#ጥበቃ
ታዋቂው የሀዲስ ዘጋቢ እና የሰሃባ ተማሪ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) ሙሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) በአንድ ወቅት ከሰዎች ጋር እየተጓዙ ሳለ መሸባቸውና በወንዝ ዳርቻ ላይ ለማደር ወሰኑ። ማደሪያ ሲያዘጋጁ የአካባቢው ሰዎች ወደ እነርሱ ቀርበው እንዲጅ አሏቸው “ከዚህ ቦታ ሂዱ እዚህ ለማረፍ የሚሞክር ሁሉ ይዘረፋል። ይህንን ሲሰሙ ቡድኑ በሙሉ ዕቃውን ጠቅልለው ወደ ሌላ ቦታ ሄዱ - ከመሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) በስተቀር። እሳቸው ባነበቡት የጥበቃ አያት በሚሰጠው ደህንነት በመተማመን ብቻቸውን ምንም ሳይፈሩ ቀሩ።
ከዚያም ሙሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) የተከሰቱትን ክስተቶች እንዲህ ብለዋል:- “ወንበዴዎቹን ሳይ ገና አልተኛሁም። የተመዘዘ ሰይፍ ይዘው ነበር። ከሰላሳ ጊዜ በላይ ሊቀርቡኝ ቢሞክሩም መቅረብ አልቻሉም። ደህናና ሰላማዊ ሆኜ እስከ ጠዋት ድረስ በደንብ ተኛሁ። ሲነጋ እቃዬን ሰብስቤ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ስጓዝ ከዘራፊዎቹ አንዱ ግዙፍ የሆመ ቀስት ተሸክሞ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ቁጥቋጦ ውስጥ አጋጠመኝ። ጠራኝና “አንተ ሰው ነህ ወይስ ጂን?” ሲል ጠየቀኝ። "ሰው - ከአደም (ዐለይሂ ሰላም) ዘሮች" ስል መለስኩለት። ይህን ሲሰማ ደነገጠ፡- “ግን ሚስጥርህ ምንድን ነው? ከ70 ጊዜ በላይ ልናገኝህ ብንሞክርም በብረት ግንብ ተዘጋግተናል። እኔም መለስኩለት፡- “ምስጢሩ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ከነብይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የነገሩኝ ሐዲስ ነው፡- “በሌሊት ሰላሳ ሶስት የቁርኣን አንቀፅ ያነበበ ከሰው ሸር ፤ ከአዳኝ አውሬ፤ በቤተሰቡና በሀብቱ ከሚደርስ አደጋ ይጠበቃል እስከ ማለዳ ድረስ ፍጹም ደኅንነት እና ምቾት ይኖረዋል።” ሐዲሱን ዘግቤ ስጨርስ ውስጡ በጣም ተነካ ከፈረሱ ላይ ወርዶ ቀስቱን ሰበረ። "በአላህ ተአላ ስም ዳግም ወደ ዘረፋ ህይወት እንደማይመለስ ቃል ገባ።"
በሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት አንቀጾች፡-
1. ሱረቱ በቀራህ (ቁጥር 1-5፣ 255-257፣ እና 284-286)
2. ሱረቱ አዕራፍ (ቁጥር 54-56)
3. ሱረቱ በኑ ኢስራኢል (ቁጥር 110-111)
4. ሱረቱ ሳፋት (ቁጥር 1-11)
5. ሱረቱ ረህማን (ቁጥር 33-35)
6. ሱረቱ ሐሽር (ቁጥር 21-24)
7. ሱረቱ ጂን (ቁጥር 3-4)
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<