Fearless soul (ፍርሃት አልባ ነፍስ)
ታፈቅሪኛለሽ ወይ ብዬ ጠይቄያት አላውቅም እራሴን መጠራጠር ይመስለኛል ፈሪ መሆንን አልፈልግም በተለይ በፍቅር ።ትኩር ብዬ ሳያት ነፍሴ የሳለቻት ነፍስ ያላት ስእል እንጂ ህያው አትመስለኝም ሠው አንዴት ጥርት ያለ ማንነት ይኖረዋል? ።ህይወት አታስጨንቃትም ቀለል አድርጋ ትኖራታለች ደስተኛ ናት ከገንዘብ ጋር የሚጋጋጥ ትግል ውስጥ አይደለችም በቃ አትጨንቅም የሕይወት ሒደቷ በጫካ መሀል ኩልል ብሎ እንደሚወርድ ወራጅ ውሃ ጥርት ያለ ነው እሷ ተፈጥሮ ናት አብረን ስንሆን ስላም ይሰማኛል ሌላ አለም ወስጥ ነኝ አልፈራም ሁሌም አንድ አይነት ናት ።ደፈራርሳ አታስደነግጠኝም በቃ አምናታለሁ ።ውስጤ ላሉት ጥያቄዎች ከንፈሯ ላይ ፣ጣቶቿ ላይ አይኗ ውስጥ አገኛለሁ ታዲያ ታፈቅሪኛለሽ ወይ ጥያቄ ነው?
ፍቅር ረቂቅ ነው!
hanu 🦋
>>Click here to continue<<