TG Telegram Group Link
Channel: ብርቅ APPS
Back to Bottom
በዚህ ሁሉ ፍርሃት፣ ሰቀቀን፣ ጭንቀት፣ ህመም እና ሞት ውስጥ ኮሮና ቫይረስ ያመጣው አንድ ጥቅም ተገኝቷል!

@berkapps @berkappsbot
ብርቅ APPS pinned «በዚህ ሁሉ ፍርሃት፣ ሰቀቀን፣ ጭንቀት፣ ህመም እና ሞት ውስጥ ኮሮና ቫይረስ ያመጣው አንድ ጥቅም ተገኝቷል! ምን መሰለህ? አውሮፓ፣ ኤሽያ እና አሜሪካ የሰዎች እንቅስቃሴ እጅጉን ተገድቧል! ከምግብ አቅራቢ እና ጤና ተቋሟት ውጪ ትምህርት ቤቶች፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ ስራ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ተገድበዋል! ይህ ሁሉ ምስቅልቅል ግን ለዓለም አንድ ጥቅም አስገኝቷል! በበካይ ጋሶች ልቀት…»
444 በሚል ቁጥር ስልካችሁ ላይ ሲደወል የየት አገር ቁጥር ነው ብላችሁ በመደናገጥ ፋንታ 😂 አንሱና ስለ ኮሮና ቫይረስ በነጻ ትምህርት ውሰዱ።
Ethio telecom 🙏

#stayclean
#staysafe
⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️
ለመረጃ እና ጥንቃቄ ያህል!!!!

አንዳንድ ሰዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል “Surgical/Medical glove” እና የ “ጨርቅ ጏንት” እያደረጉ ነው!

እውነት “surgical/medical glove” እና “የጨርቅ ጏንት” ቫይረሱን ይከላከላል?

“Surgical/medical/Latex Glove”

በመጀመርያ እነዚህ ጏንቶች የተሰሩት ለህክምና ግልጋሎት ሲሆን የጤና ባለሙያዎች ለአጭር ሰአታት የሚጠቀሙባቸው ናቸው። አነዚህን ጏንቶች በማድረግ አራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ መከላከል አይቻልም። እንደውም አነዚህ ጏንቶች ተጋልጭነታችንን በተቃራኒው ይጨምሩታል። አንደኛ በጣም በቀላሉ የሚቀደዱ (የሚበሱ) ከመሆናቸው ባሻገር ንክኪ ከፈፀምን በኃላ ጏንቱ ላይ ሊከማች በሚችለው ቫይረስ/ቆሻሻ ፊታችንን ወይም ሌላ የሰውነታችንን ክፍል የመንካት እድላችን ሰፊ ነው። በሽታውን በዋነኝነት የምንከላከለው እጃችንን በተደጋጋሚ በመታጠብ ነው። ነገር ግን ጏንት ካደረግን እጃችንን በተደጋጋሚ የመታጠብ አዝማሚያችን ይቀንሳል። ጏንትን ደግሞ ማጠብ አይመከርም። በተጨማሪም “World Health Organisation”(WHO) የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል ከጤና ባለሙያዎች በስተቀር ሰዎች “surgical/medical glove” ወይም “ጏንቶች“ እንዲያደርጉ በፍፁም አይመክርም።

“የጨርቅ ጏንት/Running gloves”

እነዚህ ጏንቶች የተሰሩት እጃችንን ከብርድ ለመከላከል እና ለስፖርታዊ አንቅስቃሴዎች ነው። ከሰሞኑ ብርድ እጅህን ትከላከልበታለህ እንጂ ከኮሮና አይታደግህም አባዬ! እንደውም ቫይረሱ ጨርቅ ላይ ለሰአታት ስለሚቆይ በጏንቱ ይዘኸው የመዞር ሰፊ እድል ይኖርሃል! በዛ ላይ በጨርቅ ጏንቶች ስልካችንን ማዘዝ ስለማንችል በተደጋጋሚ እያወለቅን እናጠልቃቸዋለን! ይህ ደግሞ ንክኪ እና ተጋልጭነታችንን ይጨምረዋል!

ለማንኛውም “surgical/medical glove” ወይም “ጏንቶችን” ለማይጠቅመን ነገር እንደ ጉድ አየሸመትን በኃላ ላይ የጤና ባለሙያዎቻችን እጥረት እንዳያጋጥማቸውና ሌላ ቀውስ ውስጥ እንዳንገባ ስጋ!

