TG Telegram Group & Channel
Ethio Enlightenment | United States America (US)
Create: Update:

ውድ ተመራቂዎች🧑‍🎓👩‍🎓

በዛሬው ዕለት ተመራቂ ስትባሉ በአንድ የሙያ መስክ ላይ ምን ያክልእውቀት እንዳለ ያም እውቀት እንዴት ወደ ሃብትና ብልፅግና ደኅንነትና ሰላም፣ ፍትህና ዲሞክራሲን እንደሚሆን ጊዜ እንዴት ገንዘብ እንደሚሆን፣እውቀት ካለ ውሃን ሽቅብ ማፍሰስ ጉምን መዝገንን ለመመልከት ነው።
° ° °
ልክ ክብሪት እንደመጫር ነው። በርቶ ይጠፋም ይሆናል ወይም ይቀጣጠል ይሆናል ፤ ከዚህ በኋላ ለናንተ የተሰጣችው ሃላፊነት ነው። ዛሬ ስውሩ የእውቀት
አለም መጋረጃ ለእናንተ የተገለጠም ስለሆመሆኑ የምስክር ቀን ነው። ለእውቀት መቅደስ ምስጢር ተካፋይ ለመሆን ብቁ እጩ መሆናቹ የተገለጠበት ዕለት ነው።
° ° °
ስለሆነም ዋናው የዕውቀት ፍለጋ ዋናው ትምህርት ቤት ከፊት ለፊታችሁ ነው።
እስከዛሬ መምኅራን ያስተምሯችሁ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን እራሳችሁን በራሳችሁ ታስተምራላችሁ።
° ° °
እስከዛሬ በሳምንት ማብቂያ ወይም በሴሚስተር ማለቂያ ላይ መምህራኖቻችሁ ይፈትኗችሁ ነበር። ከእንግዲህ ወዲህ ደሞ ኑሮ በየቀኑ ትፈትናችኋለች። እስከዛሬ የትምህርት ውጤት A እና B ወይም ቁጥር ነበር። ከዚህ በኋላ ግን የፈተና ውጤታችሁ ብልፅግና ወይም ድህነት ፣ፍቅር ወይም ጥላቻ፣ ሹመት ወይም ሽረት ፣ክብር ወይም ወርደት፣ ህይወት ወይም ሞት ሆኖ ይመጣል
° ° °
በትምህርት ቆይታችሁ በተደጋጋሚ ትፈተኑ ነበር። መፈተን ምን እንደሆነ ፣ የፈተና ውጤት ምን ሊያስከትል እንደሚችል በአግባቡ ተለማምዳችኋል። አዕምሮአችሁ የፕሮብሌምን ሶሉሽን በወረቀት ላይ ማምጣትን ተምሯል።
° ° °
እንድታብራሩ፣ ከብዙ ምርጫዎች ትክክለኛውን እንድትመርጡ፣እውነትና ውሸትን እንድትለዩ ፣ በየወገኑ እንድታዛምዱ ተጠይቃችው አልፋችኋል። አሁን የልምምድ ግዜ አብቅቶ እውነተኛው የፈተና ህይወት ከዚህ በኋላ ይጀምራል። ሙሉ ትጥቅ ይዛችኋልና ይህንን ነባራዊ አለም ለመቀበል ልበሙሉ እንጂ የምትረበሹ አይደላችሁም። የችግር ሁሉ መፍቻ እውቀት መሆኑን ተረድታችኋልና።

~ዓለማየሁ ዋሴ

🀄️🀄️ሉን
@ethio-enlightenment

>>Click here to continue<<

Ethio Enlightenment

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)