#ለወደደው 1⃣
በአንዱ ለሊት የበስራ መስጂድ ኢማም ማሊክ ኢብኑ ዲናር አርፍደው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነበር። አንድ ሰው "አላህ...አላህ...አላህ" እያለ ሲጮህ ሰሙ። ፊታቸውን አዙረው የሚሰማውን ድምፅ ሲያጣሩ አንድ የተኛ ሰካራም ሆኖ አገኙት።
መሀረባቸውን በውሃ አርሰው የሰውየውን ከንፈር ጠራረጉት፡- ‹‹ከሁለት ከንፈሮች ታላቁ መለኮታዊ ስም በአልኮል ረክሶ እንዳይወጣ አላህ ሆይ የዚህን ሰው ልብ ምራው።" ሲሉ ዱኣ አደረጉ።
በዚያች ሌሊት ማሊክ ህልም አዩ። "አንተ የሰውየውን ከንፈር ስለ እኛ አነጻህው እኛ ልቡን ስላንተ አንጽተናል"
ቀናት እና ሳምንታት አለፉ አንድ ቀን ፈጅር ላይ አንድ ሰው ሙሉውን ሶላት እያለቀሰ ሲሰግድ ሰሙ። ከዚያም በኋላ እንዲህ ሲሉ ዱኣ አደረጉ ፡- “ጌታዬ ሆይ ንገረኝ ዛሬ ላከብርህ ንስሐዬን ተቀብለሃልን ነፍሴን አጽናና ዘንድ።"
"ማነህ፧" ወደ ሰጋጁ በማምራት ኢማም ዲናር ጠየቁ።
ከንፈሬን ያነጻሃቸው ሰው እኔ ነኝ።
ኢማሙም "አሁን ሁኔታህ እንዴት ነው?"
ሰውየውም “አንተ በተኛህ ጊዜ የመራኝ የኔን ሁኔታ ነግሮሃል” አላቸው።
ስለ ማሊክ ኢብኑ ዲናር ልብ ሊባል የሚገባው ነገር አለ። ብዙ ሰዎች በእጁ ንስሃ ገብተዋል ምክንያቱም እሱ ራሱ ንስሃ ከመግባቱ እና የሃሰነል በስሪ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት ሰካራም ነበር እና በመጨረሻም የሃሰን ምትክ ሆነ። በዚህ ግላዊ ልምዱ ምክንያት፣ በቀላል፣ ልቦችን እንደሚመልስ እና ልማዶችን እንደሚያጸዳ በአላህ ኃይል ይተማመናል። ማናቸው? ምን ሰሩ? እንዴት ተመለሱ?
ይቀጥላል...
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<