TG Telegram Group & Channel
Ethio Enlightenment | United States America (US)
Create: Update:

የሀገር ፍቅር ስሜት-- በምን ይለካል?

▪️የሀገር ፍቅር ስሜት ዓለም አቀፋዊና ሁለንተናዊ ነው፡፡ አንዱ ጋ በርቶ ሌላው ጋ የሚጠፋ ሻማ አይደለም፡፡ ሰውና ሀገር እስካሉ ድረስ አብሮ የሚኖር ነው፡፡ አብሮነቱ ህያው ሲሆን፤ ክሱትነቱም እውነት ነው፡፡ በየትኛውም የዓለም ፅንፍ ወይም እንብርት ላይ የሚኖር፤ በየትኛውም ሀገር ውስጥ የሚላወስ፤ የየትኛውም ሰው ልብ ውስጥ የሚነግስ ነው፤ የሀገር ፍቅር ስሜት!
° ° °
◾️እርግጥ ነው፤ ከሰው ሰው ሊለያይ ይችላል፡፡ ይህ ስሜት ከመሆኑ አንፃር ሊቀያየር የሚችል ነው፡፡ የሀገር ፍቅር በልብ ውስጥ እንደ ማህተም ታትሞ የሚኖር ህያው ስሜት ነው፡፡
° ° °
◾️ሀገርን ሲያጫውቷት የሚነሽጥ፤ ሲኮረኩራት የሚያስቅ፤ ሲኮረኩማት የሚያቃስት!
የሀገር ፍቅር (Patriotism) በየዜጋው ልብ ውስጥ ስሩን ሰዶ፣ የሚያብብ አበባ ነው፡፡
° ° °
◾️ የአበባው ዓይነት ፅጌረዳ ሲሆን በእሾህም የታጠረ ነው፡፡ አባቶቻችን እሾህ ሆነው ወራሪዎችን በመውጋት ሲመክቱ የኖሩት ለዚህ ነው፡፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ለቅኝ ገዢዎች ፈፅሞ የማይመቹ ሆነው ኖረዋል፡፡
° ° °
◾️ወደፊትም ይቀጥላሉ። ጠላትን በየጊዜው መክተው መልሰዋል፡፡ ወደፊም ይመክታሉ፡፡ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ፍቅር እስከ ሞት ይታገላሉ፡፡
° ° °
◾️የሀገር ፍቅር ስሜት እንቅልፍ ይነሳል፡፡ አንድ ባለሀብት ከ‘ኔ ቢጤ ደሀው የበለጠ ንብረቴና ሀብቴ ይሰረቃል ብሎ እንደሚያስበውና ዘ ወትር እንደሚበረግገው ሁሉ ኢትዮጵያውያንም ጠላታቸውን ነቅተው ይጠብቃሉ፡፡ ጠብቀው ይመክታሉ፡፡
° ° °
◾️መክተው ይመልሳሉ፡፡ ይህ የትላንት እውነት ነበር፡፡ ዛሬም ቋሚ እውነት ነው፡፡ ነገም እውን ሆኖ ይ🀄️ጥላል፡፡

Join us 👇
@ethio-enlightenment

>>Click here to continue<<

Ethio Enlightenment

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)