TG Telegram Group & Channel
Daniel t(h)omas ኢትዮጵያዊ | United States America (US)
Create: Update:

የቴሌ ኮም ዘርፍ ሽያጭና ሰሞነኛው ዛቻ::
የዓለም አቀፍ ተቁዋማት አመራሮችና የኅያል አገራት መንግስታት በጋራ የቀረጹትን ፖሊሲ ያለ አንዳች ጉርምርምታና ተቃውሞ ወደ ተግባር ለመለወጥ ይረዳቸው ዘንድ ልዩ ጥንቃቄ ያደርጋሉ:: ዕቅዳቸውም በጥንቃቄ የተጠናና የግድ መፈጸም የሚኖርበት ዕቅድ ነውና ለተፈጻሚነቱ ሲሉ ማናቸውንም አይነት መስዋዕትነት ይከፍላሉ:: ከተራ ትችት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በብሄራዊ ደረጃ እስከ መብጠልጠል ድረስ ያለውን ውርጅብኝ በደስታ ያስተናግዳሉ::
የማይግባቡ መስለው ነገር ግን ተናብበው የሚሰሩ ናቸውና በመካከላቸው አንዳችም ጸብ ሳይኖር ውጊያ ቀረሽ ግብግብ ውስጥ የገቡ መስለው ይታያሉ::በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በቃላት ከመወራረፍ ያለፈ ሃሰተኛ የሚሳኤል ውጊያም ሊያደርጉ ይችላሉ:: ዕቅዳቸው ዳር ይድረስ እንጂ የዓለምን ህዝብ ጫጫታና ሃሜት እንዲሁም ትንተና ከመጤፍ አይቆጥሩትም!
በዚህ አይነት ሁኔታ "መስለው" ሳይሆን "ሆነው!" ስለሚተውኑ ለብዙዎች እንዲህ ያለውን እውነት ማስረዳት አይቻልም:: ማስረዳት ቢቻልም አስረድቶ ማሳመን አይቻልም::
እንዲህ ያለውን የረቀቀ አካሄዳቸውን ደግሞ በተቀደደለት የሰበር ዜና ቦይ በሚፈሰው በብዙሃኑ ህዝብ የፕሮፖጋንዳ ጫጫታ ያጅቡታል ሂደቱንም ከህዝብ ዕይታ ይጋርዱታል::የህዝቡን ትኩረት ሌላ ላይ እንዲሆን አድርገው ያቀዱትን ስራም ይሁን ሴራ በመንግስታዊ ህግ ያለ አንዳች ውይይትና ጉርምርምታ በምክር ቤት ደረጃ በሙሉ ድምጽ ያስጸድቁታል::መሻታቸውን በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ያውሉታል::
በዚህ መሰሉ አካሄዳቸው ምክንያትም የነጠሩ ሴራ አዘል እውነቶቻቸው በጩኸት ብዛትና በተደጋጋሚ ሃሰተኛ የሰበር ዜና ርግብግቦሾች ይዳፈኑላቸዋል...::
**********
አብይ አህመድ ስልጣን በያዘ ማግስት ከአንደበቱ የወጣው የመጀመሪያው ቃል "ፕራይቬታይዜሽን..." የሚለው ቃል ነው:: ለዚህም የኖቤል ቀብዱን ወስዶዋል:: ህወሃት (ለራሱና ለቢዝነስ ኢምፓየሩ ሲልም ቢሆን) በአብዮታዊ ዲሞክራሲና በልማታዊ መንግስት ስም ዘግቶ ይዞት የነበረውን ርዕዮት ማስለወጥና ፕራይቬታይዜሽንን ተግባራዊ ማስደረግ ይፈልጉ ነበር::ነገር ግን ኢህአዴግ "ይህ የሚሆነው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ነው!" የሚል ቁርጥ ያለ አቁዋም ይዞ በድርቅናው ቀጥሎ ነበር የቆየው::
አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ይህን ጉዳይ የግድ ተግባራዊ ማድረግ ነበረባቸውና ህወሃት መራሹን ኢህአዴግንና የፕራይቬታይዜሽንን ጉዳይ ዘግቶ የያዘባቸውን የቢዝነስ ኢምፓየር ኤፈርትን ጥለው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ብልጽግናን ተክተዋል::
በብልጽግና አማካኝነትም የቴሌኮሙን ዘርፍ የመቆጣጠር የረጅም ጊዜ ፍላጎትና ህልማቸውን በትላንትናው ዕለት አሳክተዋል::(የቴሌ ኮም ዘርፍ ሲባል የስልክና የኢንተርኔት ዘርፍ ብቻ ማለት ለሚመስላቸው የዋህ ዜጎች እንደዚያ ማለት እንዳልሆነ ወደፊት በስፋት ለማስረዳት ይሞከራል) እናም ያ የአሜሪካና የእንግሊዝ የቀደመ ህልማቸው ዛሬ ተሳክቶ የቴሌኮሙን ዘርፍ እንግሊዝና አሜሪካ በቁጥጥር ስር አውለውታል ወይም ገዝተውታል::
ወይም የመጠቅለል ጅምራቸውን በፓርላማ አስጸድቀው ዘርፉን በበላይነት ይዘውታል::
