TG Telegram Group Link
Channel: ብርቅ APPS
Back to Bottom
ሀገራዊ ምርጫ እና የሳይበር ደህንነት ሥጋት

በተለያዩ ሀገራት መራጮች እንደ ቀድሞው ድምጻቸውን በወረቀት ከመስጠት ወደ የኤሌክትሮኒክስ ድምጽ መስጫ ማሽኖችን በመጠቀም ለሃገራዊ እና ለክልላዊ ምርጫዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

@berkapps @berkappsbot
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
ሀገራዊ ምርጫ እና የሳይበር ደህንነት ሥጋት

በተለያዩ ሀገራት መራጮች እንደ ቀድሞው ድምጻቸውን በወረቀት ከመስጠት ወደ የኤሌክትሮኒክስ ድምጽ መስጫ ማሽኖችን በመጠቀም ለሃገራዊ እና ለክልላዊ ምርጫዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ኤሌክትሮኒክ ድምፅ /Electronic voting/ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎችን በመጠቀም ድምጽ መስጠትን እና መቁጠርን የሚያግዝ ስርዓት ሲሆን እነዚህ የኤሌክትሮኒክ ድምጽ መስጫ ማሽኖች ደግሞ ከበይነ-መረብ ጋር የተገናኙ ኮምፒተሮችን ይጠቀማሉ፡፡

የድምጽ መስጫ ማሽኖች ከበይነ-መረብ ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን ተከትሎ የሳይበር ጥቃት ሰለባ ስለመሆናቸው መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡

ሀገራት በድምጽ መስጫ ማሽኖች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡
#የምርጫ ስርዓቶችን እንዴት ባለ መልኩ ደህንነታቸዉን ማስጠበቅ እንችላለን?
ሃገራዊም ሆኑ ክልላዊ ምርጫዎችን የሳይበር ደህንነት ሁኔታ ማረጋገጥ ማለት ምርጫን እና የምርጫን መሠረተ-ልማቶች ከሳይበር ሥጋት ወይም ጥቃት መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ይህም የምርጫ ጣቢያዎችን የምርጫ ማሽነሪዎች፣ የምርጫ ቁሳቁሶች፣ የምርጫ ጽ/ቤት በይነ-መረብና መሠረተ ልማቶች እንዲሁም የመራጮች መረጃ ቋትን እንዳይበረበሩ፣ ሰርገው እንዳይገቡ ወይም ጉዳት እንዳይደርሱ መከላከል ነው፡፡

የሳይበር ሥጋት ወይም ጥቃት በምርጫ ወይም በምርጫ መሠረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀመው በተለያዩ አካላት ቢሆንም በውስጥ ሠራተኞች፣ በመንግስት በሚደገፉ የተደራጁ ቡድኖች ወይም ወንጀለኞች አማካኝነት በስፋት ሊከሰት ይችላል፡፡

#የሳይበር ጥቃት ፈጻሚዎች ዓላማ ምንድን ነው?

የሳይበር ጥቃቶችን በምርጫዎች ላይ የሚያደርሱ አካላት መነሻ ዓላማ በምርጫ ሂደቱ ወይም በውጤቱ ላይ ተጽዕኖ ማሳረፍ፤ ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደትን ተዓማኒነትና የህዝብን አመኔታ ማሳጣት ወይም ፖለቲካዊ አለመረጋጋት መፍጠር ነው፡፡
የአሜሪካን የ2016 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ከምርጫ ጋር በተገናኘ የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶች ተፈፅመዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ሀገራት ምርጫዎቻቸው ለሳይበር ጥቃት የተጋለጡ እንዳይሆኑ የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎችን በስፋት ሲሰሩ ይስተዋላል፡፡
#ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ምርጫዎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃችን እንዴት መግታት ይቻላል?

በሃገራት የሚከናወኑ ሃገር አቀፍም ሆኑ ክልላዊ ምርጫዎች በማንዋል /Manual/ እና ቴክኖሎጂ መሠረት ባደረጉ /technology based/ ዘዴዎች በቅንጅት የሚከናወን ነው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረቀት እና ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ የመሥራት አዝማሚያ በስፋት የሚስተዋል ሲሆን ይህም በከፍተኛ ሁኔታ እያጋጠመ የመጣውን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የሳይበር ጥቃትና ተከትሎ የሚመጣውን አደጋ መጠን ለመቀነስ በማሰብ ነው፡፡

