#ዘይኒ_ኩሊ_ዘይን
ክፍል አራት
ኢሻ/አዳር
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የዒሻን ሰላት ያዘገዩት ነበር። ወደ ቤት በሚመሱስበት ወቅት በአንዳንድ ምሽቶች አስፈላጊና ፖለቲካዊ የሆኑ ነገሮችን ለመወያየት ሶሓቦቹን አቡበክርና ዑመርን ይጎበኛሉ፤ አልያም ወደ ቤት አቅንተው ከቤተሰባቸው ጋር ውይይት አድርገው ይተኛሉ። በመንፈቀ ለሊት ይነቁና የተሀጁድ ሶላትን ይቀጥላሉ። በሌሊቱ መገባደጃ አካባቢ ሚስታቸውን 'ዊትር' እንድትሰግድ ከእንቅልፍ ከቀሰቀሱና ከሰገዱ ቡሀላ እስከ ፈጅር አዛን ድረስ ትንሽ ያርፋሉ።
ተግባራዊ ጠቃሚ ምክር፡ ከኢሻ በኋላ በተቻለህ ፍጥነት ብትተኛ፤ በለሊቱ ክፍል ቢያንስ ሁለት የተሀጁድ ሶላትን ለመስገድ ሞክር። ሽልማቶቹ አስደናቂ ናቸው!
በዚህ ዘመን የተለያዩ የስራ ሰአቶችን እንደሚያጣብቡን ምንም ጥርጥር የለውም ተግባራችንም ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) በነዚያ ጊዜያት ከነበሩት የተለየ ነው። ያ ግን የእሳቸው፦ ምሳሌ ላለመከተል ሰበብ አይሆንም! ዛሬም ቢሆን በእለት ተእለት ተግባራቸው ውስጥ ነብያዊ ሱናን ማካተት የቻሉ እና ድንቅ፣ ስኬታማ እና ውጤታማ ህይወት የሚመሩ በርካታ ስኬታማ ሰዎች አሉ። ከእነዚያ ሰዎች አንዱ ለመሆን እንሞክር ኢንሻ አላህ!
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<