TG Telegram Group & Channel
አዲስ ጥበብ/ Addis Tibeb | United States America (US)
Create: Update:

ኤልያስ መልካ "ወርቃማው" የሙዚቃ ዘመን ነው !

በዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያ ታጅቦ እና ዓለማቀፍ የምት ዘሮችን ተንተርሶ ቺግቺጋ፣ ፖፕ፣ ትዝታ/ዋልዝ እና ሬጌን የመሳሰሉትን ቅንብሮች ከአገርኛ ቅኝቶች ጋራ ደባልቆ ከአንድ ክ/ዘ በላይ በተጓዘው የአገሩ "ዘመናዊ" ሙዚቃ "ወርቃማው የሙዚቃ" ዘመን እይተባለ በስፋት ሲሞካሽ የምንሰማው የዕለት ተዕለት ትርክት ነው። ይህ ትክክል ነው፤ ትክክል አይደለም የሚለው አግባብ የሆነው ጥያቄ ለባለሙያዎቹ ተከድኖ ይቀመጥና፤ አንድ ትክክለኛ ቁምነገርን ግን እናስታውስ።

ለመሆኑ እንዲያው በጥቅሉ "ወርቃማ" የሚል ምክንያትነቱ አጠያያቂ የሆነ ስያሜ ያገኘው የ"1950" ዎቹ እና ቀጥሎም የመጣው እና እስከ "1980" የተቀነቀነው ሙዚቃ ምን ያህል በጥልቀት እና ዓለማቀፋዊ ባህሪያትን በተላበሰ የባለሙያዎች ጥናት እና ህዝባዊ ተሳትፎ ተተንትኖ ይሆን እንደ ደብተራ መፅሐፍ ሚስጥር ሆኖ በታመነበት ስያሜው እንዲፀና የተደረገው? አንድንስ ሙዚቃ ወይም የሙዚቃ ዘመን ምርጥ ወይም "ወርቃማ" የሚያሰኘው ባህሪይቱ ምን ምን ናቸው?...ለመሆኑ ሙዚቃ እንደ ሌሎቹ የስነጥበባት የዘር ሃረጉ ምርጥነቱ ወይም ውጤቱ የሚለካው በተደራሲያኑ ላይ በሚፈጥረው ሁለንተናዊ ተፅዕኖ ነው ወይስ በደራሲያኑ እና ባለሙያዎቹ ብቃት ነው?...እነዚህ እና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎች ተንሸራሽረው እና ዓለማቀፍ ምጣኔ ያለው ጥናት እና ምርምር ተካሂዶ ቁርጥ ውስኔ ላይ እስካልተደረሰ "ሾላ በድፍኑ" የመሰለ ትርክት ከትርክትነቱ አያልፍም።

በርካታ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና አድማጮች "ያሁኑ ሙዚቃ ይሻላል፤ የድሮ ሙዚቃ?" ወይም ደግሞ የድሮውን ሙዚቃ "ወርቃማ" ያሰኘው ምክንያት ምንድን ነው? በሚል ለሚቀርብላቸው የተሳከር ጥያቄ የሚሰነዝሩት የተሳከረ መልስ በዋናነት በሁለት መሰረታዊ ጽንሰ-ሃሳቦች ላይ የቸነከሩ ሆነው ይገኛሉ፦ አንድም የፈረደበት "ባንድ" ሌላው ደግሞ ስንፍና እና አቅመቢስነት የሚያጠቃውና የድምጻውያኑ ለገንዘብ የሚሰጡት ቦታ። እንግዲህ የየቀድሞውን እና ያሁኑን ሙዚቃ አስመልክቶ ለሚቀሰቀሰው ስሜታዊ ክርክር ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ዋናዋናዎቹ እነኚህ ሁልቱ ከሆኑ "ተከራካሪዎች ሆይ በከንቱ አተከራከሩ፤ ይልቁን ጉንጭ አልፋ ክርክራችሁን ወዲያ አሸቀንጥሩና ኤልያስ መልካ የተባለን የዘመኑን የሙዚቃ ፈላስፋ በሰላ ጆር፣ በተረጋጋ ልብ እና በሚያሰላስል አዕምሮ ተዘጋጅታችሁ አድምጡ ትባላላችሁ !

