እግረ መንገድ -
ወያኔ ቅጥረኛ ነብሰ ገዳይ ጦር የአርሚ 70 ነገር .......
የሱዳንን ሰንደቅአላማ ክንዱ ላይ ለጥፎ አልቡርሃንን በመደገፍ በሱዳን ጦርነት ውስጥ እየተሳተፈ ያለው የአርሚ 70 ጦር አባላት አንድ ችግር ገጥሟቸዋል ተብሏል።
እንደሚታወቀው አልቡርሃን ለወያኔ ከሚከፍለው ዶላር በተጨማሪ ለያንዳንዱ ታጣቂ 300 ዶላር ለመክፈል ተስማምቶ ነበር ታጣቂዎቹን ከወያኔ የገዛቸው።
እስካሁን ድረስ ከ150 ሚሊየን ዶላር በላይ ለወያኔ የተከፈለው ሲሆን የታጣቂዎቹ ድርሻ ወደ ብር እየተቀየረ ና እየተቆራረጠ ሲሰጣቸው ቆይቷል።
አሁን ግን አንድ ችግር ተፈጥሯል። ነገሩ እንዲህ ነው..
ከመቀሌ በመጣ አዲስ ትዕዛዝ መሠረት ከአራት ቀናት በፊት የጦሩ አዛዦች አዲስ መመሪያ አወረዱ።
ይኸውም .."የሱዳን መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ የሰራዊቱ የቀለብና አልባሳት ወጪ የትግራይ መንግስት እየሸፈነ ስለሆነና መንግስትም የትግራይን በጀት ስላቋረጠ ይሄንን እጥረት ለመቅረፍ የበኩላችንን ድርሻ ማበርከት ስላለብን እያንዳንዱ ታጣቂ ከተፈቀደለት 50 ዶላር ውጪ ቀሪው 250 ዶላር ለትግራይ ገቢ እንዲደረግ ወስነናል" የሚል ነው።ይሄንን ውሳኔ ተከትሎ ከመደኒ ወደ ኢትዮጵያ ደንበር (ሸረሪና) ለመዛወር ዝግጅት ላይ የነበሩ የ702ኛ ኮር እና የወዲነጮ ክፍለጦር አባላት
"እስካሁን ድረስ ያልከፈላችሁን 1800 ዶላር እያለ ይህንን ውሳኔ ልንቀበል አንችልም።የተሰጠንን ግዳጅ አንፈፅምም-አንሄድም" ማለታቸው የታወቀ ሲሆን ላለፉት ሁለት ቀናት በእነዚህ "አመፀኛ" በተባሉት አባላት ላይ ሰፊ የእስር ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።በዚሁ ሳቢያም የሚሸሸው ቅጥረኛ ታጣቂ ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ታውቋል።
P.S
ስንት የሚጋራ መረጃ እያለ በባንዳና በቅጥረኛ ነብሰ ገዳይ ወሬ ልጥመዳችሁ ? በቃ ለዛሬ አፉ በሉኝ 😂
>>Click here to continue<<
