#የአሹራ_ክስተቶች
"አሹራ ማለት አላህ ሁሉንም አንቢያዎች በማህበረሰባቸው ከሚደርስባቸው በደል ያዳነበት እለት ነው። ትርጉሙ 'አሻ ኑራ - 'የበራ ቀን' ማለት ነው።
በዚህች ቀን አላህ ብዙ ነብያትን አከበረ። 1) አደምን (ዐ.ሰ) ለሰው ልጆች አባት እንዲሆን መረጠው። 2) ኢድሪስን (ዐ.ሰ) ወደ ሰማይ ከፍ አደረጋቸው። 3) ሰይዲና ኑህን (ዐለይሂ-ሰላም) በእለቱ በመርከባቸው ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር አዳነ። 4) ሰይዲና ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከእሳት የወጡበት። 5)ሰይዲና ዩኑስ (ዐ.ሰ) ከአሳ ነባሪው የወጡበት 6) ሰይዲና ዳውድ (ዐ.ሰ) ይቅር የተባሉበት ቀን። 7) የሱለይማን (ዐለይሂ-ሰላም) መንግሥት መለሰለት። 9) ሰይዲና ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ከጉድጓድ የወጡበት 10) ሙሳ (ዐ.ሰ) ከፊርኦን ጭቆና የዳኑበት 11) አዩብን (ዐለይሂ-ሰላም) በዚያ ቀን ከህመማቸው ገላገላቸው። 12) ሰይድና ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) በዚያ ቀን ወደ ሰማይ አነሳቸው። 13) የመልእክተኞች መደምደሚያ የሆኑት ሰይዲና ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) እና ሰይዳታ ኸዲጃን (ረ.ዐ) እንዲጋቡ አደረገ በዚህም ቀን ወደ መዲና እንዲሰደዱ አደረገ። 14) ሁለቱ የጀነት ወጣቶች የውዱ (ሰ.ዐ.ወ) የልጅ ልጆች መሰዋእት የሆኑበት። በዚህ ቀን ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ፤ ብዕርንም በዚህች ቀን ፈጠረ።"
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<