በምርጫ ወቅት የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶች የተለያየ መልክ ያላቸው ሲሆኑ የሳይበር ጥቃቶቹም በተለያዩ አካላት የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ የሚከተሉት መሰረታዊ ዓላማዎች ለጥቃት ፈጻሚዎች መነሻዎች ናቸው፡-
#ከምርጫ ጋር ግንኙነት ባላቸው መሠረተ-ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች የምርጫውን ምስጢራዊነት፣ ምሉዕነት እና ተደራሽነት የማሳጣት፤
#የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ምርጫውን በሚያስተዳድሩ አካላትና እና የዲሞክራሲ ተቋማት ላይ ያለን ታዓማኒነት የማሳጣት፤
#የሳይበር ጥቃት በምርጫ ባለድርሻ አካላት፣ ፓርቲዎች፣ ተወዳዳሪዎች፣ መገናኛ ብዙሃን እና የምርጫ ቅስቀሳዎች ላይ የመክፈት እና
#የምርጫ ቅስቀሳ ውድድርን በሀሰተኛ መረጃ የማዛባት ዓላማ አላቸው፡፡
በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት በምርጫ ወቅት ማናቸውም ዓይነት የሳይበር ጥቃቶች እንዳይፈጸሙና የጥቃት ሰለባ እንዳይሆኑ ዘርፉን የሚመሩ የሙያተኛ ቡድን አባላትን በማደራጀት አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ሊያደርጉና ግንዛቤ የማሳደግ ሥራዎች ሊሠሩ ይገባል፡፡ በዚህ ረገድ አስቀድሞ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መመልከትና ሀገራችን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በመቃኘት መፍትሔ ማበጀት ይጠይቃል፡፡

@berkapps @berkappsbot
አንድ ቢሊዮን የአንድሮይድ ስልኮች የመረጃ ጠለፋ ሥጋት ውስጥ ወድቀዋል፡፡

@berkapps @berkappsbot
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
አንድ ቢሊዮን የአንድሮይድ ስልኮች የመረጃ ጠለፋ ሥጋት ውስጥ ወድቀዋል፡፡

አንድ ቢሊዮን አንድሮይድ ስልኮች የደህንነት ማዘመኛቸው /security updates/ መቋረጡን ተከትሎ ለመረጃ ጥቃት መጋለጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ማዘመኛው መቆሙን ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎችን ለመረጃ ሥርቆት፣ ለራንሰም እና ማልዌር ጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ከፈረንጆቹ 2012 እና ከዚያ በፊት የወጡ የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

መረጃዎች እንደጠቆሙት ከሆነ በመላው ዓለም ከሚገኙ የአንድሮይድ ስልኮች ውስጥ 42.1 ከመቶ የሚሆኑት የአንድሮይድ እትም /version 6.0/ እና ከዚያ በታች ኦፕሬቲንግ ሲስተም /operating system/ እንደላቸው ያሳያል፡፡

የአንድሮይድ ምርቶች የደህንነት ማስጠበቂያ መረጃ መሰረት ቨርዥናቸው 7.0 በታች የሆኑና የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ የ2019 ምርቶች የደህንነት ሥጋት የለባቸውም ተብሏል፡፡

• ሞቶሮላ ኤክስ /Motorola X/
• ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤ 5/ Samsung Galaxy A5/
• ሶኒ ዝፔሪያ Z2/ Sony Xperia Z2/
• ኤል ጂ ጉግል ሌክሰስ/LG / Google Nexus 5/
• ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ /Samsung Galaxy S6/

የጸረ-ቫይረስ ኩባንያው ኤቪ ከላይ በተጠቀሱት ስልኮች ላይ ቫይረስ በመልቀቅ ባደረገው ሙከራ በአንዳንድ ስልኮች ከፍተኛ የሚባል የጥቃት ተጋላጭነት መፍጠሩን ጠቁሟል፡፡
መረጃው እንዳመለከተው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም ከሚገኙ ከአምስት አንድሮይድ ስልኮች ሁለቱ የደህንነት ማዘመኛ /security updates/ እንደማይደርሳቸውም ታውቋል፡፡

ወችዶግ /Watchdog/ ጎግልና ሌሎች ስማርት ስልኮች ለምን ያህል ጊዜ ማሻሻያቸው እንደሚቆይ ግልፀኝነት እንዲኖራቸውና ለተጠቃሚዎች ማሻሻያ በማይቀርብበት ጊዜ ሌሎች አማራጮችን እንዲያሳውቅ ተጠይቋል፡፡
የእርስዎ ስልክ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የደህንነት ሁኔታውን ለማረጋገጥ ከታች የተቀመጡትን አማራጮች ይሞክሩ፡፡

1. የእርስዎ እየተጠቀሙበት ያለው የአንድሮይድ ምርት ከሁለት ዓመት በላይ እጅዎ ላይ ከቆየ ወደ አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስሪቱ ሊዘምን እንደሚችል ያረጋግጡ፡፡ ይህንም ለማድረግ Settings የሚለውን በመክፈት > System የሚለውን በመምረጥ > Advanced System update የሚለውን በመጫን ለማዘመን ይሞክሩ።

