TG Telegram Group & Channel
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy | United States America (US)
Create: Update:

...ካለፈው የቀጠለ

የዘመነ ትንሳኤ አነሳስና ምንነት

‹‹ዘመነ ትንሳኤ›› በ1350 አካባቢ በፍሎረንስ (ሰሜን ጣሊያን) በሚኖሩ ጥቂት ሥነ ሰብዓውያን (Humanists) የተጀመረ ‹‹የጥንት ትምህርቶችና የሥነ ፅሁፍ ዳግም ልደት ነው (Renaissance means a rebirth of literature and a devotion to classical learning)፡፡›› የዘመን ርዝማኔውም እስከ 16ኛው ክ/ዘ ድረስ ያሉትን የፕሮቴስታንትና የካቶሊክ ተሐድሶዎችን (Protestant Reformation and Catholic Counter Reformation) እንዲሁም የሳይንስ አብዮትን ያጠቃልላል፡፡ አንዳንድ ፀሐፍት ደግሞ ዘመኑን እስከ 17ኛው ክ/ዘ ድረስ ያደርሱታል፡፡

‹‹Renaissance›› የሚለው ፅንሰ ሐሳብ የኢኮኖሚ አሊያም የፖለቲካ ፅንሰ ሐሳብ ሳይሆን የባህል ፅንሰ ሐሳብ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ‹‹Renaissance›› በ14ኛው ክ/ዘ የነበሩ ምሁራን (ሥነ ሰብዓውያን) የጀመሩት የሥነ ፅሁፍ ንቅናቄ (Literary Movement) ነው፡፡ በመሆኑም፣ ‹‹ዘመነ ትንሳኤ›› በሁሉም መስክ ያሉ የአውሮፓ ምሁራን ህይወት ላይ ተፅዕኖ የሳረፈ የባህል ንቅናቄ (Cultural Movement) ነው የጥንት ግሪካውያንንና ሮማውያንን የሥነ ሰብዕ ሥራዎችን (Humanities) በድጋሜ የማንሳት ሥነ ፅሁፋዊ ንቅናቄ ነው፡፡ በዚህ ንቅናቄ ያልተነካ የሙያ መስክ የለም ኪነ ጥበቡ፣ ሥነ ፅሁፉ፣ ፖለቲካው፣ ፍልስፍናው፣ ሳይንሱ... ሁሉ ተፅዕኖ አርፎበታል፡፡

ዘመነ ትንሳኤ በባህሪው ፀረ ሃይማኖት ንቅናቄ አልነበረም፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛዎቹ ሥነ ሰብዓውያን የቤ/ክ ሰዎች ስላልነበሩ ለሥነ መለኮት (Theology) አነስተኛ ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም፣ በአቋማቸው ግን ፀረ—ሃይማኖት አልነበሩም፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን፣ ለመካከለኛው ዘመን ‹‹የጨለማው ዘመን (Dark Age)›› የሚለውን መጠሪያ የሰጡትም በዚያው ዘመን የነበሩ እነዚህ ሥነ ሰብዓውያን ናቸው፡፡ ይሄንንም ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው Petrarch ነው፡፡

የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንም የሥነ ሰብዕ ንቅናቄው ተቃዋሚ አልነበረችም፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ቤተ ክርስትያኗ በርካታ የሥነ ሰብዕና አርት ሥራዎችን ስፖንሰር ስታደርግ ነበር፡፡ ለዚህም ጥሩ ተጠቃሽ የሚሆነው ቤ/ክኗ በወቅቱ ታዋቂ ሰዓሊ የነበረውን ራፋኤልን (Rapahael) በ1509 ኮሚሽን በማድረግ በቫቲካን ለጳጳሳት መኖሪያ የተሰራው ቪላ ቤት ግድግዳ ላይ የጥንት ግሪክ ፈላስፎችንበአንድነት እንዲሳል ማድረጓ ነው። ይሔም ስእል "school of Athens" ይባላል።

