TG Telegram Group & Channel
ብርቅ APPS | United States America (US)
Create: Update:

በዚህ ሁሉ ፍርሃት፣ ሰቀቀን፣ ጭንቀት፣ ህመም እና ሞት ውስጥ ኮሮና ቫይረስ ያመጣው አንድ ጥቅም ተገኝቷል!

ምን መሰለህ?

አውሮፓ፣ ኤሽያ እና አሜሪካ የሰዎች እንቅስቃሴ እጅጉን ተገድቧል! ከምግብ አቅራቢ እና ጤና ተቋሟት ውጪ ትምህርት ቤቶች፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ ስራ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ተገድበዋል!

ይህ ሁሉ ምስቅልቅል ግን ለዓለም አንድ ጥቅም አስገኝቷል!

በበካይ ጋሶች ልቀት ምክንያት የሚፈጠረው የአየር ብክለት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ቀንሷል!

የአውሮፕላኖች በረራ በፊት ከነበረበት ከእጥፍ በላይ ቀንሷል፣ በካይ ፋብሪካዎች ስራ አቁመዋል፣ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል! በዚህ ምክንያት ወደ አየር የሚለቀቀው "Nirogen Dioxide" በጣም ቀንሷል! በአውሮፓ በተለይም በጣልያን የሚገኙ ወንዞች ከመዝናኛ እና ንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ አረፍ በማለታቸው ምክንያት ከ 100 አመት በፊት ወደነበራቸው ጥራት ተመልሰዋል። ንፁህ አየር ማየት ተችሏል!

በተለይ የቻይና አየር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተሻሽሏል። ከብዙ አመታት በኃላ ንፁህ ውሃ፣ ንፁህ አየር እና ንፁህ ሰማይ ሰዎች ማየት ችለዋል! ይህንን ደግሞ ያረጋገጠጡት የ "NASA pollution monitoring satellite" እና የ "European Space Agency" ናቸው!

የዓለማችን አንደኛ በካይ ወይም ካርቦን ለቃቂ (Carbon Emitter) የሆነችው ቻይና የካርቦን ልቀቷ በቫይረሱ ምክንያት በ 25% ቀንሷል! "ኦዞን" አረፍ ብሏል! በቻይናዋ "ውሃን ግዛት" ከሳተላይት የተገኘ ምስል የሚያሳየው ልዩነት አስደናቂ ነው! ቫይረሱ ከመከሰቱ በፊት እና በኃላ የተገኘውን የሳተላይት ምስል ከታች ተመልከቱ!

በከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ የሚታወቁት እነ "New York" እና "Seattle" የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በመቀነሱ ሳብያ የካርቦን ልቀታቸው ወደ 28 % ቀንሷል!

በተቃራኒው አሳሳቢ የሆነው የሰዎች ቅጥ ያጣ ስግብግብነት ነው! አውሮፓ፣ አሜሪካ እና አውስትራሊያ የሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች ባዶ እየሆኑ ነው! ሰው ረጃጅም ሰልፎችን እየተሰለፈ ምግብ፣ ሶፍት፣ ሳኒታይዘር እና የፊት ማስኮችን ለአመት እያቀደ እየሸመተ ነው! ብዙ ሱፐር ማርኬቶች ድብድቦችን እያስተናገዱ ነው! ሰው እየተባላ ነው! በተለይ በሶፍት እና በሳሙና ምክንያት!

አንድ ነገር ብዬ ልውጣ! ይህንን ባልልህ ደስ ይለኝ ነበር! ነገር ግን ሐገራችን ላይ በቅርቡ የከፋ ነገር ይፈጠራል! ዛሬ ላይ ያለው የተጠቂዎች ቁጥር በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በብዙ ቁጥር ይጨምራል! ስራ ይዘጋል፣ የንግድ ተቋማት ይዘጋሉ፣ ሰዎች ከቤት መውጣት ይከለከላሉ፣ብዙ ሞቶችን እናስተናግዳለን፣ ብዙ ዘግናኝ ነገሮችን እንሰማለን!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት "ቫይረሱ ጉንፋን" ነው! የሚካበደውን ያህል አይደለም! እንቆጣጠረዋለን!" ምናምን ብለው አቅለውት ነበር! ትላንት በሰጡት መግለጫ ላይ ግን በጣም ተደናግጠዋል! ማቅለላቸው ልክ እንዳልነበር አምነዋል! ከጤና ባለሙያዎቻቸው ያገኙት መረጃ ደግሞ ይበልጥ አስደንግጧቸዋል! "....በጣም ፈጠነ ከተባለ ክትባት ወይም መድሃኒቱን ማግኘት የምንችለው በመጪው ሐምሌ ወይም ነሃሴ ወር ላይ ነው!..." ተብለዋል! የሟቾች ቁጥር በአሜሪካ አሻቅቧል! በየቀኑ አዳዲስ ኬዞች በእጥፍ እየጨመሩ ነው! አውሮፓ ክፉኛ ሾቃለች! ዱቄት ሆናለች! አብዛኛዎቹ ሐገራት ድንበሮቻቸውን እየዘጉ ነው! ከቤት መውጣትን እያገዱ ነው!

በተቃራኒው አፍሪካ እየሳቀች ነው! ህዝቦቿ እየቀለዱ ነው! "ብረት ድስት" ፣ "ፌስታል" እና "ጫማ" አፋቸው ላይ እንደ "ፌስ ማስክ" እያደረጉ ፎቶ እየተነሱ ነው! "Meme" እየሰሩ እየፎገሩ ነው! አስቂኝ አስቂኝ መከላከያ መንገዶችን እየሞከሩ ነው! የሆነ ተዓምር ካልተፈጠረ ከጥቂት ሳምንታት በኃላ ግን ነገሮች የተገላቢጦሽ ይሆናሉ!

ለማንኛውም በተቻላችሁ መጠን እራሳችሁን ጠብቁ፣ እጃችሁን ታጠቡ፣ ከሰዎች ጋር ንክኪ አቁሙ፣ ያድናል ወይም ይከላከላል የተባላችሁትን ሁሉ አትሞክሩ! ሁሉም በየእምነቱ ፀሎት ያድርግ! ወደ አምላካችሁ ፊታችሁን አዙሩ!

ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ!😀

@berkapps @berkappsbot

>>Click here to continue<<

ብርቅ APPS

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)