2. ስልክዎን የተባለውን ቅደም ተከተል ተከትለው ማዘመን ካልቻሉ ስልክዎ በመረጃ ጠላፊዎች እጅ የመውደቅ እድሉ ከፍተኛ ስለሆነ እና የአንድሮይድ ስልክዎ የቨርዥን 4 እና ከዚያ በታች ከሆነ ይበልጥ ተጋላጭ ስለሚሆኑ አፕሊኬሽኖችን ከህጋዊ የአፕሊኬሽን ማውረጃው ከGoogle Play ስቶር ከማውረድ ይቆጠቡ፡፡

3. ከአጠራጣሪ አጭር የጽሁፍ መልእክት /SMS/ እና የመልቲ-ሚዲያ መልዕክቶች /MMS/ ይጠንቀቁ፡፡

4. በስልክዎ ያሉ ሚስጥራዊ እና ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን (በሃርድ ድራይቭ እና አልያም በክላውድ አገልግሎት (cloud service) ላይ መጠባበቂያ ያስቀምጡ፡፡

5. በመተግበሪያዎች በኩል የሞባይል ጸረ-ቫይረስ ይጫኑ ነገር ግን ጸረ- ቫይረሱ ለአሮጌ ስልኮች አገልግሎቱ የተገደበ አለመሆኑን ያረጋግጡ

@berkapps @berkappsbot
#ለጥንቃቄ
#አንብባችሁ #ለሌሎችም #አስተላልፉ

ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!

@berkapps @berkappsbot
ብርቅ APPS
#ለጥንቃቄ #አንብባችሁ #ለሌሎችም #አስተላልፉ ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል! @berkapps @berkappsbot
#ለጥንቃቄ
#አንብባችሁ #ለሌሎችም #አስተላልፉ

ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!

በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ
ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

< ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

< ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

< በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ!

< የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡

< በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

< አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን
በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች

#ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::

2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!!

በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ
ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ
በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም
መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ፡፡