በመሆኑም፣ በወቅቱ የሥነ ሰብዓውያን ዋነኛ ፍላጎት የነበረው በክርስትና አውድ ውስጥ የጥንት ግሪካውያንና ሮማውያን የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች በድጋሜ እንዲያቆጠቁጡና ከመንፈሳዊው ህይወት ጎን ለጎን ለዓለማዊው ጥበብም ትኩረት እንዲሰጠው የማድረግ ጥረት ነው፡፡

በርግጥ፣ የጥንት የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች ከመንፈሳዊነት ይልቅ ዓለማዊ ይዘት ያላቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከ1000 ዓመታት በፊትም ክርስትና ‹‹አያስፈልጉኝም፤ የአህዛብ ሥራዎች ናቸው›› በማለት የቀበራቸው ናቸው፡፡ በ14ኛው ክ/ዘ የተነሱት ሥነ ሰብዓውያን ግን ‹‹ያስፈልጉናል›› በማለት ከተቀበሩበት እንዲወጡ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ይሄ እንግዲህ ፊት ለፊት የማይታይ በክርስትናና በሥነ ሰብዓውያን መካከል ያለ ውስጣዊ ተቃርኖ ነው፡፡

ይሄ ውስጣዊ ተቃርኖ በጊዜ ሂደት ምን ይፈጥር ይሆን? ወይም ደግሞ በሌላ አነጋገር፣ ዓለማዊ የሆኑት የጥንት የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች መንፈሳዊ ከሆነው ክርስትና ጋር መሳ ለመሳ ሲቀመጡ፣ ይሄ መስተጋብር (dynamism) ክርስትናን ቀስበቀስ ወዴት ይወስደው ይሆን? ይሄ ጥያቄ ወደፊት ከ100 ዓመታት በኋላ በProtestant Reformation እና በካቶሊክ ‹‹Counter Reformation›› የሚመለስ ይሆናል፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን፣ የዘመነ ትንሳኤ ምሁራን የጥንት የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች እንዲያብቡ ከመፈለግ ውጭ ክርስትናን የመቃወምም ሆነ የማደስ (Reform የማድረግ) ሐሳብ እንዳልነበራቸው መታወቅ አለበት፡፡

በአጠቃላይ ዘመነ ትንሳኤ

👉ከመንፈሳዊው ህይወት "ብህትውና" ጎን ለጎን ሀይማኖቱን ሳያጠፋ ለአለማዊው ህይወት (ለጥንት ግሪካውያንና ሮማውያን እውቀት) ትኩረት መሰጠት የጀመረበት

👉የፕሌቶ ፍልስፍናዊ ሀሳቦች ገዢ ሆነው ዳግም የተነሱበት

👉የካፒታሊዝም ስርአት መፈጠር ጋር ተያይዞ በመካከለኛው ዘመን (በፊውዳል) ከነበረው የሕዝባዊ ህይወት ይልቅ ግላዊ ህይወት እያየለ መምጣት የዚ ዘመን መገለጫዎች ናቸው።

የዘመነ አብርሆት አነሳስና ምንነት

ዘመነ አብርሆት የሳይንስ አብዮትን (Scientific Revolution) ተከትሎ በአውሮፓ ከ17ኛው ክ/ዘ መጨረሻ እስከ በ18ኛው ክ/ዘ መጨረሻ ድረስ የተከሰተ ምሁራዊና ፍልስፍናዊ ንቅናቄ ነው፡፡ ንቅናቄው ከፈረንሳይ ጀምሮ ወደ ጀርመን፣ ስኮትላንድና ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች የተስፋፋ ነው፡፡ ልክ በዘመነ ትንሳኤ ጊዜ በፍሎረንስ (ጣሊያን) እንደሆነው ሁሉ፣ ዘመነ አብርሆትም በፈረንሳይ ከዩኒቨርሲቲ ውጭ ያሉና ራሳቸውን በንባብ ያበለፀጉ ምሁራን የጀመሩት ፍልስፍናዊ ንቅናቄ ነው፡፡

