#በሙሀረምና_በአሹራ_ምን?
1. "ከኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የዙልሂጃህን የመጨረሻ ቀን እና የሙሀረምን የመጀመሪያ ቀን የፆመ ሰው የሃምሳ ዓመታት ወንጀሉ ይማራል።
2. ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የሙሀረምን የመጀመሪያ ጁምዓ የፆመ አላህ የቀደመ ወንጀሎቹን ይማርለታል፣ የሙሀረምን ሶስት ቀን የፆም ሰው አላህ እያንዳንዱ የመልካም ስራ ምንዳውን በዘጠኝ መቶ ያባዛለታል።
3. ከአኢሻህ ኡሙል ሙእሚኒን (ረዐ) እንደተላለፈው ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)። “እስከ ዐሹራ ድረስ የመጀመሪያዎቹን አስር የሙሀረም ቀናት የጾመ ሰው ጀነት አል-ፍርዶስ ይወርሳል።"
4. የዐሹራ ጾም ሱና ነው ሙአከዳህ በጣም ተፈላጊ ነው። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) የመዲና አይሁዶች በእለቱ ሲጾሙ ባዩ ጊዜ ምን እንደሆነ ጠየቆቸው። ሙሳ በኒ ኢስራኢል ከፈርዖን እጅ የመራቸው ቀን እንደሆነ ነገሮቸው። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) “ከእናንተ አይሁዶች የበለጠ በሙሳ ላይ መብት አለኝ” አሉ። ያን ቀንም ጾሞ እንዲፆምም አዘዙ። ይህ ከዓኢሻ (ረዐ) የረዘመ ዘገባ አካል ነበር።
5. ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የዐሹራን (10ኛውን ሙሀረም) የፆመ ሰው አላህ አንድ ሺህ ወንጀል ይሰርዝለታል አንድ ሺህ ምንዳ ይፅፍለታል፣ የሺህ ሸሂድንም ምንዳ ይሰጠውል፣ በጀነትም ውስጥ ሰባ ቤተ መንግሥቶችን ይገነባለታል፣ አካሉንም ከጀሀነም እሳት እርም ያደርገዋል።
6. በሌላ ሀዲስ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አሹራን የፆመ ሰው የሺህ መላኢኮች ምንዳ ይሰጠዋል ። በዐሹራ ቀንም ‹ቁል ሁዋ አሏሁ አሀድ›ን ሺ ጊዜ ያነበበ ሰው አላህ በእዝነት አይኖች ያየውና ከሲዲቂን (ከእውነተኞቹ) አድርጎ ይፅፈዋል።
7. በሌላ ሀዲስ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ከአሹራ በፊት ያለውን ወይም ከዚያ በኋላ ያለውን ቀን በመፆም ከአይሁዶች ተለዩ።"
8. በዐሹራ ቀን አራት ሱና ረከአት የሰገደ ሰው ከፋቲሐ በኋላ በእያንዳንዱ ረከዓ ‹ቁል ሁዋ አሏሁ አሀድ› አስራ አንድ ጊዜ ያነበበ አላህ የሃምሳ አመት ወንጀሉን ይማርለታል። በዐሹራ ቀን የሱና ሻወር ያወሰደ ሰው በዚያ አመት ከሞት ህመም በስተቀር አይታመምም እና ኩህልን በአሹራ ቀን አይኑን የተቀባ ሰው በዚያ አመት ህመም አይሰማውም።
9. የአሹራ ዱዓ፡-
“ሀስቡን አላሁ ወኒመል ወኪል፣ ኒእመል መውላ ወኒእማን ነሲር” [70 x]፣
“ሀስቡን አሏህ መለአል ሚዛን ወሙንታሀል ኢልም፣ ወመብለገል ሪዳ፣ ወዚነተል አርሽ፣ ላ መልጃአ ወላ መንጃ ሚነሏህ ኢላ ኢለይህ። ሱብሀን አሏህ 'አደደ- ሸፍኢ ወል አርሺ፣ ወአደደ ከሊማቲ ረቢና- ታማቲ ኩሊሀ። አስዓሉከ ሰላመ ቢራህማቲከ ያ አርሃመ ራሂሚን፣ ወላ ሀውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል አሊይል አዚም ወሁወ ሀስቢየላህ ወኒእምል ወኪል፣ ኒዕማል መውላ ወኒእማን ነሲር። ወሰለሏሁ ዐላ ሰይዲና ሙሐመዲን ወአላ አሊሂ ወሷቢሂ አጅመዒን። [7x]
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<