@berkapps @berkappsbot
Share share share share
ብርቅ APPS pinned «#ለጥንቃቄ #አንብባችሁ #ለሌሎችም #አስተላልፉ ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል! በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን…»
—————————
በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ አስተማማኝ መረጃዎች
—————————
.
ትርጉም እና ቅንብር Isaac Eshetu (Talk Ethiopia)
.
.
ኮሮና እስካሁን ድረስ አገራችን ኢትዮጵያ ስለመግባቱ የተነገረ ነገር ባይኖርም ከአገራችን የሕክምና አቅም አንጻር ከፍተኛ ፈተና ሊፈጥር እንደሚችል ግልጽ ነው። አስቀድሞ መረጃ ማግኘቱ አንገብጋቢ ነው። በእንዲህ ዓይነት ወቅት ትልቅ ችግር ከሚፈጥሩት ነገሮች አንዱ ደግሞ የሐሰት ዜናዎች እና መረጃዎች ናቸው። በበሽታው አጭር ዕድሜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ የተሳሳቱ አመለካከቶች ተረጭተዋል። የሰዉን ጭንቀት እንዴት ወደብር መቀየር እንደሚችሉ ጠንቅቀው የሚያውቁ የስፓም ፈልፋዮችም ሥራ ፈትተው አልተቀመጡም።
.
ጥንቃቄ ያሻናል። በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ምንጮቻቸው ያልታወቁ እና ጊዜያዊ ጭንቀታችንን የሚያስታግሡ ነገሮችን ሼር ማድረግ አደጋ አለው። ያልተጣራ መረጃ ብዙ ጉዳት ያደርሳል። ለማስታወቂያ ገንዘብ በሚል እውነት የሚመስል ሐሰት ፈጥረው እየጻፉ ገንዘብ የሚያጋብሱ ብዙ ስፓመር ዌብሳይቶች አሉ። በእንግሊዝኛ የተጻፈ ነገር ሁሉ አስተማማኝ አይደለም።
.
በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አንዳንድ ሼር የተደረጉ የተሳሳቱ የአማርኛ ጽሑፎች አይቼ ተረብሼ ነበር ጠዋት። ትላልቅ የሚባሉ ገጾች እንኳ ሳያጣሩ የማስፋፋት ነገር ይታይባቸዋል። እናም ሰሞኑን ካነበብኳቸው እና ካየኋቸው አስተማማኝ ምንጮች የተረጋገጠ መረጃ መሰብሰብ እና መተርጎሙ የተሻለ መስሎ ስለታየኝ ከሁለት ምንጮች የወሰድኳቸውን መረጃዎች በጽሑፍ አቀናብሬ መጥቻለሁ።
.
ዋነኛ ምንጭ ያደረግኩት የዓለም ጤና ድርጅት (@World Health Organization) በጤና ባለሙያዎቹ ያዘጋጃቸውን አጫጭር ቪዲዮዎች ሲሆን በሁለተኛ ምንጭነት ደግሞ Science Insider የተሰኘው ዕውቅ ሚዲያ ሁለት የበሽታ ቁጥጥር ዘርፍ ኤክስፐርቶችን በመበጋዝ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማረም ያዘጋጀው ቪዲዮ ነው። የባለሙያዎቹን ማንነት በየመግቢያው ላይ፣ የቪዲዮዎቹን ሊንክ ደግሞ በየመጨረሻው ላይ አስቀምጣለሁ። ድጋሚ የማንበብ አጋጣሚ የማያገኝ ሰው ሊኖር ስለሚችል ጽሑፉን በተለያየ ክፍል ከማድረግ ይልቅ ቢረዝምም በአንድ ጽሑፍ ማድረግ መርጫለሁ። በዚህ አጋጣሚ በበሽታው ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩ የሚቀያየሩ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እና ሁሌም አፕዴትድ መረጃ ለማግኘት መጣር እንዳለብን ለማስታወስ እወዳለሁ።
.
ከሁለቱ አስተማማኝ ምንጮች ወዳገኘሁት መረጃ ከመግባቴ በፊት ግን ከሌሎች በርካታ ምንጮች ካነበብኩት በመነሣት የተወሰኑ እርማቶችን ልጠቁም፦
.
———
እርማት 1
———
.
ኮሮና የቫይረስ ዓይነት ነው። ቫይረሶች እንደባክቴሪያ በአንቲባዮቲክ ስለማይጠፉ በአብዛኛው የማገገም ትሪትመንት ነው የሚደረግላቸው። ይህም ሰውነታችን ራሱ የበሽታ መከላከያ ሥርዓቱን (Immune System) ተጠቅሞ በሽታውን እስኪያሸንፈው እገዛ በማድረግ ነው። ሙቅ ነገሮችን በመብላት እና በመጠጣት፣ አልያም ፀሐይ በመሞቅ ከኮሮና መፈወስ እንደሚቻል የሚገልጹ መረጃዎች ፍጹም ሐሰት ናቸው። ይህን ዓይነት የተሳሳቱ መረጃዎች በቀጥታ ጉዳት ባያደርሱም ታማሚውን አጓጉል ተስፋ በመስጠት ወደሕክምና እንዳይሄድ፣ ሌሎች አስተማማኝ መንገዶችንም እንዳይጠቀም ያሳንፋሉ።
.
———
እርማት 2
———
.
ኮሮና ቫይረስ ከሰው አካል ውጭ ምን ያክል ረጅም ጊዜ መቆየት እንደሚችል የተረጋገጠ ነገር የለም። በጥቅሉ ረጅም ጊዜ ከሰው አካል ውጭ መቆየት ባይችልም «ከ8 ደቂቃ በኋላ፤ ከ1 ሰዓት በኋላ ይጠፋል» ወዘተ ዓይነት መረጃ የሚሰጡ ጽሑፎችን መጠንቀቅ ያሻል።
