መግባባት ነበረኝ ።
ሁሉም ለማለት ይቻላል አዲስ የሆነ ሰው ለመቆየት ሲመጣ ተዋውቀው ለማወያየት፣ ተስፋ ለመስጠት እንዲሁም ህይወት መጥፎ ገጿን ስታሳያቸው ለጊዜው ገሸሽ ለማለት የመጣውን እርስ በርስ ለማፅናናት የማይሠለቹ ናቸው 🇪🇹
ማክሰኞ ቀን ነው የቅዳሴ ሰአት እስኪደርስ የገዳሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመቆየት ከእናቴ ጋር እያወራን መንገድ ጀመርን ድንገት አንዲት እናት እጄን ያዝ አደረጉኝ ደነገጥን ፈገግ አሉና "አንዴ ልጅሽን ልስረቅሽ˝ አሉ ወደ እናቴ እያዮ መልስ ሳይኖረን መተያየት ጀመርን ።"እየቀለድኩ ነው ነይ ልጄ ወደ ገዳሙ የሚወሰድ እቃ እንድታግዢኝ ነው አሉ ...........˝።
ተከተልኳቸው ከእማማ ጋር የትውውቃችን አጋጣሚ ይህ ነው (የተባረከች ቀን)ከዛን ቀን ጀምሮ ገዳሙን ለቅቄ እስከምወጣ እንገናኛለን ብዙ እናወራለን (አብዛኛውን ጊዜ የሚያወሩኝ እሣቸው ናቸው )አለማዊውን ፣መንፈሳዊውን ፣የህይወት አጋጣሚዎቻቸውን እንዲሁም የደረሱበትን እና የሰሙትን ታሪክ ሳይሰለቹ ያጫውቱኛል ።
እኔ ፦እማማ አሁን እንደነገሩኝ ከሆነ ግን እኮ ልጁ ራሱን ያጠፍበት የደረሰበት ችግር ከባድ ስለሆነ ነው ፈጣሪ ደሞ ይህንን ስለሚያውቅ በሰማይ ቤት ህይወቱ ያማረ ይሆንለታል አይደል ?
እማማ ፦አዩኝ ለደቂቃዎች አዩኝ
እኔ ፦😳
አንዳንዴ በምጠይቃቸው ጥያቄ ይገረማሉ ፣ይናደዳሉ ፣ይስቃሉ ፣ይቆጣሉ ግን ሁሌም ደስ እያላቸው መልስ ይሰጡኛል ።
እማማ ፦ሀና
እኔ ፦አቤት
እማማ ፦ስንት አባት አለሽ ?
እኔ ፦አንድ 😳
እማማ ፦ሞኚት እሺ ....አሁን በደንብ አድምጪኝ አባትሽን ትወጅዋለሽ ፣ታከብሪዋለሽ እንዲሁም ትፈሪዋለሽ አይደለም ?
እኔ ፦አዎ
እማማ ፦በጣም ጥሩ አሁን ልብ በይ እንግዲህ አባትሽ "ሀና የሰጠሁሽን የቤት ስራሽን ሀሉ በሚገባ ተወጥተሽ ቃሌን በሚገባ በማስተዋል ተግብረሽ የሰጠሁሽ ጊዜ ሲያበቃ ስጠራሽ ብቻ ድምፄን ሰምተሽ ትመጫለሽ ˝አለሽ ሰማሽ ?
እኔ ፦አዎ እማማ
እማማ ፦እሺ እንግዲህ ከዛማ አንቺ የተነገረሽን የአባትሽን ቃል አንዱንም በማስተዋል ሳትተገብሪ ሀሉንም በዋል ፈሰስ ጥለሽ የከበደሽ ይመስልሽና ተሰላችተሽ በገዛ ፈቃድሽ ድምፁን ሳታደምጪ ሳትጠሪ ወደ እሱ ሄድሽ አንበል ልጁ ነሽ ይወድሻል ነገር ግን እጅግ በጣም የሚያዝንብሽ ልቡን የምትሰብሪው አይመስልሽም አንቺስ በፌቱ ቆሞ አይኑን ለማየት ድፍረቱ ይኖርሽ ይሆን እእ ሀና !?
እኔ ፦ ዝም
እማማ ፦በይ ሂጂ በደንብ አሰላስይው አንቺ ልጅ ደሞ ወደ በኋላ እንገናኛለን ....
እኔ ፦እእ እሺ እማማ በቃ በኋላ .....

ሀና ስንት አባት አለሽ 🤔?.....

#All waves pass no matter how high ,stay strong !
#You are important
#always put your hope in God !
Please share it could change the world for one person .
✍️hanu🦋

>>Click here to continue<<

Ethio Enlightenment

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)