የፍልስፍና ምንነት
ፍልስፍና የሰው ልጅ አካባቢውንና የራሱን ማንነት የሚረዳበት መንገድ ነው፡፡ ግምታዊ፣ ባህላዊ፣ ሳይንሳዊ ወይም ሐይማኖታዊ ከሆነው የግንዛቤ መንገድ በተለዬ ሁኔታ ነገሮችን ለመረዳትና ለመግለጽ የሚረዳ የእውቀት አይነት ነው ።
ከዚህ በተጨማሪ ፍልስፍና የምንለው የሰው ልጅ ማወቅ የሚፈልገውን ነገር ሙከራ ሣያደርግ፣ ልኬትንና ስሌትን ሣይጠቀም በህሊናዊ የመረዳትና የማመዛዘን ሁኔተ ብቻ ተጠቅሞ ነገሮችንና ሁኔታዎችን ለማወቅ የሚያስችለው መንገድ ነው::
የፍልስፍና እውቀት የተመሠረተው በህሊና የመገንዘብ አቅም ላይ ነው፤ በአጭሩ የፍልስፍና እውቀት ህሊናዊ እውቀት ነው፡፡ ህሊናዊ እውቀት የሚገኘው ደግሞ በህሊናዊ ተግባር (rational enterprise) ነው፡፡
በህሊናዊ ተግባር እውነትን ከሀሰት፣ ትክክል የሆነውን ስህተት ከሆነው መለየት የሚያስችለን አዕምሯዊ ሥራ ነው፡፡ አዕምሮ ሠራ የምንለው መጠየቅ ሲጀምር ነው፡፡ ሲመራመር ነው፤ እውነትን ሲፈልግ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ህይወቱን የሚመራ ሰው ፈላስፋ እንለዋለን፡፡
ሚለር ተመሣሣይ ሀሳብ አላቸው::
“ፍልስፍና ህሊናዊ ተግባር በመሆኑ በአመለካከቶቻችን ሥር ሊኖሩ የሚችሉ ድንቁርናን፣ ጭፍን አምላኪነትን፣ ወገንተኛነትን፣ የሌሎችን ሀሳብ በጭፍን መከተልን ፤ አዕምሮቢስነትን ለማስወገድ ይሻል።የምንከተላቸው ሀሳቦቻችን መጠየቅ ፤ መመርመርና በማስረጃና በአመክንዮ መደገፋቸውን መፈተሽ ያስችለናል።
ፍልስፍና እውነትን ይፈልጋል፣ ትርጉምን ይፈልጋል፣ ሰው እየኖረበት ያለውን የኑሮ ዘይቤውን ጠንካራና ደካማ ጐኑን፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን፣ መልካሙንና መጥፎውን ለመለየት ዕለት ዕለት ይፈልጋል፡፡ ፈላስፋም ፍለጋ ካልወጣ የኖረ ያህል አይሰማውም፤ ህሊናው እውነትን በመፈለግ ሱስ የተለከፈ ነው፤ ለፈላስፋ መኖር ማለት እውነትን ማወቅ ማለት ነው፡፡
ለዚህ ይመስላል ሜሪ ግሬስ (Mary Grace) የተባሉ ፈላስፋ የካቫኑ (John F.. Kavanaugh) የሚለውን ጽሑፍ ተመስርተው የሚከተለውን ለመናገር የተገደዱት፡፡
"ፍልስፍና ሰዎች ደስ ብሏቸው እንዲኖሩ መነቃቃት ይፈጥርላቸዋል፤ ብዙ መጠየቅ፣ መመለስ፣ መረዳት፣ መማር ያለብህ ነገር አለ በሚል አስተሳሰብ ተገፋፍተው መኖር እንዲችሉ ያደርጋቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምንም እንኳ ሥቃይ የሚፈጥሩ ፈተናዎች በየመንገዱ ላይ ቢኖሩም ፍልስፍናን መከተልና መያዝ ዋጋው ከፍ ያለ፣ አስደሳች፣ ህሊና የሚሰጠው ሃሴትም ተወዳዳሪ የሌለው ነው፡፡
የፍልስፍናን ምንነት ለመረዳት ባደረግሁት ጥረት በብዙ ነገር ብስለትን (ዕድገትን) እንደጨመርሁ አምናለሁ፤ እናም ራሴን ከፍልሰፍና ውጭ አደርጌ ማሰብ የማልችል ነገር ሆኖብኛል፡፡"
ትለናለች
ለመሆኑ ፈላስፋ ምን አይነት ባህሪ አለው?
ይቀጥላል
@zephilosophy
>>Click here to continue<<