.
———
እርማት 3
———
.
ኮሮና ቫይረስ የያዘው ሰው «የአፍንጫ እርጥበት (ንፍጥ) የለውም» የሚሉ መረጃዎች የተሳሳቱ እና የዓለም ጤና ድርጅት የበሽታው ምልክቶች ብሎ ካስቀመጣቸው እውነታዎች የሚቃረኑ ናቸው።
.
በጥቅሉ እኒህን ካየን አሁን ወደሁለቱ የመረጃ ምንጮች በመመለስ የተወሰኑ ነጥቦችን እንይ፦
.
.
—————————
🔵 በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች በጥያቄ እና መልስ
—————————
.
ይህ ክፍል የተዘጋጀው በልቅ ትርጉም ዘይቤ ሲሆን የግድ አስፈላጊ የማይባሉ ጥያቄ እና መልሶች እንዲዘለሉ ተደርገዋል። (ሙሉውን በሊንኩ ማግኘት ይችላል።) በቅንፍ የተቀመጡት ማብራሪያዎች የእኔ ሲሆኑ ቀሪው በሙሉ ትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ባይቀመጥም የባለሙያዎቹ ነው።
.
መልስ አቅራቢዎቹ ዶ/ር ሲራ ማዳድ - የኒውዮርክ ከተማ የጤና እና የሆስፒታሎች ጠቅላላ ሥርዓት ልዩ የፓቶጅን ፕሮግራም ኤክስፐርት/ዳይሬክተር (NYC Health + Hospitals System-wide Special Pathogens Program) እና ፕ/ር ስቴፈን ሞርስ - የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የበሽታ ምንጭ እና መስፋፋት ጥናት ፕሮፌሰር (Professor of Epidemiology at Columbia University) ናቸው።
.
———
ጥያቄ — በኮሮና በሽታ የተያዘ ሰው ሁሉ ይሞታልን?
———
.
🗨 ዶ/ር ሲራ ማዳድ፦ ስለኮሮና ገና ብዙ የማናውቀው ነገር ቢኖርም እስካሁን ያሉት ጥናቶች የሚጠቁሙት በአደጋነት መለስተኛ ከሚባሉት ቫይረሶች የሚመደብ መሆኑን ነው። ወደሞት የማድረስ ዕድሉ 2 በመቶ ነው። (በሽታው ከሚይዛቸው ሰዎች ወደሞት የሚደርሱት 2 በመቶው ብቻ ናቸው [ከመቶ ታማሚ 2 ሰው]) በበሽታው ከሚያዙት ውስጥ ከ18 እስከ 20 በመቶው አሥጊ ደረጃ (critical condition) ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።
.
🗨 ፕ/ር ስቴፈን ሞርስ፦ የሚሞቱት 2 በመቶውም ቢሆን ሆስፒታል ኦልሬዲ የገቡት ስለሆኑ ታመው ሆስፒታል ከገቡት ሰዎች 98 በመቶው የመዳን ዕድል አላቸው ማለት ነው። ስለዚህ በኮሮና መያዝ የሞት ፍርድ አይደለም።
.
———
ጥያቄ፦ ኮሮና የሚይዘው ቻይናዎችን ብቻ ነውን?
———
.
🗨 ፕ/ር ስቴፈን ሞርስ፦ አይደለም። በሽታው ቻይና ቢጀምርም የሁላችንም ሆኗል።
.
🗨 ዶ/ር ሲራ ማዳድ፦ ተላላፊ በሽታዎች ድንበር አያከብሩም። ሁላችንም የመታመም ዕድል አለን።
.
———
ጥያቄ:‐ የአፍ መሸፈኛ ማስክ መልበስ ከበሽታው ይጠብቃል?
———
.
🗨 ፕ/ር ስቴፈን ሞርስ፦ ብዙ ሰዎች እንዲያ ይመስላቸዋል። እርግጥ ማስክ ሲለበስ የደኅንነት ስሜት እንዲሰማን ያደርግ ይሆናል። ብዙው መሸፈኛ የሚለብሰው ሰው በትክክል እንኳ አይጠቀምበትም። ዓይነቱንም ያለማወቅ ችግር አለ።
.
🗨 ዶ/ር ሲራ ማዳድ፦ ሁለት ዓይነት መሸፈኛ ነው ያለው። ብዙው ሰው ለብሶት የሚታየው ቀለል ያለው የሕክምና አፍ መሸፈኛ አለ። ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ N-95 የሚባለው የሕክምና ባለሙያዎች የሚለብሱት መተንፈሻ መሣሪያ ያለው ማስክ ነው። አየር ወለድ የሆኑ ተህዋሶችን 95 በመቶ አጥልሎ ያስቀራል። እሱንም ቢሆን ምንም አየር እንዳያስገባ ከፊታቸው ቅርጽ ጋር ሙሉ ለሙሉ መግጠሙ ተረጋግጦ ተሞክሮ ነው የሚለብሱት።
.
🗨 ፕ/ር ስቴፈን ሞርስ፦ N-95 መሸፈኛ መልበስ በጣም ምቾት የሚነሣ እና ለመተንፈስም የሚያስቸግር የመሸፈኛ ዓይነት ነው።
.
🗨 ዶ/ር ሲራ ማዳድ፦ ደግሞም ማስክ የሚለበሰው በበሽታው ለታመሙ ሰዎች (እና ለአስታማሚዎች) እንጂ ገና ላልታመሙ ሰዎች አይደለም። ኮሮናን ለመከላከል ቁልፉ ነገር ለ20 ሰከንድ እጅን በደንብ (በሣሙና) አዘውትሮ መታጠብ ነው። ኦልሬዲ ለታመመ እና ቤቱ ተገልሎ ለተቀመጠ ሰው ግን ሌሎች ተጨማሪ ተግባራት ያስፈልጋሉ።
.
———
ጥያቄ፦ የጉዞ ክልከላ ማድ
ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገብቷል!

"ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፤ በተደረገው ምርመራ አንድ ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች አንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።" ኢ/ር ታከለ ኡማ

@berkapps @berkappsbot
ቀጥታ!

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር [COVID-19] በተመለከተ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።
ቫይረሱ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው 25 ሰዎች በለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጓል። የመለየት ስራው ቀጥሏል

@berkapps @berkappsbot
ሶስት ነገሮች

1) በሽታው ከ134 በላይ ሀገራት ላይ የተከሰተ ነው፡፡እኛ ጋ ብቻ የተፈጠረ ይመስል አንዋከብ፡፡ተረጋግተን የምንታዘዘውን ብቻ እንፈጽም!

2) የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህም የበለጡ ብዙ ወረርሽኞችን አይቷል፡፡በአንድነት ከቆምን እንችለዋለን፡፡

3) አላስፈላጊ ቅብጥርጥር በማውራት ቤተሰቦቻችንን እና የመረጃ አክሰስ የሌላቸውን ሰዎች አናውክ፡፡

@berkapps @berkappsbot
በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተገኘው የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ተጨማሪ መረጃዎች እነሆ፦

- ትላንት Positive ሆኖ የተገኘው ጃፓናዊው ግለሰብ የመጀመሪያው የጉዞ ታሪክ የሚያሳየው ከጃፓን እንደተነሳ ነው።

- FEBRUARY 23 ቡርኪነፋሶ ገብቷል። MARCH 4 ደግሞ አዲስ አበባ ገብቷል።

- አዲስ አበባ ከገባ በኃላ በMARCH 9 ማለትም ከ5 ቀን በኃላ ምልክት ማሳየት ስለጀመረ ጤና ተቋም ይሄዳል፤ በዚህም ወቅት ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥቆማ ይደርሰዋል።

- የፈጣንሽ ምላሽ የሚሰጠው ግብረ ኃይል ለጃፓናዊው የሚያስፈልገውን ምርመራና ክትትል ካደረገ በኃላ በለይቶ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል።

- በትላንትናው ዕለት እዛው የለይቶ ማቆያ ጣቢያ እያለ ናሙናው ተሰርቶ ቫይረሱ እንዳለበት ተረጋግጧል።

@berkapps @berkappsbot
ኮሮና ቫይረስ አዲስ የመረጃ ማጭበርበሪያ ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል

@berkapps @berkappsbot
ብርቅ APPS
ኮሮና ቫይረስ አዲስ የመረጃ ማጭበርበሪያ ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል @berkapps @berkappsbot
ኮሮና ቫይረስ አዲስ የመረጃ ማጭበርበሪያ ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል

ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተገናኘ በኢ-ሜይል የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች በዚህ አመት ከታዩት የመረጃ ማጭበርበሪያዎች እጅግ የከፋ ሆኖ መገኘቱን የደህንነት ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

ኮሮና ቫይረስን እንደ ማጭበርበሪያ እየተጠቀሙበት ያሉ የሳይበር ወንጀለኞች ግለሰቦችን ጨምሮ ኢንዱስትሪዎችን ፣የኤሮስፔስ ኩባንያዎችን ፣ የትራንስፖርት ተቋማትን ፣ ፋብሪካዎችን ፣ የእንግዳ ማረፊያዎችን ፣ የጤና ተቋማትን እና የመድን ድርጅቶችን ኢላማ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

እነዚህ የማጥመጃ ኢ-ሜይሎቹ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች የሚላኩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ እንግሊዝኛ ፣ ፈረንሳይኛ ፣ ጣልያንኛ ፣ ጃፓንኛ እና ቱርክኛ ቋንቋ የተጻፉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

የሳይበር ደህንነት ኩባንያው ፕሩፍፖይንት /Proofpoint/ ተመራማሪዎች በፈረንጆቹ በፌብሩዋሪ 2020 ለደንበኞች አንድ ያልተለመደ ኢ-ሜይል ሲላክ ለመጀመሪያ ጊዜ መመልከታቸው ታውቋል፡፡

አንዳንድ መልእክቶች በቻይና እና በእንግሊዝ መንግስታት ወጪ ስለተሸፈነው ክትባት ዝርዝር በዚህ ሰነድ ውስጥ አለ መልእክቱም "ከታምረኛው ዶክተር" የተላከ ነው የሚል ይገኝበታል፡፡

ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን አያያዥ /link/ በሚጫኑበት ወቅት የመግቢያ ዝርዝሮችን ለመሰብሰብ ታስቦ ወደተፈበረከው ማጥመጃ ድረ-ገጽ እንደሚወስዳቸው "ፕሩፍፖይንት" ጠቁሟል፡፡
ተቋሙ ባደረገው ዳሰሳ ወንጀለኞቹ ለማጥመጃ የሚውሉ በአንድ ጊዜ እስከ 200,000 የሚደርሱ ኢ-ሜሎች እየላኩ መሆኑ ገልጿል፡፡

