TG Telegram Group & Channel
Zemedkun Bekele (ዘመዴ) | United States America (US)
Create: Update:

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የብዙዎች ጥያቄ ነው። "ሰዉ ምን ነካው? ምነው ደነዘዘ? ለምን ፈሪ ሆነ? ሀሞቱ የፈሰሰው ለምንድነው? ለምን አይቃወመም? ምን እስኪሆን ድረስ ነው የሚጠብቀው? ብላ ብላ ወዘተረፈ ንግግሮች ከብዙ አቅጣጫዎች ይሰማሉ። ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው አይደል የሚባል? አይ መሬት ያለ ሰው የሚሉም አሉ። እንደዚያ ነው። በእኔ እይታ ግን ለምን ሰው ፈሪ እንደሆነ በስሱ ለማሳየት ልሞክር።

"…ሰዉ ፈሪ የሆነበት ምክንያት መነሻ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም። መጠራጠር፣ አለመተማመን፣ ጠልፎ መጣል፣ ሸውከኝነት፣ አቃጣሪነት፣ አሳልፎ መስጠት፣ እወደድ ባይነት፣ ክህደት፣ ምቀኝነት፣ አስመሳይነት፣ ስግብግብ ራስወዳድነት፣ በሌላ ውድቀትና ሞት የራስ ነፃነት ፈላጊነት፣ ውሽልሽልነት፣ እስስትነት፣ መስሎ አዳሪነት፣ ሆዳምነት፣ ያለኝ ይበቃል አለማለት፣ የሌላ ፈላጊነት፣ ከሀዲነት፣ መናፍቅነት እነዚህና እነዚህን መሰል ኮተቶች፣ ከሰውነት የሚያሳንሱ ባሕርያት ባለቤቶች የሆንን ሰዎች መብዛት ሰዉን ፈሪ አድርገውታል።

"…የሕግ አለመኖር፣ የፍትሕ አለመኖር፣ አምባገነንነት መፈጠር ሰዉን ፈሪ ያደርገዋል። በተለይ የጭካኔ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስር፣ የጉልቤው መብዛት፣ በሕግ አምላክ የምትልበት ሥርዓት ያለመኖር ሰዉን ፈሪ ያደርገዋል። በአንድ ሀገር ሀገረ መንግሥቱ ጸንቶ የሚኖረው የሕግ የበላይነት፣ ተጠያቂነት፣ ፍትሕ፣ ርትዕ ሲኖር ነው። በሕግ አምላክ ስትለው ቀጥ ብሎ የሚቆም ሕግ አውጪ፣ ሕግ ተርጓሚ፣ ሕግ አስፈጻሚ አካል ሲኖር ያን ጊዜ ሀገረ መንግሥቱ ይጸናል። በዚያ ላይ ተጠያቂነት ሲኖር፣ መልካም አስተዳደር ይፈጠራል። ዜጎችም በነፃነት ይኖራሉ። ፍርሃትም ከሰው ልቡና ይጠፋል። ሁሉም ከሕግ በታች ይሆናል።

"…በነገሥታቱ ዘመን ጭቆና ቢኖርም በባንዲራው አምላክ፣ በሕግ አምላክ፣ በጃንሆይ፣ በእግዚአብሔር ስም፣ በአላህ ብሎ አንድ ሰው ከተናገረ ይደመጥ ነበር። የአባቴ ገዳይ ሸሽቶ ቤተ ክርስቲያን መስጊድ ከገባ እንኳ ፍትህ ያገኝ ነበር። የፍትህ ውሳኔው ሞት እንኳ ቢሆን የሞት ብይን በፍትሕ ሜዳ ሲበየን ተጠቂውም ወገን፣ አጥቂውም ወገን አይከፉም ነበር። ምክንያቱም ፍትሕ ለሁሉም እኩል ስትሆን ሕመም ቢኖረውም ቅቡልነት ግን አለው። ይኖረዋልም።