#ታጠብ!
#ታጠቢ!
#ታጠቡ!

That is so far the only medically proven way to prevent yourself from this deadly virus!👌👌

@berkapps @berkappsbot
#Coronavirus : ራሳችንን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ስልካችንን እንዴት እናጽዳ? ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ። ምን ያህል ጀርም ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል? ኮሮናንስ ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት?

@berkapps @berkappsbot
ብርቅ APPS
#Coronavirus : ራሳችንን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ስልካችንን እንዴት እናጽዳ? ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ። ምን ያህል ጀርም ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል? ኮሮናንስ ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት? @berkapps @berkappsbot
#Coronavirus : ራሳችንን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ስልካችንን እንዴት እናጽዳ? ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ። ምን ያህል ጀርም ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል? ኮሮናንስ ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት?

ስልካችንን ለማጽዳት 70 በመቶ አልኮል ያለው ዋይፐር መጠቀም የሚቻል ሲሆን በረኪና ግን አይመከርም። ቀላል ሳሙናና ውሃም ለማጽዳት እንደሚያገለግልም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረረርሽኝ እንደሆነ ገልጿል። ድርጅቱ ይህ ወረርሽኝ ራሳችን ልንከላከለው የምንችለው መሆኑንም አስታውቋል።

ይህንንም ለማድረግ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ፊታችንን በተደጋጋሚ አለመነካካት፣ በምናስነጥስበት አልያም በምናስልበት ወቅት አፍና አፍንጫችንን በሶፍት አልያም በክርናችን መሸፈን የሚጠቀሱ መከላከያዎች ናቸው።

በቤታችንም ሆነ በምንሰራበት ስፍራ በተደጋጋሚ የእጅ ንክኪ የሚበዛባቸው ስፍራዎችን ማጽዳት ከመከላከያ መንገዶቹ መካከል አንዱ ነው።
ነገር ግን ስልካችንን በየደቂቃው የምንጠቀም እንደመሆናችን እንዴት ማጽዳት እንዳለብን እስካሁን ካላሰብን ቀጣዩ ጠቃሚ ነጥብ ይሆናል።
ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ በፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ። ምን ያህል ጀርም ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል? ኮሮናንስ ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት?

የአሜሪካን የጤና ስርዓት በበላይነት የሚቆጣጠረው ሲዲሲ በምናስነጥስበት አልያም በምናስልበት ወቅት ከሰውነታችን የሚወጣው ጀርም በሚረጭበት ስፍራ ላይ ለሰዓታት በሕይወት ይቆያል ብሏል። ስለዚህ ቆሽሸው የሚታዩን ነገሮችን በአጠቃላይ እንድናፀዳ ይመክራል።
በማጽዳትና ከቫይረሱ ነጻ በማድረግ ረገድ ልዩነት እንዳለም ተቋሙ ያሳስባል። መጀመሪያ ቆሻሻውን ማጽዳት ቀጥሎም ከቫይረሱ ነፃ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባል።

ስልካችንን ለማጽዳት 70 በመቶ አልኮል ያለው ዋይፐር መጠቀም የሚቻል ሲሆን በረኪና ግን አይመከርም። ቀላል ሳሙናና ውሃም ለማጽዳት እንደሚያገለግልም ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ዶ/ር ሌና ሲሪክ በዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ለንደን ማይክሮባዮሎጂስት ናቸው። እርሳቸው እንደሚመክሩት ከሆነ ስልክዎን ለማጽዳት ከቻርጀሩ መንቀል፣ መሸፈኛ ካለው ማውለቅ ቅድሚያ ልትወስዷቸው የሚገባው ተግባር ነው።
ዋና ዋና የሚባሉት የስልክ አምራቾች ስልካችንን ለማጽዳት ኬሚካሎች፣ ለእጃችን ማፅጃነት የምንጠቀምባቸው ሌሎች እንዲሁም ሸካራ ነገርን ለማጽዳት የሚያገለግሉ ዋይፐሮችን መጠቀምን አይመክሩም።

ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው የስልክዎን ስክሪን መከላከያ ይጎዳሉ አልያም ያወድማሉ የሚል ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ሌና፣ በቀላሉ በውሃና በሳሙና በተነከረ ጥጥ ወይም ከጥጥ በተመረተ ጨርቅ ማጽዳት በቂ ነው። በጥጥ ወይም በጨርቁ የስልክዎን ስክሪንም ሆነ ጀርባ እንዲሁም ጎኖች ማጽዳት ይችላሉ። በዚህ ወቅት ግን የሚያጸዱበት ፈሳሽ በስልኮቹ ክፍተቶች በኩል እንዳይገባ ጥንቃቄ ያድርጉ።

