📜መልዕክተEnlightenment📜
ይህችን ምድር ከተቀላቀልን በኋላ ለመኖር የምንመርጣቸው የራሳችን የሆኑ የኑሮ ዘዬዎች አሉን። እንደ ፊት ገፅታችን ሁሉ ፍላጎትና ምኞቶቻችን፣ባህሪያችን
እጅግ ብዙና የተለያዩ ናቸው። ሁሉም የህይወቱን እሩጫ እንዲሮጥበት የተሰጠው መም ቢኖረውም በየትኛው መም መሮጥ እና እንዴት መሮጥ እንዳለበት ማወቅና መረዳት ደግሞ ለሯጩ የተሰጠ የቤት ስራ ነው።
ከዚህም በመነሳት በምድራችን ላይ ያሉ ሰዎችን በሶስት መደብ ከተን እንመልከት
🔵ተመልካች
- በምድራችን ላይ ካሉ ሰዎች አብዛኛውን ቁጥር የሚወስደው ይህ መደብ ሲሆን መገለጫቸውም የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ከመራመድ ይልቅ ከዳር ቆመው የሌሎችን ስኬትና ጉብዝና እያደነቁ ወይም እየተቹ መኖርን የሚመርጡ ናቸው።
ወደ ሚፈልጉት የህይወት ግብ መጓዝ የሚፈሩት ውድቀትና ሽንፈትን ፈርተው አይደለም ስኬትን እንጂ!!
⚫️ አስመሳዮች(<<የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች>>)
-ይህ ሁለተኛው ጎራ ከመጀመሪያው መደብ በቁጥር ያልተናነሰ ብዛት ያላቸው ሲሆኑ የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች የሚለው ያገሬ ምሳሌያዊ አባባል በእጅጉ ገላጭ ነው። የራሱን እረስቶ በሌሎች ሰዎች ሆነው መታየት የሚፈልጉ ከራሳቸው ደስታና ስሜት ይልቅ በጓደኞቻቸው ፣ በጎረቤቶቻቸው ያልሆኑትን ለመሳል ጊዜያቸውን፣ገንዘባቸውንና ሃይላቸውን ቀለም በሌለው ብሩሽ ለመሳል የሚሞክሩ ሰነፍ ሰአሊዎች ናቸው።
🔴ልባሞቹ
-እነዚህ መደቦች እንደ አልማዝ የከበሩና በቁጥርም ያነሱ ናቸው። ላመኑበትና ለፈለጉት አላማ ህይወታቸውን ለመስጠት ቅጣት ታክል የማይሰስቱ ከመባል
ይልቅ መሆንን ከወሬ ይልቅ ማድረግ የሚመርጡ የጨለማ ሞገስ ያላቸው የባለ
ሁለት ልብ ባለቤቶች ናቸው።
ሁላችንም መደባችን የመምረጥ መብትና አቅም አለን ልባሞችን ለመምሰል ሳይሆን ለመሆን ልብ እንግዛ!!!✨💖
Join us👇
💡@ethio_enlightenment💡
>>Click here to continue<<