ሁኔታው ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ እንዲመስልና ዘርፉ ከኢትዮጵያ መንግስት እጅ እየወጣ እንደሆነ እንዳናስብም ከ24 ሰዓት በፊት በሰየሙት አዲስ ስያሜ "Global partnership for ethiopia" ከሚለው አዲስ ስያሜ ጋር አገናኝተው የዘርፉን ሽያጭ ጨረታ ያሸነፉትን አካላት ይፋ አድርገዋል::”አሜሪካና እንግሊዝ የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ገዙት” ከማለት ይልቅም በዚህ መንገድ አጨናብሮ መግለጹ የተሻለ እንደሚሆን ያውቃሉና ዜናውን በዚያ መንገድ ነው ይፋ ያደረጉት::
ዞሮ ዞሮ ግን Vodafone, Vodacom safari com, sumitomo corporation,and CDC group ሄድ ካርተራቸውን የተለያዩ አገራት ያድርጉ እንጂ የሁሉም ተቁዋማት መስራችና ዋና ባለቤት እንግሊዝና አሜሪካ ናቸው::የቴሌኮሙ ዘርፍ የተሰጠውም ለእነርሱ ነው::
ይህ በመሆኑም አሜሪካና እንግሊዝ ደስታቸው ወደር የለሽ ሆኖዋል:: የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚ/ርም ከእነሱ በላይ በደስታ ጮቤ መርገጡን ገልጾዋል:: ለ1.5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል, 8 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ማድረግ ይችላል, 850 ሚሊዮን ዶላር ጨረታውን አሸንፎዋል,ወዘተ የሚለውን ዜናም ለ "መጡልን" ባዮች አብስረዋል::ለ"መጡብን" ባዮች አርድተዋል::
ህዝቤ ደግሞ "አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እቀባ ልታደርግ ነው"
"አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ልትጥል ነው"
"በፍርሃት ኢምባሲዎቻቸውን ዘግተው ዋሉ...
"አሜሪካ ተላላኪዋ ህወሃት ስለወደቀባት ተበሳጭታ የኢትዮጵያን መንግስት ጠምዳ ይዛዋለች...የቀድሞ ወዳጁዋ የህወህት መውደቅ አበሳጭቶዋት... የመንግስት ህግ የማስከበር ዘመቻ ከንክኖዋት ጥምድ አድርጋ ይዛናለች... ይቺን መሰሪ ሰልፍ እንወጣባታለን... ባንዲራዋንም በአደባባይ እናቃጥልባታለን..." ምናምን የሚል ሌላ ጫዋታ ውስጥ ነው::
ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ይህን አይነቱን ሰበር ዜና በመሰባበር ላይ ነው!
በትናንትናው ዕለት በተወካዮቹ አማካኝነት" ተስማምቻለሁ ይሁን" ብሎ ስለፈረመበት ጉዳይ ግን ምንም የገባው ነገር የለም!
ህዝቡ እንዲህ ይነሆልል ዘንድም እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ አፈቀላጤው መሪ ተብየ መድረክ እያመቻቸ "ማንም እንደፈለገ የማያዘን አገራችንን ቁርስ ይህን ብይ እራት ምን በላሽ ይሄን ቀሚስ ልበሽ...የሚሉን ሉዓላዊነታችን ያልገባቸው የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ያልተረዱ..." እያለ የሃሰት ዛቻውን እያንበለበለ በመፎተት የግርዶሹን ቀዳዳ ይደፋፍን ነበር::
በተቀደደለት ቦይ መፍሰስ...የሚለው ጉዳይ በዚህ መንገድም ይገለጻል ለማለት ነው...::
ዲጂታል ሲስተም ውስጥ ከመግባት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ዘርፈ ብዙ ነገሮችን ወደፊት በስፋት የምናያቸው ይሆናል::
እስከዚያ ድረስ ሊንኮቹን ተጭናችሁ እነዚህን 4 ትረካዎች እያደመጣችሁ ቆዩ::
https://youtu.be/SwvgH5TjbSA

https://youtu.be/2aeHXa32gBE

https://youtu.be/Zie4wh8550Y

https://youtu.be/Tnz0kEWE1Ig
በዚህ የፌስቡክ ገጽ ከሚቀርቡ ጽሁፎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሃሳቦች የሚተረኩበት ቻናል ነውና የዚህ ገጽ ተከታዮች ቻናሉን ሰብስክራይብ ብታደርጉለት መልካም መሆኑን እጠቁማለሁ::መልዕክቱንም አስተላልፌያለሁ::
https://www.youtube.com/channel/UCpNPc78FhPGSXhAVVh_jQuA

>>Click here to continue<<

Daniel t(h)omas ኢትዮጵያዊ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)