ኤልያስ መልካ በጠባብ ክፍል ውስጥ አንድ ኪቦርድ ይዞ ሙዚቃን በማቀናበር የመጀመሪያው አይደለም፣ ከመጀመሪያዎቹ ግን አንዱ ነው። ከሱም በፊት ከሱም በኋላ የመጡት ግን የሙዚቃ እውቀት እና የመሳሪያዎች ጥራት ካልከፋፈሏቸው በስተቀር በመሰርታዊ የመሽን ቅንብር አንዱን ካንዱ ለመለየት በሚያስቸግር መልኩ ተመሳሳይ እና አሰልቺ ናቸው። ኤልያስን ታዲያ ምን ለየው?...

ኤልያስ ወደ ሙዚቃ የገባው ቦክስ ጊታር በመጫወት ነው። እሱ ቦክስ ጊታር (የክር መሣሪያ) በሚጫወትበት የልጅነት እድሜ ደግሞ የአገሩ ሙዚቃ በጡሩንባ የታጀበ (ብራስ ባንድ) ነበር። የሙዚቀኛን ጆር ብቻ ሳይሆን የአድማጭንም ጆሮ የታደለው ኤልያስ መልካ ከልጅነት ዘመኑ ገናና የነበረውን "ሮሃ" የተሰኘ የአንጋፋዎችን ባንድ ሙዚቃ ሲያዳምጥ ይማረክበት የነበረው ድምጽ ሠላም ሥዩም ከሚያናግራት ጊታር የሚወጣው እንጂ ከሌሎቹ አልነበረም። ስለዚህ የኢትዮጵያ "ዘመናዊ" ሙዚቃ የምት አንድነት እና ተደጋጋሚነት የሚያጠላበት እንደሆነ በመረዳት አዲስ ድምጽ እንደሚያስፈልገው በመገንዘብ ወደ ሙዚቃ ቅንብሩ "ሀ" ብሎ ሲገባ በጡሩንባ የተደበደበውን ሙዚቃ በክር አክሞ ማስታመም ነበር ተቀዳሚው ሥራ።

ከዚህም በላይ የትውልዱን የባህር ማዶ ሙዚቃ መላመድ በጥበባዊ አይኖቹ አሻግሮ የተመለከተው ወጣት አሰልቺ እና ድግግሞሽ የሚስተዋልበትን "ቺግቺጋ" የተሰኘውን የአገሩን የሙዚቃ ሥልት እንደ ሞገደኛ ምሁር ፈነቃቅሎ ሳያፈራርሰው በዘዴ እና በጥበብ ከ ባህርማዶዎቹ "ሬጌ"፣ "ሮክ ኤን ሮል" እና "ፖፕ" ሙዚቃ ስልቶች ጋራ ተጣጥሞ የሚሄድበትን መንገድ እንደ አንዳንዶቹ ተስፈኞች ባሕር ማዶ መሻገር ሳያስፈልገው ደጁን ቆልፎ በመለማመድ እና ተፈጥሮ ያደለችውን የሙዚቃ ምትሃት እንደዛር በላዩ ላይ እና በተከታዮቹ ላይ በማውረድ ላለፉት ሃያ ዓመት በመደነቅ ስሜት ውስጥ የሰማናቸውን ጊዜ አይሽሬ ሙዚቃዎች አበርክቶልናል።

የአብነት አጎናፈር ሁለት ቀደምት ሥራዎች፣ የሚካኤል በላይነህ ሁልተኛ አልበም፣ የትዕግስት በቀለ "ተረታሁ"፣ የዘሪቱ ከበደ "ዘሪቱ" እና የሚኪያ በኃይሉን "ሸማመተው"ን ለአብነት መጥቀስ ብቻ በቂ ነው።

