TG Telegram Group & Channel
ብርቅ APPS | United States America (US)
Create: Update:

"Google"ልን እራሱ "Google" ለምን አታደርግም አባዬ?

እሺ እሱን ተወው እና ለመጀመርያ ግዜ ኢንተርኔት አግኝተህ "Google" ላይ "Search" ያደረከው ነገር ምንድነው?
.
.
.

ለማንኛውም ስለ "Google" እና "Google" ኩባንያ የገረሙኝን እና ብታውቃቸው ይጠቅሙሃል ብዬ ያሰብኳቸውን ነገሮች እንደሚከተለው ቀድጄልሃለሁ!😃

የአሜሪካዋ የቴክኖሎጂ መናገሻ በምትባለው "San Francisco" "Silicon Valley" ውስጥ የሚገኘው "Google" ኩባንያን ለየት የሚያደርገው የቢሮው ሁኔታ እና የሰራተኞቹ የአሰራር መንገድ ነው።

ተቀጣሪዎች "....በዚህ ሰዓት ውጣ፣ በዚህ ሰዓት ግባ ፣ ከዚህ እስከ እዚህ ሰዓት ስራ፣ ፊርማ ፈርም፣ እዚህ ተቀመጥ ፣ ይሄንን አትጠይቅ፣ ይሄንን አትንካ፣ ይሄንን ብቻ ስራ!...." ምናምን መባል የለባቸውም! እንደዚህ አይነት ኃላ ቀር አሰራሮች ለብዙ አመታት ውጤት አላመጡም!፣ ፈጠራን አላበረታቱም!፣ ሰራተኛውንም አሰሪውንም አልጠቀሙም!" ብሎ የሚያምነው የ "Google" ኩባንያ የራሴ አሰራር፣ የራሴ የስራ ፍልስፍና አለኝ ይላል! በዚህም ፍልስፍና እጅግ ውጤታማ ሆኗል!

የመጀመርያው ድርጅቱን ከስራ ቦታ ይልቅ ሁሉም ነገር የተሟላለት መኖርያ ቤት የሚመስልበትን መንገድ ፈጠሩ። የተለመደውን የቢሮ ቅርፅ አስወገዱ! ድርጅቱ ውስጥ የአለቃ እና የሰራተኛ ወንበር የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ቢሮ ክፍት ነው። ሁሉም የፈለገበት ቦታ ላይ ተቀምጦ መስራት ይችላል! የግል ንብረት፣ የግል ኮምፒውተር፣ የግል ወንበር ምናምን የለም! ማንም የምንም ነገር ባለቤት አይደለም! ሁሉም ነገር የሁሉም ንብረት ነው።

የሰራተኞቹን የፈጠራ ብቃት ለመጨመር እና አዕምሯቸው የተፍታታ እንዲሆን በማሰብ የሚዝናኑባቸው እንደ ፑል፣ ቴኒስ፣ ጆተኒ፣ ጎልፍ፣ ዲጅታል ጌም መጫወቻዎች፣ መዋኛ ገንዳዎች እና የሙዚቃ መሳርያዎች በየቦታው አሉ። አንድ ሰራተኛ በፈለገበት ሰዓት መጫወት እና መዝናናት ይችላል።

ስራህን ስትሰራ የተሻለ ስሜት እንዲሰማህ ውሻህ ወይም ድመትህን ጭምር ይዘህ መሄድ ትችላለህ። ድርጅቱ ገደብ (Limitation) የሰዎችን የመፍጠር "tendency" ይቀንሳል! ብሎ ያምናል።

ውስጡ 25 ትልልቅ ካፍቴርያዎች እና ሬስቶራንቶች ያሉት "Google" ሰራተኞቹ በፈለጉት አጋጣሚ ያሻቸው ምግብ እንዲቀርብላቸው ያደርጋል። አንድ ሰራተኛ ከ 200 ጫማ (60 ሜትር) በላይ ከምግብ መራቅ የለበትም በሚል ፍልስፍናም ድርጅቱ ያምናል! "የራበው አይሰራም! ሁሉም ነገር የቀረበለት ሰራተኛ ደግሞ ትኩረቱን ወደ ስራ እና ስራ ብቻ ማድረግ ይችላል!" በሚል አመለካከት ያምናሉ።

ሰራተኞቹ አዓምሯቸው ከተወጣጠረ እራሳቸውን ለማፍታታት በቢሮ ውስጥ ማሳጅ የሚደረጉባቸው ክፍሎች እና የሰለጠኑ እና ፍቃድ ያላቸው የማሳጅ ቴራፒስቶች ዝግጁ ሆነው ይጠብቋቸዋል!

