መልዕክተ-Enlightenment
የቆሸሸው ልብስ
አዲስ ጎጆ የቀለሱ ወጣት ሙሽሮች አዲስ ጉርብትና ይጀምራሉ።
በቀጣዩ ቀን ቁርሳቸውን በመመገብ ላይ ሳሉ ሚስት በመስኮት አሻግራ ጎረቤቷ የታጠቡ ልብሶችን ስታሰጣ ታያትና በመገረም ስሜት ውስጥ ሆና እንዴ......!!!
° ° °
ሴትየዋ ወይ ማጠብ አትችልም አልያም ደግሞ ያለሳሙና ነው ልብሶቹን ያጠበቻቸው በጣም ቆሽሸዋል እኮ!!! ባልዬው ግን አንዳች ቃል አላወጣም ነበር።
° ° °
ሁልጊዜ ጎረቤቷ ልብስ ባሰጣች ቁጥር አሻግራ እየተመለከተች ትችቷንና ስድቧን ታወርድባት ጀመር።
° ° °
ታድያ ከወራት በኋላ ያቺው ጎረቤቷ ልብስ ስታሰጣ አይታት ለመተቸት ስትነሳ ልብሶቹ እጅግ ውብና ፅዱ ሆነው ታያቸዋለች።
በመገረም ስሜት ለባሏ አየህ ውዴ በመጨረሻ እንዴት ማጠብ እንዳለባት አወቀች መሰለኝ! ወይ ደሞ አንዷ ባለሙያ ሴት አስተምራት ይሆን?
° ° °
ባል እንዲ ሲል መለሰላት <<ዛሬ ጠዋት ተነስቼ መስኮቶቹን አፅድቼያቸው ነበር።>>
° ° °
⚫️በህይወት ውስጥም እንደዚው ነው። ስለ ሰዎች ያለን እይታ የሚቃኘው በመስታዎቶቻችን ጥራት ላይ ነው።
° ° °
አመለካከት እንደ ሃምሌ ደመና ከጨገገ በውስጡ ንዴትን ፣ ጥላቻና ቅናትን ካዘለ የፍርድን ሰይፍ ለመምዘዝ በእጅጉ የፈጠንን እንሆናለን።
° ° °
🔵ፍርድ ስለተፈራጁ ሳይሆን ስለፈራጁ ይናገራል።!!
ሰናይ ጊዜ....😊😊
Join us 👇
@ethio-enlightenment
>>Click here to continue<<