ከዚህ ባሻገር ኤልያስ እንደ አብዛኞቹ አንድዬ አቀናባሪዎች ኪቦርድ ላይ በተሞላ መሣሪያ በመጫወት "የትም ፍጪው ..." አይነት ንዝላልነት ፈጽሞ የሌለበት ሙሉ ሙዚቀኛ መሆኑን ለመመስከር "ኦሮማይ" በተሰኘው የእንዳሌ አድምቄ ሁልተኛ አልበም፣ "አንተ ጎዳና"በተሰኘው የሚካኤል በላይነህ ሁልተኛ አልበምና በሌሎችም ጥቂት የማይባሉ ቅንብሮቹ ውስጥ "ሙሉ" ሊባል የሚችል የባንድ ስብስብ ተጥቅሞ የግሉን ችሎታ በባንድ ልክ የፈተሸ የግለሰብ ባንድ ነው። ለነገሩ በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ተማሪ እያለ ከመምህራኖቹ ጋራ መድረክ ተጋርቶ ሙዚቃ በመጫወት በእሱ ሰበብ አብሮት የድሉ ተጠቃሚ ከነበረው አብሮ አደጉ ቢንያም በድሩ ካልሆነ የትኛው ተጠቃሽ ሙዚቀኛ ሊጠራበት እንደሚችል እርግጠኛ አይደለሁም።

ከ"መዲና" አንስቶ "ስሪ ኤም" እና "ሚሊኒየም"አንቱ የተባሉ አንጋፋዎቹ የአገሪቱ ሙዚቀኞች ጋራ እኩል ተሰልፎ ሙዚቃን በግል ስቱዲዮ ብቻ ሳይሆን ብርቱ ጥረት በሚጠይቀው የአደባባይ ፈተናም ተዋውቋታል።ይህ ልምዱም መሬት ከሆነው ግለሰባዊ ማንነቱ እና ትህትናው ጋራ ተዳምሮ ከአንድም ሁልት ሦስት ጊዜ ጓደኞቹን በማሰባሰብ ተወዳጅ ባንዶችን ለማቋቋም በቅቷል። "አፍሮ ሳውንድ"፣ "ዜማ ላስታስ" እና "ኢትዮ ግሩቨስ" ተጠቃሾች ናቸው። ሥለዚህ የድሮ ሙዚቃ ወርቃማነቱ በባንድ መታጀቡ ከነበር የአንድ ሰው ጭንቅላት የሰራው የማይመስለውን እና አንድ ሆኖ ባንድ መሆን በቻለው ኤልያስ መልካ የተቀናበሩ ሙዚቃዎችን አብሮ መጥራት ተገቢ ይሆናል ማለት ነው።

ሁለተኛውም አመክንዮ ከዚህ የተለየ አይደለም። "የድሮ ሙዚቀኞች ካሴት ሲሰሩ ብዙ አመታት ይወስድባቸው ነበር፣ በዛ ላይ ለገንዘብ አልነበረም የሚሰሩት፤ ለጥበብ ነበር።" ከተባለም በዘመናችን ይህን ሲያደርግ ያየነው አንድ ሰው እሱ ኤልያስ መልካ ብቻ ነው። አንድን ድምጻዊ በሰለጠነ የመብት ውል አስማምቶ ስለ ካሴት ሥራ እና ውጤቱ ሙሉ ማብራሪያ ሰጥቶ ሲየበቃ ከ4 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚፈጅ የጊዜ ሰሌዳ ለትውልድ የሚተርፍ አልበም እሚደሰኩሩ ያደረጋቸው ድምጻውያን እሱ አርቆ ያስቀመጣቸው የዝና ማማ ላይ ሆነው ካልጠመሙ በቀር መናገር ይችላሉ።

ከኢዮብ መኮንን፣ እስከ ጌቴ አንለይ ያሉትን በርካታ ድምጻውያንን የቀድሞ ማንነት እና ሙዚቃዊ መረዳት በማጠያየቅ ከኤልያስ ጋራ ከተወዳጁ በኋላ ስለመጣው አዲስ ማንነት ምሥክር መስጠት ይቻላል።

እንደ እኔ አይነቱ እድለኛ አድማጭ ደግሞ ኤልያስ መልካን ደጅ ሳይጠና እና እነኛን ሁሉ የመልካም ሙዚቃ አሰራር ውጣ ውረድ ሳያይ ቤቱ ቁጭ ብሎ የእጆቹ አሻራ ያረፈባቸውን ሥራዎቹን በመኮምኮም የነብስም የሥጋም ድኅነትን አግኝቷል።

ከዕሜዪ ይቀጥልልህ ወዳጄ !!!

(በሄኖክ)

>>Click here to continue<<

አዲስ ጥበብ/ Addis Tibeb

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)