ዘመነ አብርሆት በአብዛኛው ከፍልስፍና አንፃር የሚተረጎመው ‹‹አመክንዮ ወይም ምክንያታዊነት በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ›› አንፃር ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ፍልስፍና ዘመነ አብርሆትን የሚተነትነው ከአመክንዮ የዕድገት ሂደት አንፃር ነው፡፡ ለዚህም ነው ዘመነ አብርሆት ‹‹The Age of Reason›› ተብሎም የሚጠራው፡፡

ምንም እንኳ ‹‹ዘመነ ትንሳኤ›› ለፍልስፍና ያበረከተው አስተዋፅዖ አነስተኛ ቢሆንም፣ በአብርሆት ዘመን ግን በርካታ ፈላስፎችና የፍልስፍና ሥራዎች የተገኙበት ወቅት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ 18ኛው ክ/ዘ ‹‹የፍልስፍና ምዕተ ዓመት (The Century of Philosophy)›› እስከመባል ደርሷል፡፡

‹‹ሆኖም ግን፣ በፈረንሳይ የዘመነ አብርሆት ምሁራንና ፈላስፎች በዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህራን አልነበሩም፡፡ ይሄም የሚያመላክተን በዘመነ አብርሆት መሰረታዊ የፍልስፍና ዕውቀት ለሁሉም ሰው ያስፈልገዋል የሚል አመለካከት በዘመኑ የነበረ መሆኑንና የፍልስፍና ዕውቀት በዩኒቨርሲቲ ላሉ መምህራን ብቻ የተተወ ሙያ ገና መሆን እንዳልጀመረ ነው፡፡››

በአጠቃላይ ዘመነ አብርሆት

👉 የአመክንዮ በብቸኝነት የበላይ ሆኖ የታየበት ይህም በፊት የእውነት ፣ የስነምግባርና የስልጣን ምንጭ ተደርገው ሲታዩ የነበሩትን ሃይማኖትንና ባህልን የሚገዳደር ነው።

👉የአርስቶትል ፍልስፍናዊ ሀሳቦች እና ሳይንስ የገነነበት

👉ተጠራጣሪነት(skepticism to tradition) አመክንዮ የበላይ መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ ባህላዊ አስተሳሰቦች እና ልማዶች ላይ የሰፈነበት

👉ግለሰባዊነት (Indivisualism)፦ ግለሰብ የማንንም ሞግዚት ሳይፈልግ በራሱ ውሳኔ ሰጪ የሆነበት

👉ዴይዝም (deism) የአርስቶትል ሜታፊዚካል ፍልስፍና የታየበት ነው። በዚህ ፍልስፍና መሰረት ፈጣሪ አለ ግን ፈጣሪ ይችን ምድር ፈጥሮ ከጨረሰ በኋላ በራሷ ሜካኒካዊ ህግጋት እንድትመራ ትቷታል ወይም ፈጣሪ እዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት የለውም የሚል ፍልስፍና ነው። በዘመነ አብርሆት የነበሩ አብዛኞቹ ፈላስፍች ዴይስት ነበሩ።

በቀጠይ ስለ ዘመናዊነት እና ድህረዘመናዊነት እናያለን
ይቀጥላል
@zephilosophy

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
ዘመነ አብርሆት፣ ዘመናዊነት እና ድህረ- ዘመናዊነት (Enlightenment,Modernity and Postmodernity) ምንጭ ፦ የፍልስፍና ትምህርት ቅፅ ፩ አርታኢና አዘጋጅ ፦ ብሩህ አለምነህ የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እርስ በእርሳቸው በሚቃረኑ የሐሳብ ታሪኮች ውስጥ አልፏል። እነዚህም የመካከለኛው ወይም የጨለማው ዘመን (Dark age)፣ ዘመነ ትንሳኤ (Renaissance)፣…

>>Click here to continue<<

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)