ማኢዳህ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
5፥115 አሏህ፡- «እኔ ማዕድዋን በእናንተ ላይ አውራጅዋ ነኝ፡፡ በኋላም ከእናንተ የሚክድ ሰው እኔ ከዓለማት አንድንም የማልቀጣውን ቅጣት እቀጣዋለሁ» አለ፡፡ قَالَ اللَّهُ إِنِّي مُنَزِّلُهَا عَلَيْكُمْ ۖ فَمَن يَكْفُرْ بَعْدُ مِنكُمْ فَإِنِّي أُعَذِّبُهُ عَذَابًا لَّا أُعَذِّبُهُ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ
የቁርባን ነገረ መለኮት"Eucharistic Theology" በክርስትና ዐበይት ከሚባሉ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት መካከል አንዱ ነው፥ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት"Five Fundamental Sacraments" የሚባሉት፦ ምሥጢረ ሥላሴ፣ ምሥጢረ ሥጋዌ፣ ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ቁርባን እና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው። በምሥጢረ ቁርባን እሳቤ ውስጥ ዐበይት ክርስቲያኖች "ክርስቶስ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ነው" ብለው ያምናሉ፦
ዮሐንስ 6፥51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።
"ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ ሥጋዬ ነው" ስለሚል ክርስቶስ እራሱ የሚበላ ማዕድ እንደሆነ ይናገራሉ፥ ይህም ማዕድ ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት እንደሆነ ተነግሯል፦
ዮሐንስ 6፥53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።
"ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነው" ብሏል ተብሏል፦
ዮሐንስ 6፥54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።
"የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦
ማቴዎስ 26፥26 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ።
ነገር ግን ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ እንጀራው የሥጋው ምሳሌ እንደሆነ ተርጉሞታል፦
"እንጀራውን አንሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ "ሥጋዬም ይህ ነው፥ እርሱም የሥጋዬ ምሳሌ ነው" ብሎ የራሱን ሥጋ አደረገው"።
Against Marcion (Tertullian) Book IV(4) Chapter 40
በጽዋ ውስጥ ያለውን ወይን ደግሞ "ደሜ ይህ ነው" እንዳለ ተዘግቧል፦
ማቴዎስ 26፥27-28 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።
አውግስጢኖስ ዘሂፓ ወይኑ የደሙ ምሳሌ እንደሆነ ተርጉሞታል፦
"የሥጋው እና የደሙን ምሳሌ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ"።
Expositions on the Psalms (Augustine) Psalm Chapter 3 Number 1
ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "የኑባሬ ለውጥ"Tran Substantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"Mystical Change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። ሰዎች ጠፍጥፈው የሠሩት እንጀራ እና የጠመቁት ወይንን "የአምላክ ሥራ የሆነው ኢየሱስ ነው" ማለት የጤና ነው? መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው ሥጋ ከሰው ሰውነት ጋር ሲዋሐድ የሰው ሰውነት አምላክ ይሆናልን? ቁርባን በልተው ሲጸዳዱት ያ መለኮት ይጸዳዱታልን?
በፕሮቴስታንት ደግሞ ሁሉም ባይሆንም "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርታቸው አላቸው፥ ይህም "የኑባሬ ኅብረት"Con Substantiation" ይባላል።
"ፋሲካ" በሚባል "በዓል" ላይ በመሸም ጊዜ ኢየሱስ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ እንደተቀመጠ ይናገራል፦
ማቴዎስ 26፥20 በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ። Ὀψίας δὲ γενομένης ἀνέκειτο μετὰ τῶν δώδεκα μαθητῶν
"ጠረጴዛ" የሚለው የግዕዙ ቃል እራሱ "ማዕድ" ወይም "ገበታ" ማለት እንጂ ባለ አራት እግር ያለው "ጻሕል(ሳሕን) ወይም "ወጭት" አይደለም፥ "ጠረጴዛ" የሚለው የግዕዙ ቃል እራሱ "ትራፔዛ" τράπεζα ከሚል ግሪክ ኮይኔ የመጣ ሲሆን "ማዕድ" ማለት ነው። ለምሳሌ፦
የሐዋርያት ሥራ 16፥34 ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው። ἀναγαγών τε αὐτοὺς εἰς τὸν οἶκον παρέθηκεν τράπεζαν,
እዚህ አንቀጽ ላይ "ማዕድ" ለሚለው የገባው ቃል "ትራፔዛን" τράπεζα እንደሆነ ልብ አድርግ!
>>Click here to continue<<