"…ይሄን የቆየ ለዘመናት ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ጋር የኖረ ፍትሕ፣ ርትዕ፣ ሕግና ሥርዓት አክባሪነት፣ የነበረንን ፈሪሐ እግዚአብሔር ሁሉ ሙልጭ አድርጎ መጀመሪያ ከኢትዮጵያውያን ልቦና ያወጣው ደርግ የተባለ ቅጥረኛ የኦሮሙማ አገዛዝ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ነው። ደርግ መጀመሪያ የሰበረው፣ ያጠፋው ምልክት፣ ምሳሌ፣ አርዓያ የሚሆኑትን በሙሉ ነው። ሕዝቡን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስበውን የ3ሺ ዘመን ምልክት የዘውድ ሥርዓትን አጠፋ፣ ገረሰሰ፣ ጣለ። ንጉሡንም፣ ፓትርያርኩንም በጭካኔ አንቆና አፍኖ ገደለ። ጭካኔ በፍትሕ፣ በሕግ፣ በሥርዓት ስፍራ ዙፋን ላይ ተቀመጠች።

"…ደርግ ቀይ ሽብር የሚል ሕግ ማስከበሪያ ሥርዓት ቀርጾ መጣ። ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ የሆነው ምን ይጠየቃል። መጀመሪያ ንጉሠ ነገሥቱን አፍኖ ገድሎ በላያቸው ላይ ቢሮ ሠርቶ ተቀመጠ። ነገርየው ተጣርቶ ባይነገረም ንጉሠ ነገሥቱን አፍነው ከገደሏቸው በኋላ በመንግሥቱ ኃይለማርያም መሪነት የተወሰኑቱ የደርግ ባለ ሥልጣናት ንጉሡን አርደው ደማቸውን በመጠጣት ሥጋቸውንም በመብላት ባዕድ አምልኮ መፈጸማቸውም ነው የሚነገረው። ቆይቶ በመንግሥቱ ኃይለማርያም ትእዛዝ ከፍርድ ውጪ ከ60 በላይ ሀገሬን ብለው ያገለገሉ ምሁራን የሆኑ ኢትዮጵያውያን በመሃይሞቹ ወታደሮች ተረሸኑ፣ ተጨፈጨፉ። ጭካኔና አረመኔነቱ ከዚህ ነው የጀመረው የሚሉ አሉ። ፍረሃትም በሰው ልቦና ነገሠ።

"…በንጉሡ ጊዜ አምስት ሳንቲም ነዳጅ ላይ ጨመረ ብሎ በነፃነት ተቃውሞ ያሰማ የነበረ ሕዝብ፣ ንጉሠ ነገሥቱን ሌባ፣ ሌባ ብሎ አዋርዶ አንገት አስደፍቶ በውርደት ያስገደለ ሕዝብ በንጉሠ ነገሥቱም ሆነ በሌሎች ተረገመ። ደርግ አለንጋ፣ አርጩሜ ሆኖ መጣ። ኢድዩ፣ ኢህአፓ፣ መኢሶን ወዘተ ተባብሎ ተቧድኖ ተጨፋጨፈ። ለውጥ አመጣለሁ ብሎ ከመስመር በወጣና በምዕራባውያን ተንኮል ተጠልፎ ሀገሩን ያዋረደ በሙሉ በአደባባይ ደሙ ፈሰሰ። የተማረ የገደለው ትውልድ ባልተማረው አብዮት ጠባቂ ተረሸነ። አብዮታዊ እርምጃ ተወሰደበት።

"…ሕግን አፍርሶ በሕግ አምላክ ቢል ማን ይስማ? በባንዲራው አምላክ ቢል ማን ይስማ? በእግዚአብሔር፣ በአላህ ቢል ማን ይስማ? እግዚአብሔር የለም ብሎ ፓትርያርኩን ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወስዶ አንቆ ገድሎ ከኢህአፓ ሴቶች ጋር በአንድ ጉድጓድ የቀበረ፣ የፕሮቴስታንቶቹን መሪ ፓስተር፣ የእስልምናውን ሁሉ የገደለው ደርግ ፈጣሪ የለም ብሎ መፈክር የቀረፀው ደርግ ቤተክርስቲያን ወደ አዳራሽንት ካልቀየርኩ ብሎ የፎገላውን ደርግ ማን ያስቁመው? ኢትዮጵያ በጡንቻ በሚያስቡ ጎሮምሶች እጅ ወደቀች፣ ተሰበረች፣ አሁን ይኸው ለመሞት እያጣጣረች ትገኛለች። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከደርግ ጭካኔ የተነሣ ፈሪ ሆነ። ለሞተባት ልጇ የጥይት የምትከፍል እናት ስትፈጠር አለቀ። ነገሩ ሁሉ ደቀቀ።