የማይምካስት /Mimecast/ ወንጀል ሃላፊ የሆኑት ካርል ወርን ተጠቃሚዎች “በኢ-ሜይል አማካኝነት ከሚላኩ ከማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት ያላቸውን መልእክቶች ምላሽ አይስጡ” ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ከኢ-ሜሎች ጋር የተገናኙ መልእክት ላይ ያሉ አገናኝን ለመጫን እንዳይሞክሩ ተመክሯል፡፡

አንዳንድ አጭበርባሪዎች የዓለም ጤና ድርጅትን የሚወክሉ በማስመሰል ተጠቃሚዎችን እያጨበረበሩ ሲሆን "ይህ ሰነድ የበሽታውን ስርጭት እንዴት መከላከል እንደሚችሉ በዝርዝር ይገልጻል" የሚሉ ማጭበርበሪያዎችን ጭምር ይጠቀማሉ ተብሏል፡፡

ነገር ግን ስለ ኮሮና ቫይረስ አባሪው ምንም ዓይነት ጠቃሚ ምክር እንዳልያዘ እና ይልቁንስ ኤጀንት ቴስላ ኪይሎገር /AgentTesla Keylogger/ በተባለው አጥፊ ሶፍትዌር ኮምፒውተራችንን ለጥቃት ተጋላጭ እንደሚደርገው ታውቋል፡፡

አጥፊ ሶፍትዌሩም በኮምፒውተር ቁልፍዎ የሚተይቡትን እያንዳንዱን ፊደል እየተከታተለ እንደሚመዘግብ ነው የታወቀው፡፡

በቢቢሲ በአምስት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ በተሰማሩ ገጾች ላይ ባደረገው ዳሰሳም ጉዳዩ እውነት ሆኖ እንዳገኘው አስፍሯል፡፡

ምንጭ ቢቢሲ
@berkapps @berkappsbot
እስካዛሬዋ እለት በአለም ላይ 138,432 ህዝብ በበሽታው ተይዟል፡፡ከዚህ ውስጥ የሞተው 5,082 ሰው ብቻ ነው፡፡ይህም ከ4% በታች ነው፡፡ድኖ የወጣው ሰው ቁጥር ደግሞ 51% ገደማ ነው፡፡ስለዚህ አይደለም የተጠረጠረ የታመመ ሁሉ አይሞትም፡፡
አሁንም በድጋሚ ለመናገር ያህል

"እ ን ረ ጋ ጋ!"

@berkapps @berkappsbot
No need to panic and cause others to behave uncontrollable ድንጋጤ እና እጅግ የተጋነነ ፍርሐት የበለጠ ጉዳት ውስጥ ይከታል።

ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የተጋነነ ፍርሀት የጉንፋን ምልክት ያለባቸው ሰዎች ላይ እንግልት ፤ ወይም ደግሞ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ሊያደርግ ይችላል።

በመረጃ ላይ የተመሠረተ ጥንቃቄ አድርጉ። ቤተሰቦቻችሁ ምን ማድረግ እንዳለባቸው በመረጃ ላይ ተመስርታችሁ ምከሩ።

@berkapps @berkappsbot
ብርቅ APPS pinned Deleted message
በዚህ ሁሉ ፍርሃት፣ ሰቀቀን፣ ጭንቀት፣ ህመም እና ሞት ውስጥ ኮሮና ቫይረስ ያመጣው አንድ ጥቅም ተገኝቷል!

ምን መሰለህ?

አውሮፓ፣ ኤሽያ እና አሜሪካ የሰዎች እንቅስቃሴ እጅጉን ተገድቧል! ከምግብ አቅራቢ እና ጤና ተቋሟት ውጪ ትምህርት ቤቶች፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ ስራ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ተገድበዋል!

ይህ ሁሉ ምስቅልቅል ግን ለዓለም አንድ ጥቅም አስገኝቷል!

በበካይ ጋሶች ልቀት ምክንያት የሚፈጠረው የአየር ብክለት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ቀንሷል!

የአውሮፕላኖች በረራ በፊት ከነበረበት ከእጥፍ በላይ ቀንሷል፣ በካይ ፋብሪካዎች ስራ አቁመዋል፣ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል! በዚህ ምክንያት ወደ አየር የሚለቀቀው "Nirogen Dioxide" በጣም ቀንሷል! በአውሮፓ በተለይም በጣልያን የሚገኙ ወንዞች ከመዝናኛ እና ንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ አረፍ በማለታቸው ምክንያት ከ 100 አመት በፊት ወደነበራቸው ጥራት ተመልሰዋል። ንፁህ አየር ማየት ተችሏል!

