"የህወሓትን ሃጢአት የማንፃት ዘመቻ"!
ከሁሉም አቅጣጫ የሚዘረጋው መስመር መገናኛቸው አንድ እየሆነ ተቸግረናል። ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከታች ወደ ላይ፣ በሁሉም መልኩ የሚሰመረው ረዲየስ ወደ አንድ ዓላማ እያመለከቱ ነው። ይሄውም በግርግር መሀል የህወሓት በደል እንዲረሳ፣ ሀጢያት እንዲነፃ ማድረግ ሆኗል።
የግራ ዘመሙ ብሄርተኛ ድሮም ህወሃት ላይ አይጨክንም። በስልጣን ሸኩቻ እና ቅናት ለጊዜው ይሻኮቱ ይሆናል እንጂ በአስተሳሰብ አይጣሉም። ህወሓት ድል ቢቀናው ኖሮ ማሊያውን ቀይሮ ለማገልገል ግማሽ ቀን አይፈጅባቸውም። አሁን ጭራሽ በሀላል ህወሓትዬ ነይልኝ እያሉ ነው።
ወትሮ ከህወሓታዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር የሚታረቅ ፖለቲካ የላቸውም የሚባሉትም ዘለው ባቡሩ ላይ እየተሳፈሩ ይገኛሉ። እነኚህ ቡድኖች በሁለት መልኩ ይገለጣሉ። አንደኛው ጎራ በግልጽ "ወያኔ በስንት ጣእሙ" የሚለው ነው። እነኚህ ከአገዛዙ ጋር በጣም ቤተኛ የነበሩና ከጊዜ በኋላ የተጣሉ ናቸው። ቂም፣ በቀል፣ ጥላቻ እና እልህ የሚያራዣቸው disparate and desperate group።
ሌላው ደግሞ ወያኔ ክፉ ብተሆንም፣ ህዝባችንን ሰታሳድድ ብትቆይም፣ ግልገል አንባገነን ብታዋልድብንም፣ ለአሁኑ ጠላታችን ሌላ ነው የሚሉት ናቸው። እንግዲህ ለነኚህ ስብሰቦች ጥቃት እለታዊ እንጂ መዋቅራዊ መሆኑን ይዘነጉታል። የርዕዮተዓለም ጉዳይ በግርጌ ማስታወሻ መልክ ይታለፋል። አንዱን ጨቋኝ አባርሮ ሌላውን መተካት የረዥም ዘመን ልምዳቸው ነው። ነውራቸውን በታክቲክ ስም ማሳመር የአዘቦት ተግባራቸው ሆኗል።
እኔ ግን አንድ ወፍራም የመርህ መስመር አለኝ:- ወያኔያዊ አስተሳሰብን መልሶ ለመትከል ከሚንደፋደፍ ሰብስብ ጋር ምንም ዓይነት ህብረት አይኖረኝም። የተቃውሞ ጎራ ዝም ብሎ ነፃ ትግል ሊሆን አይችልም። በሰላማዊ መንገድ የሚታገል፣ ጠመንጃም ብዕርም እኩል ማንገብ አይችልም። መዋቅራዊ ጥቃትን (structural violence) የሚታገል ወያኔያዊ መንፈስን ሊላበስ አይገባም። ብል[ፅ]ግና ፉንጋ ስለሆነች የፈታናትን ህወሓት በሌላ ቬሎ ሊድረን የሚጥረውን አልቀበልም።
ወያኔያዊ አስተሳሰብ መልሶ አይነግስም። አበደን!
(Moges Zewdu Teshome )
>>Click here to continue<<