"…አየህ ያን ጊዜ የሞተው ሞቶ፣ ያለቀው አልቆ አባቴ ገሚሱ ልታገል ብሎ ጫካ ገባ። ገሚሱ ደግሞ እግሬ አውጪኝ ብሎ በሱዳን እና በጅቡቲ፣ በኬንያም አድርጎ እንደኔ ፈረጠጠ፣ ተሰደደ፣ ድራሽ አባቱም ጠፋ። ጫካ የገባው ገሚሱ በህወሓትና በሻአቢያ እዚያው በረሀ ተበላ፣ ተጨፈጨፈ፣ የተቀረው ለወያኔና ለሻአቢያ ተገረደ፣ ገረድ ሆነ። እነ ብራኑ ነጋ፣ እነ በረከት ስምኦን ገረድ ሆኑ። የተሰደደው በሙሉ በአውሮጳና በአሜሪካ በምዕራቡ አለም ቅብዝብዝ ሆነ። የተረገመ ትውልድ ስለነበረ ቢለብስ አያምርበት፣ ቢበላ አይጠግብ፣ ቢጠጣ አይረካ፣ ገንዘብ ኖሮት እንኳ ደስታ የራቀው ትውልድ ሆነ። ያ ትውልድ አሁንም በከዘራ እየሄደ ልቡ ጥቁር ነው። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባይ ክፉ አረመኔ ነው። የተረገመም አይደል?

"…የደርግ አባላት ጭካኔን ዘርተው፣ ሰዉን ትውልዱን ፈሪ፣ ዱዳ አድርገው ራሳቸውም ገሚሱ በሶማሌ ጦርነት፣ ሌሎች በሰሜኑ ጦርነት የአሞራ ሲሳይ፣ የጅብ የጥንብ አንሳ ቀለብ ሆኑ። ገሚሱም ወያኔ ሳትመጣ በመፈንቅለ መንግሥት ሰበብ ተጨፋጨፍው ዋጋቸውን ተቀባበሉ። ገሚሶቹ ወያኔ ስትመጣ እግሬ አውጪኝ ብለው ተሰደዱ። ለ17 ዓመታት የተንደላቀቀ ቤተሰብ ይመሩ የነበሩት የደርግ ቤተሰቦች ወያኔ ስትመጣ ወደ ስደት በተራቸው ፈረጠጡ፣ ገሚሱም እጁን አንከርፍፎ እንደ ጭራሮ ተሰልፎ በየቀበሌው እጁን ለወያኔና ለሻአቢያ አስረከበ። የደርግ ቤተሰቦች በተራቸው ተበተኑ። ለማኝ፣ ስደተኛ፣ ተንከራታች ሆኑ። እርግማን ነዋ?

"…የደርግ ባለ ሥልጣናትም በቀለዱበት ሕግ ተቀለደባቸው። አላገጡባቸው። በጥይት እንደነሱ ረሽነው ባያጠፏቸውም ወያኔዎች ፍርድ ቤት በማመላለስ አደንዝዘው አጀዝበው፣ አሳቅቀው፣ አማቅቀው ገደሏቸው። ፍርድ ጨርሰው ሊወጡ ሁለት ቀን የቀራቸውን የደርግ ባለ ሥልጣናት በመርዝ መርዘው ደፏቸው። እነርሱ ፍትሕን፣ ሕግን፣ ርትዕን፣ ሥርዓትን አጥፍተው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በደም አበላ እንዳጥለቀለቁ እነርሱም በተለያየ ምክንያት ፍዳቸውን በሉ። ዋናው የኦሮሙማ አውሬ፣ ቡልጉ ጭራቁ መንግሥቱ ኃይለማርያም ብቻ እንደጀዘበ ሞቱን እየለመነ ሳያገኛት በኅሊናው እየማቀቀ በቁም እስር ኑሮውን በስደት ይገፋል።

"…ትምህርት አቋርጠው ለእረፍት እንደወጡ በዚያው ጫካ የገቡት አረመኔዎቹ የትግሬ ነፃ አውጪዎቹ እነ ህወሓት 17 ዓመት ሙሉ በጫካ ኑረው፣ ባንክ እየዘረፉ፣ ድልድይ እያፈረሱ፣ ሃይማኖትና…👇ከታች ይቀጥላል…

>>Click here to continue<<

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)