"አስታራቂው_አህመድ!"
ቢስሚላሂ ብዬ መድሁን ልጀምረው፤
ስለ ዘይኔ ላውራ ስለዛ ደግ ሰው፤
ታማሚ ናፋቂ በየሀገሩ ሞልቷል፤
በመናም ለማየት አንቱን ይናፍቃል፤
መዲና መርገጥን ሁሉም ተመኝቷል፤
አንቱ ያ ሙስጠፋ አሽረፉል ሹረፋ፤
ዝናዎት የጎላ ውዴታው የሰፋ፤
እኛም ለመጠጋት እርሷ ጋር ለመድረስ፤
በሳዳቶቹ በኩል ጉዞ ስንገሰግስ፤
ከአብሬት ጀምረን ሼኽ መህሙድ ድረስ፤
በነዚህ ሰዎች ነው የልባችን ሚደርስ።
መጀን በሰይዲ በገውስ አብዱልቃድር፤
ትንሹም ትልቁ ለሱ ገብቶ ሚያድር፤
መጀን በሀሰነል በስሪ መገን በቢያዚድ፤
አሳምረው ሰፉት የሱፊዩን መንገድ፤
መጀን በጋዛሊ መገን በሩሚው ጀላሉዲን፤
የእውቀት አብነት ያበጁ ኪታቡን፤
መጀን በረመዳን ቡጢ መገን በጁነይድ፤
የጠላትን መሰረት ገንድሶ የሚንድ፤
መጀን በሼህ ካባኒ መገን በሼህ ናዚም፤
ፈጥነው ያደርሳሉ ሀድራውን ለሚያልም፤
መጀን በቡራኢ መገን በሼህ መህሙድ፤
ሁልጊዜ እንኑር በሙሀባው ስንነድ፤
መጀን በኔው በአለቃዬ ዩኑስ ኤምሬ፤
የግጥሙ ሰዳሪ የቅኔ መምህሬ፤
ላንቱ ገብቻለው ባንቱ ነው ማማሬ።
መጀን በአልፈቂህ መገን በአባድር፤
የተቅዋቸው ፅናት ፆም የማያሳድር፤
መጀን በራያ ሙፍቲ መገን በጀማ ንጉስ፤
ሲጠሯቸው ጊዜ በቶሎ የሚደርስ፤
መጀን በወረዋዩ መገን በቃጥባሪዩ፤
ህይወታቸውን ሙሉ በዲኑ የሰዩ፤
መጀን በአህመድ በደዊ መገን በዳኖቹ፤
ሀድራቸው የሚያጠገብ ለሁሉ የሚመቹ፤
መጀን በሼህ አሊ መገን በጫሌ፤
ለአቅል የከበዳ ስራቸው አያሌ፤
መጀን በሼህ ኢልያስ መገን በኑርሁሴን፤
ስማቸው ሲነሳ ሸረኛ የሚያበን፤
መጀን በገዳባኖ መገን በአልከሶ፤
ሀይባቸው ያማረ ከላማቸው ለስልሶ፤
መጀን በዘመናችን ኡስታዝ ፈድሉ፤
የመውሊድ አጋፋሪ እውቀት የሚያበሉ፤
መጀን በአብሬቶች መገን በሚቅባስ፤
ከሙስጠፋ ዘንዳ በቶሎ የሚያደርስ።
መጀን በፋጢማ መገን በእናቴ አሚና፤
በጀነት አለቆች ሀሳባችን ይቅና፤
መጀን በአኢሻ መገን በረሱል ሚስቶች፤
ከፊልስጤም ምድር ይሰማ የምስራች፤
መጀን በአሲያ መገን በመርየም፤
ለጀነቱ ሰርግ ሁሉ ሰው ይታደም፤
መጀን በኔ ራቢዓ መገን በሰይዳ ነፊሳ፤
የአላህ ሙቀረብ ዱኣቸው በላዕ ሚያነሳ፤
መገን በአውገረድ ሀዋ መገን በዙለይካ፤
ልባችን በፍቅር ያብብና ይፍካ፤
መጀን በሴቶች ሁላ መገን በእንስቶች፤
ዱኣችን ይሰማ ያድርገን ማንሰለች።
መጀን በአባቶች መገን በእናቶች፤
አድርገን ጌታዬ ለሰይዲ ምንመች፤
መጀን በአውሊያው አለምን በሞሉት፤
ወራሾች ተደርገው ከላይ በተሰጡት።
በነዚህ ሁሉ ወዳጆቻችሁ ብለናል፤
ዛሬ ከሀድራችሁ መታደም ሽተናል፤
ከሰይዲ ሚቅባስ በኩል ለምነናል፤
በሼህ መህሙድም ደብዳቤ ልከናል፤
በሙፍቲ ዑመር ቶሎ አስከትለናል፤
ሰይዲ ለወዳጅ አያውቁምና እንቢ፤
እኛንም አዝልቁን ከመዲናው ግቢ፤
ከረውዷው እንፍሰስ ሁኑልን ዋቢ፤
ወዳጅ አድርጋችሁ ምረጡን እድሉን፤
ከሀድራችሁ ስብሰባ እኛንም ሰብስቡን፤
በባለከራማው ጠላት በሚያርዱት፤
በሙፍቲ ዑመር በኩል ቪዛ ይስጡት፤
እኛም እንደነሱ በከንቱ አንሙት፤
በዘንድሮው አመት ታሪክ ይመዝገብ፤
ሀጅ የምናደርግበት ይሁንልን ያረብ፤
ሌላ ወሬ የለን ስላንቱ ነውንጅ፤
እንዲው እንደናፈቀን ሳናይ እንዳናረጅ፤
በመካ መዲና አስጉዘን መውላና፤
ሁሉ ባንተ ነው የጠመመው ሚቃና።
አሚን!!!!
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<