TG Telegram Group & Channel
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics" | United States America (US)
Create: Update:

ሕይወትን መስጠት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥49 "በአሏህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፤ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ"፡፡ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ

የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምላክ እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራ እና በቃል ብርቱ ነቢይ ነበር፥ ኢየሱስ አምላክ ሲያደርግ እያየ የሚያደርግ እንጂ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፦
ሉቃስ 24፥19 እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በአምላክ እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ”።
ዮሐንስ 5፥19 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፥ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።

"ያ" የሚለውን የሩቅ አመልካችን ተውላጠ ስም አብ ለኢየሱስ ለማሳየት የሚያደርገውን ሥራ ያመላክታል፥ “ይህን” የሚለው የቅርብ አመልካችን ተውላጠ ስም “ያ” የሚለውን ተክቶ የመጣ ሲሆን አብ ለወልድ እንዲያደርግ የሚያሳየውን ሥራ ያመላክታል፦
ዮሐንስ 14፥31 አብም እንዳዘዘኝ እንዲሁ አደርጋለሁ።

አንድ አምላክነት ያለው ማንነት ምን መሥራት እንዳለበት ሌላ ማንነት እንዴት ያሳየዋል? አብ ወልድ ምን ማድረግ እንዳለበት ያሳየዋል፦
ዮሐንስ 5፥20 አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።

ኢየሱስ የሚያደርገውን ሁሉ አብ እያሳየው ብቻ ነው፥ “ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል” ሲል የሚሠራውን ሥራ ፈጣሪ እያሳየው ያደርጋል ማለት ነው። ከፈጣሪ እያየ የሚሠራ ማንነት እራሱ ፈጣሪ ከሆነ አንዱ የሚያሳይ ሁለተኛው እያየ የሚኮርጅ ሁለት ፈጣሪ ይሆን ነበር። ወልድ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት አብ ያሳየዋል ማለት ወልድ ሙታንን እንዲያስነሳ፣ ለምጻም እንዲያነጻ፣ ሽባ እንዲተረትር መመሪያ፣ ሥልጣን እና ኃይል ይሰጠዋል ማለት ነው፥ ለምሳሌ ፈሪሳውያን በሰይጧን ዘንድ ያዩት ያደርጋሉ ማለት ሰይጧን መመሪያ እየሰጣቸው ያደርጋሉ ማለት እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስም በአብ ዘንድ ያየውን ያደርጋል ማለት አብ መመሪያ እየሰጠው ያደርጋል ማለት ነው፦
ዮሐንስ 8፥38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።

ኢየሱስ ተአምር እንዲሠራ የጌታ ኃይል ሆኖሎት እንጂ ከራሱ አንዳች ሊያደርግ አይቻለውም። ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ ካልቻለ ሁሉን ቻይ አምላክ አይደለም፦
ሉቃስ 5፥17 እርሱም እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት።
ዮሐንስ 5፥30 እኔ “ከ”-“ራሴ” አንዳች ላደርግ አይቻለኝም።

“እኔ” የሚለው ባለቤት ተውላጠ ስም እና "እራሴ" የሚለው ድርብ ተውላጠ ስም የኢየሱስን ሙሉ "እኔነትን" እንጂ ሥጋን አያሳይም፥ ሥጋ ብቻውን ማንነት ስላልሆነ “እኔ” እና "እራሴ" ሰለማይል ኢየሱስ ከማንነቱ ምንም ማድረግ አይችልም። ኢየሱስ በአምላክ የተደገፈ ጥገኛ ባሪያ ነው፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ "ደግፌ የያዝሁት" ባሪያዬ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት "ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።

መንፈሱን ያሳረፈበት ተአምር እንዲሠራ ነው። ጭራሽ ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ በፈጣሪ ስም ሲሆን እርሱ ነቢይ ስለመሆኑ የሚመሰክር ነው፦
ዮሐንስ 10፥25 እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል።
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ ይህ የማደርገው ሥራ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።

ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ ሁሉ እርሱ መልእክተኛ ስለመሆኑ ምስክር እንዲሆን በስጦታ ያገኘው ስለሆነ “አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ” በማለት እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው "የሰጠኸኝን ሥራ" ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤

“የሰጠኸኝን ሥራ” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ሁሉን ማድረግ የሚችል ማንነት ከሌላ ማንነት የሚሠራበትን ዐቅም በስጦታ በፍጹም አይቀበልም፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን አብ እንዳዘዘው ኢየሱስ ያደርጋል። ኢየሱስ ሲያደርግ የነበረውን ሥራ ሙት ማስነሳት፣ ሽባ መተርተር፣ ዕውር ማብራት ወዘተ በእርሱ የሚያምን ሰው ሊያደርገው ይችላል፥ እረ ኢየሱስ ካደረገው በላይ የሚበልጥ ያደርጋል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፥ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።

እውነት ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ቢሆን ኖሮ ሁሉን የሚችል አምላክ ሊያደርግ የሚችለውን ሰው ሊያደርግ ይችላልን? ከሁሉን የሚችል አምላክ በላይ የሚበልጥ ሥራ ሊሠራ ይችላልን? ነገሩ ኢየሱስ፦ "የሚሳናችሁም ነገር የለም" ብሏል፦
ማቴዎስ 17፥20 የሚሳናችሁም ነገር የለም።

>>Click here to continue<<

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)