በተለይ የቻይና አየር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተሻሽሏል። ከብዙ አመታት በኃላ ንፁህ ውሃ፣ ንፁህ አየር እና ንፁህ ሰማይ ሰዎች ማየት ችለዋል! ይህንን ደግሞ ያረጋገጠጡት የ "NASA pollution monitoring satellite" እና የ "European Space Agency" ናቸው!

የዓለማችን አንደኛ በካይ ወይም ካርቦን ለቃቂ (Carbon Emitter) የሆነችው ቻይና የካርቦን ልቀቷ በቫይረሱ ምክንያት በ 25% ቀንሷል! "ኦዞን" አረፍ ብሏል! በቻይናዋ "ውሃን ግዛት" ከሳተላይት የተገኘ ምስል የሚያሳየው ልዩነት አስደናቂ ነው! ቫይረሱ ከመከሰቱ በፊት እና በኃላ የተገኘውን የሳተላይት ምስል ከታች ተመልከቱ!

በከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ የሚታወቁት እነ "New York" እና "Seattle" የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በመቀነሱ ሳብያ የካርቦን ልቀታቸው ወደ 28 % ቀንሷል!

በተቃራኒው አሳሳቢ የሆነው የሰዎች ቅጥ ያጣ ስግብግብነት ነው! አውሮፓ፣ አሜሪካ እና አውስትራሊያ የሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች ባዶ እየሆኑ ነው! ሰው ረጃጅም ሰልፎችን እየተሰለፈ ምግብ፣ ሶፍት፣ ሳኒታይዘር እና የፊት ማስኮችን ለአመት እያቀደ እየሸመተ ነው! ብዙ ሱፐር ማርኬቶች ድብድቦችን እያስተናገዱ ነው! ሰው እየተባላ ነው! በተለይ በሶፍት እና በሳሙና ምክንያት!

አንድ ነገር ብዬ ልውጣ! ይህንን ባልልህ ደስ ይለኝ ነበር! ነገር ግን ሐገራችን ላይ በቅርቡ የከፋ ነገር ይፈጠራል! ዛሬ ላይ ያለው የተጠቂዎች ቁጥር በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በብዙ ቁጥር ይጨምራል! ስራ ይዘጋል፣ የንግድ ተቋማት ይዘጋሉ፣ ሰዎች ከቤት መውጣት ይከለከላሉ፣ብዙ ሞቶችን እናስተናግዳለን፣ ብዙ ዘግናኝ ነገሮችን እንሰማለን!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት "ቫይረሱ ጉንፋን" ነው! የሚካበደውን ያህል አይደለም! እንቆጣጠረዋለን!" ምናምን ብለው አቅለውት ነበር! ትላንት በሰጡት መግለጫ ላይ ግን በጣም ተደናግጠዋል! ማቅለላቸው ልክ እንዳልነበር አምነዋል! ከጤና ባለሙያዎቻቸው ያገኙት መረጃ ደግሞ ይበልጥ አስደንግጧቸዋል! "....በጣም ፈጠነ ከተባለ ክትባት ወይም መድሃኒቱን ማግኘት የምንችለው በመጪው ሐምሌ ወይም ነሃሴ ወር ላይ ነው!..." ተብለዋል! የሟቾች ቁጥር በአሜሪካ አሻቅቧል! በየቀኑ አዳዲስ ኬዞች በእጥፍ እየጨመሩ ነው! አውሮፓ ክፉኛ ሾቃለች! ዱቄት ሆናለች! አብዛኛዎቹ ሐገራት ድንበሮቻቸውን እየዘጉ ነው! ከቤት መውጣትን እያገዱ ነው!

በተቃራኒው አፍሪካ እየሳቀች ነው! ህዝቦቿ እየቀለዱ ነው! "ብረት ድስት" ፣ "ፌስታል" እና "ጫማ" አፋቸው ላይ እንደ "ፌስ ማስክ" እያደረጉ ፎቶ እየተነሱ ነው! "Meme" እየሰሩ እየፎገሩ ነው! አስቂኝ አስቂኝ መከላከያ መንገዶችን እየሞከሩ ነው! የሆነ ተዓምር ካልተፈጠረ ከጥቂት ሳምንታት በኃላ ግን ነገሮች የተገላቢጦሽ ይሆናሉ!

ለማንኛውም በተቻላችሁ መጠን እራሳችሁን ጠብቁ፣ እጃችሁን ታጠቡ፣ ከሰዎች ጋር ንክኪ አቁሙ፣ ያድናል ወይም ይከላከላል የተባላችሁትን ሁሉ አትሞክሩ! ሁሉም በየእምነቱ ፀሎት ያድርግ! ወደ አምላካችሁ ፊታችሁን አዙሩ!

ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ!😀

@berkapps @berkappsbot
HTML Embed Code:
2024/05/22 01:05:14
Back to Top