ለአካባቢያዊ አየር ጥበቃ ካላቸው ትኩረት የተነሳ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞቹ ከስራ ቦታ ወደ ቤት/ከቤት ወደ ስራ ቦታ የሚመላለሱት የልቀቅ መጠናቸው እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆኑ ባሶች ነው። እያንዳንዱ ሰራተኛ የራሱን መኪና እየነዳ ቢመላለስ በአመት ሊለቀቅ የሚችለውን ከ 20 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ልቀት መቀነስ ተችሏል። ግቢ ውስጥ ሰራተኞች የሚንቀሳቀሱት በሳይክል ነው! ይህም ልቀትን ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል!

በቅጥር ግቢው የሚበቅለውን ሳር/አረም ለማስወገድ "Google" ማሽኖችን" ሳይሆን "ፍየሎችን" ነው የሚጠቀመው! በየግዜው ፍየሎችን እየተከራየ በግቢው ውስጥ የሚበቅለውን ሳር/አረም እንዲግጡለት ያደርጋል! አንድ ሰራተኛ እየሰራ በአጠገቡ ፍየል ሲያልፍ አይደንቀውም!😃 ሰራተኞቹ እንደውም እነዚህን ፍየሎች ማየታችን የፈጠራ አቅማችንን ጨምሮልናል ይላሉ።

"Google" ዋናው ኩባንያ አጠገብ ለምትገኘው "Mountain View" ለምትባል አነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ በነፃ ዋይ ፋይ እንዲያገኙ እና ኢንተርኔትን ያለምንም ገደብ እንዲጠቀሙ አድርጓል።

በድርጅቱ የተቀጠረ ሰራተኛ ህይወቱ ቢያልፍ ሚስት ወይም ባል የሟች 50% ደሞዝን ለ 10 ዓመታት እንዲከፈላት/እንዲከፈለው ይደረጋል።

በአጠቃላይ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኞች ላፕቶፓቸውን ይዘው ሸርተቴ እና ዥዋዥዌ ሲጫወቱ ማየት ብርቅ አይደለም አባዬ!😃

"Larry page" እና "Sergey Brin" በተባሉ በ "Stanford University" የ "PHD" ተማሪዎች የተመሰረተው "Google" ኩባንያ አሁን ላይ ከ 500 ቢልዮን ዶላር በላይ "worth" የሚያደርግ ሲሆን የዓለማችን "Most Visited website" ነው። የዛሬ 22 ዓመት ሲመሰረት የመጀመርያ ቢሮው የክራይ ጋራዥ ውስጥ ነበር። በወቅቱ በተከራዩት ገራዥ ውስጥ 16 ሰራተኞች ብቻ ነበራቸው! አሁን ላይ በዓለም የተለያዩ 50 ሃገራት 70 ግዙፍ ቢሮዎች እና በ ብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞች አሉት።

የመጨረሻ!

"Google" በመጀመርያ ስፔሊንጉ "Googol" የነበረ ሲሆን መስራቾቹ የድርጅቱን "Domain" ለማስመዝገብ ሲሄዱ በተፈጠረ የስፔሊንግ ስህተት ነው "Google" ተብሎ የቀረው። በነገራችን ላይ በአማካይ በቀን "1 ቢልዮን" ነገሮች "Google" ላይ "Search" ይደረጋሉ።

ደህና እደሩ!

አባዬ! ደግሞ ቢሮ ሄደህ "ለምን ግን የኛ ቢሮ እንደ "Google" አይሆንም?!" ብለህ ጠይቅ አሉህ!😃

I take no responsibility!😜

@berkapps @berkappsbot

ብርቅ APPS
Photo

>>Click here to continue<<

ብርቅ APPS

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)