የኢየሱስ ጌታ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ
በኢሥላም አስተምህሮት የኢየሱስ ጌታ አሏህ ነው፥ ኢየሱስ ከአሏህ የተሰጠው ተልእኮ "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" የሚል ነበር፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ
በባይብል ደግሞ "ኩሪዮስ" κύριος ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን ለአንዱ ፈጣሪ የሚውል ቢሆንም ለፍጡራን ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ለማመልከት ይገባል፥ ለምሳሌ፦ ሣራ ለአብርሃም፦ "ጌታ" ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፦
1 ጴጥሮስ 3፥6 እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ "ጌታ" ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት። ὡς Σάρρα ὑπήκουσεν τῷ Ἀβραάμ, κύριον αὐτὸν καλοῦσα·
እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል በግሪክ ኮይኔ "ኩሪዮስ" κύριος ሲሆን ሳራ አብርሃምን "ጌታዬ" ስትለው የገባው ቃል "አዶኒ" אדֹנִ֗י ነው፦
ዘፍጥረት18፥12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች። ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? "ጌታዬም" ፈጽሞ ሸምግሎአል። וַתִּצְחַ֥ק שָׂרָ֖ה בְּקִרְבָּ֣הּ לֵאמֹ֑ר אַחֲרֵ֤י בְלֹתִי֙ הָֽיְתָה־לִּ֣י עֶדְנָ֔ה וַֽאדֹנִ֖י זָקֵֽן׃
እዚህ አንቀጽ ላይ ሳራ አብርሃም በዕብራይስጥ "አዶኒ" אדֹנִ֗י ስትለው "አዶኒ" אדֹנִ֗י የሚለው ለፍጡራን የሚውል ማዕረግ ነው። የኢየሱስ ጌትነት በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሾ እና ጅማሮ ያለው ስለሆነ የባሕርይ ጌትነት በፍጹም አይደለም፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 ኢየሱስን አምላክ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። ἀσφαλῶς οὖν γινωσκέτω πᾶς οἶκος Ἰσραὴλ ὅτι καὶ Κύριον αὐτὸν καὶ Χριστὸν ἐποίησεν ὁ Θεός, τοῦτον τὸν Ἰησοῦν.
እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ባለቤት ሲሆን "ኢየሱስ" ተሳቢ ነው፥ በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "እንዳደረገው" የሚል ተሻጋሪ ግሥ አለ። ጌታ አድራጊው አንዱ አምላክ ሲሆን ጌታ ተደራጊው ኢየሱስ ነው፥ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ካረደገው የኢየሱስ ጌትነት መነሾ እና ጅማሮ ያለው ስለሆነ እና ጌታ ከመደረጉ በፊት በባዶነት ስለሚቀደም ጌትነቱ ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ያሳያል። ምክንያቱም "እንዳደረገው" ለሚለው የገባው ቃል "ኤፓዬሴን" ἐποίησεν ሲሆን ከዚህ በፊት ያልሆነ ወደ መሆን በመደረግ ለመጣ ነገር በግሪክ ኮይኔ ይጠቀምበታል፦
ዘፍጥረት 45፥9 "አምላክ" በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ "ጌታ" አደረገኝ። ἐποίησέ με ὁ Θεὸς κύριον πάσης γῆς Αἰγύπτου·
የግሪክ ሰፕቱአጀንት ዮሴፍ "አደረገኝ" ላለበት የተጠቀመበት ቃል "ኤፓዬሴ" ἐποίησέ እንደሆነ ልብ አድርግ! አምላክ ዮሴፍን ጌታ ማድረጉ ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ያሳያል ከተባለ እንግዲያውስ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ማድረጉ ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ያሳያል። "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ነው፥ መሢሑ በትንቢት መነጽር ያህዌህን "ጌታዬ" ብሎታል፦
ኢሳይያስ 61፥1 "የ-"ጌታዬ" የያህዌህ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ያህዌህ ቀብቶኛልና። ר֛וּחַ אֲדֹנָ֥י יְהוִ֖ה עָלָ֑י יַ֡עַן מָשַׁח֩ יְהוָ֨ה אֹתִ֜י לְבַשֵּׂ֣ר עֲנָוִ֗ים
እዚህ አንቀጽ ላይ "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ከሆነ ኢየሱስ አምላኩን "ጌታዬ" ማለቱ በራሱ የሚገዛለት ጌታ እንዳለው አመላካች ነው፥ ኢየሱስ አንድም ጊዜ "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י አልተባለም። ኢየሱስ በትንቢት መነጽር የፈጠረው ጌታ እንዳለው ተናግሯል፦
ምሳሌ 8፥22 "ጌታ" በቀድሞ ተግባሩ "ፈጠረኝ"። κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ
በግሪክ ሰፕቱአጀንት እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረኝ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤክቲሴን ሜ" ἔκτισέν με ሲሆን፣ በዕብራይስጥ ማሶሬት "ካናኒ" קָ֭נָנִי ሲሆን፣ በግዕዝ ደግሞ "ፈጠረኒ" ነው፥ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ምሳሌ 8፥22 ላይ "ፈጠረኝ" የሚለው ኢየሱስ እንደሆነ ያለምንም ልዩነት በወጥ ፍሰት አብራርተዋል። ኢየሱስን የፈጠረ ጌታ ጌትነቱ የባሕርይ ሲሆን የዓለማቱ ጌታ ነው፥ በጌትነቱ ላይ ባርነት የሌለበት ይህ ጌታ ኢየሱስን "ባሪያዬ" ይለዋል፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል። הֵ֤ן עַבְדִּי֙ אֶתְמָךְ־בֹּ֔ו בְּחִירִ֖י רָצְתָ֣ה נַפְשִׁ֑י נָתַ֤תִּי רוּחִי֙ עָלָ֔יו מִשְׁפָּ֖ט לַגֹּויִ֥ם יֹוצִֽיא׃
>>Click here to continue<<