በርግጥ አንዳንድ ውሃን የሚቋቋሙ ስልኮች ቢኖሩም ከጊዜ በኋላ ግን ይህንን ብቃታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በአግባቡ ከወለወሉ በኋላ በለስላሳ ጨርቅ ማድረቅ አይርሱ። ዶ/ር ሌና እንደሚሉት በሳሙናና ውሃ ስልክዎን ማጽዳት ቫይረሶችንና ጀርሞችን ከስልክዎት ላይ ያፀዳል።አይፎንን ስልኮችን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ አፕል ስልክዎን በአግባቡ 70 በመቶ አይሶፕሮፔል አልኮል ባላቸው ዋይፐሮች ማጽዳት እንደሚችሉ ይመክራል። እነዚህን ዋይፐሮች ከኮምፒውተር መለዋወጫዎች መሸጫ ሊያገኟቸው ይችላሉ። በዚህ ሁሉ ስልክዎን ካፀዱ በኋላ ባልታጠበ እጅዎ ከሆነ የሚጠቀሙት መልሶ ስልክዎ በጀርሞች ይሞላል። ስለዚህ እጅዎን በየጊዜው መታጠብ አይርሱ!

Via #BBC
@berkapps @berkappsbot
አፕል iPhone SE 2 የተባለ አዲስ ሞዴል አስተዋውቋል። ይህ ሞዴል ውጫዊ ገፅታው iPhone 8 የሚመስል ሲሆን ውስጣዊ ይዘቱ ከiPhone 11 ጋር ይመሳሰላል ተብሏል። መነሻ ዋጋውም በአንፃራዊነት ረከስ ያለ ሲሆን በአሜሪካ ገበያ $399 ፣በእንግሊዝ ደግሞ £419 ብቻ መሆኑን The Independent ዘግቧል።

@berkapps @berkappsbot
ፌስቡክ በአንድ ጊዜ 50 ሰዎች ጋር የሚደውሉበት ቴክኖሎጂ ይዞ መጥቷል

ኩባንያው እንደተናገረው አዳዲሶቹ ለውጦት ከታሰበላቸው ጊዜ በፊት ቀድመው ይፋ የሆኑት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው። የማርክ ዙከርበርግ ድርጅት ሰዎች ሳይጋበዙ ወደ ቪድዮ ጥሪዎቹ እንዳይመጡ የሚከላከል መላም አበጅቷል።
Sony የኤሌክትሮኒክስ Company ዜሬ አዲስ Headset ለገበያ አቅርቧል ዋጋዉ 279$ እንደሆነ ታዉቋል

@berkapps @berkappsbot
የምትመለከታት የካርቶን ገፀ_ባህሪ "Winnie the pooh" ትባላለች። የህፃናት ተረት ተረት ውስጥ ያለች "Fictional character" ናት!
ቻይና ውስጥ የዚችን አሻንጉሊት ፎቶ ማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ ብታጋራ ወይ ብትለጥፍ ዘብጥያ ልትወርድ ትችላለህ አባዬ!

ለምን መሰለህ?

አንዳንድ የሶሻል ሚድያ ተጠቃሚዎች እና የተለያዩ ግለሰቦች አሻንጉሊቷን ከቻይናው ፕሬዝደንት "Xi Jinping" ጋር በማመሳሰል እያበሸቋቸው ስለሆነ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ደስተኛ አልሆኑም!

የአሻንጉሊቷን ምስሎች ለጓደኞችህ ለማጋራት በማህበራዊ ድህረ ገፅ ብትልከው እንኳን የተላከለት ግለሰብ ጋር አይደርስም!"Censor" ይደረጋል። ቻይና ውስጥ እንደ "facebook" የሚጠቀሙበት "We chat" የተባለው ማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ እቺን አሻንጉሊት ብትለጥፋት በፍጥነት መንግስት ያጠፋዋል! በተደጋጋሚ የምትለጥፍ ከሆነ ደግሞ ተቀፍድደህ እስር ቤት ትገባታለህ!

ምን ልልህ ፈልጌ ነው?

በአሻንጉሊት እና በ "Meme" የሚበሽቅ መሪም አለ ለማለት ነው! 😃

@berkapps @berkappsbot
HTML Embed Code:
2024/05/01 01:57:17
Back to Top