TG Telegram Group & Channel
Esat Tv Official (ኢሳት) 🇪🇹️️ | United States America (US)
Create: Update:

ከጤፍ ዱቄት ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮች እና ሰጋቱራ በመቀላቀል ለህብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

ህገ-ወጥ ተግባሩ ሲፈፀም የነበረው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አጠራሩ ቆሼ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መጋዘን ውስጥ ነው። 

በመጋዘኑ ውስጥ 47 ኩንታል ምንነታቸው ያልታወቀ ስራ ስርና የእንጨት ፍቅፋቂ ሰጋ ቱራ 167 ኩንታል የጤፍ ዱቄት ተከማችቶ የተገኘ ሲሆን ባዕድ ነገሩን ከዱቄቱ ጋር የሚደባልቅ መጋዘኑ ውስጥ እንዳይወጣ የተቆለፈበት ሠራተኛ በፍተሻ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል ።

ከአካባቢው ማህበረሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የጅማ በር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በህግ አግባብ  ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በስራ ላይ የነበረውን ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎ  ባደረግው ተጨማሪ   ምርመራ የንብረቱን ባለቤትን አፈላልጎ በመያዝ  ተገቢው  ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ  የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩትን ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ህብረተሰቡ ሲመለከት  ለፖሊስ አጋልጦ በመስጠት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አቅርቧል።

@esattv1

>>Click here to continue<<

Esat Tv Official (ኢሳት) 🇪🇹️️

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)