TG Telegram Group & Channel
ፀረ ዝሙት | United States America (US)
Create: Update:

@ይነበብ
👇👇👇

#የተጨማለቀው_ህይወቴ"

ለመጀመሪያ ጊዜ ልቅ የወሲብ ፊልም ወይም ፖርኖግራፊ ያየሁት የ13 ዓመት ልጅ ሆኜ የትምህርት ቤት ጉዞ ባደረግንበት ወቅት ነበር፡፡ አንዱ ጓደኛዬ ብዙ ልቅ የሆኑ ለወሲብ የሚያነሳሱ ፎቶ ግራፎች ያሉበትን መፅሔት ከቦርሳው ሲያወጣ በጣም ነበር የደነገጥኩት፡ ፡(በእርግጥ ይህ የሆነው ኢንተርኔት ከመጀመሩ ከብዙ አመታት በፊት ነው፡፡) ጓደኛዬም ወደፊት ማወቄ ስለማይቀር አሁን አስቀድሜ ማወቄ ጥሩ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ በእርግጥ ምስሎቹ በጣም ማራኪ ናቸው የሚገርመው ነገር ደግሞ ያየሁት ምስል ሁሉ መርሳት እስኪያቅተኝ ድረስ በህሊናዬ ታትሞብኝ ነበር፡፡

ከዚህ ጊዜ ብዙም ሳይቆይ በቴሌቨዥን አልፎ አልፎ ፖርኖግራፊን የሚያካትቱ አንዳንድ ፊልሞች ቅዳሜ ቅዳሜ ማታ ይታዩ ጀመር፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ በጊዜ ወደቤት ገብቼ እተኛ እና ልክ ሁሉም ሲተኙ ቀስ ብዬ ተነሰቼ የቲቪውን ድምፅ ቀንሼ ቁጭ ብዬ እከታተል ነበር፡፡ በዚህም ጭንቅላቴ በፖርኖግራፊ እየተበከለ መጣ፡፡ በጣም ትንሽ ልጅ ሆኜ እንኳን ፖርኖግራፊ ካየሁ በኃላ እራሴን በራሴ ሳላረካ እንቅልፍ እስካይወስደኝ ድረስ ተጠናወተኝ፤ ይህም ለብዙ አመታት የለት ተዕለት ተግባሬ ሆነ፡፡ ሁሌ ይህንን ድርጊት ስፈፅም የጥፋተኝነት ሰሜት ይሰማኝ እና ሁለተኛ አልደግመውም ብዬ ማላከብረውን ቃል ለእግዚአብሔር እገባለታለሁ፡፡ እውነት ለመናገር ግን ይህንን ማቆምበት የምችልበት ምንም አቅም አልነበረኝም፡፡

ሰዎች ይህንን ቢያውቁ ስለእኔ ምን ያስባሉ የሚለው ሁሌ ያስፈራኛል፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎት ሲስፋፋ እኔ በሀያዎቹ መጀመሪያ እድሜ ላይ ነበርኩኝ፡፡ በኢንተርኔት ምክንያት ሁሉም አይነት ፖርኖግራፊዎችን ለማግኘት በጣም ቀላል ሆነ፡፡ በቀላሉ ሁሉንም አይነት ፖርኖግራፊ ማለትም ምስል፣ ቪዲዩ፣ ሙዚቃ ሁሉንም በትንሿ ስልኬ ማየት ጀመርኩኝ፡፡ ይህንን ተግባር ለማቆም ሁልጊዜ ለራሴ ቃል ብገባም አንድም ቀን ተሳክቶልኝ አያውቅም፡፡ መቋቋም ከምችለው በላይ ይሆንብኛል፡፡ ይህ የህይወት ኡደት፡ ፖርኖግራፊ ማየት፣ እራስን በራስ ማርካት፣ ከዛ መፀፀት ፣ ከዛ ድጋሚ ላለማድረግ ቃል መግባት ከዛ፣ ከዛ ደግሞ ማየት…..ይህ ከህይወቴ መቼ እንደሚቆም አላውቅም፡፡ በውጪ ለሚያየኝ በጣም ጥሩ ሰው ነው የምመስለው እንደውም በማመልክበት የሀይማኖት ተቋም መሪ ነበርኩኝ፡፡ ነገር ግን በውስጤ ያለውን ጨለማ የማውቀው እኔ ብቻ ነበርኩኝ፡፡ ሰዎች ይህንን ቢያውቁ ስለእኔ ምን ያስባሉ የሚለው ሁሌ ያስፈራኛል፡፡ ሚስት ባገባ ይህ ችግሬ ይፈታል ብዬ አስቤ ነበር፤ አገባሁ ነገር ግን የፖርኖግራፊ እና እራሴን በራሴ የማርካት ሱሴ በጋብቻ ውስጥ ሆኜም ቀጥሎ ነበር፡፡

የመጀመሪያው ትክክለኛው ነፃ የመውጣቴ አንድ ብሎ የጀመረው ፖርግራፊ ስለወሲብ ወይም ስለውበት ወይም ተፈጥሮ አለመሆኑን በተረዳሁኝ ቀን ነበር፡፡ በእርግጥ ፖርኖግራፊን ማየት የምፈልገው እራሴን መቆጣጠር እስካልችል ድረስ ቆንጆ የሆነች ሴት ስለማገኝ አይደለም ነገር ግን ሁሉም የራሴ ችግር ነው፡፡ ተቀባይነት፣ ተደናቂነትን፣ ፍቅርን እና ስልጣንን ለማግኘት ካለኝ ረሃብ የተነሳ ነው፡፡ የምጓጓበት ትክክለኛ ምክንያት ፖርኖግራፊ አለማችን ስለእኔ ማየት ያልቻለችውን አማላይነቴን ማየት ባትችልም እነዛ በፖርኖግራፊው አለም ያሉ ውብ ሴቶች ግን በፈጠርኩት የምናብ አለም በውበቴ ማልለው እጅግ ያፈቅሩኛል፡፡ ፖርኖግራፊ የጭንቅላቴ እና የልቤ ልምምዴ ውጤት ስለሆነ ከዚህ ሱስ መላቀቅ ካለብኝ መጀመሪያ መበጠስ ያለበት አስተሳሰቤ ነው፡፡ የፖርኖግራፊ ባሪያነቴን ለማስቆም ለራሴ የምነግራቸውን ውሸቶች በእውነት በመተካት በእውቀት ነፃ ለመውጣት መታገል ጀመርኩኝ፡፡

ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይህንን ሱስ ሰብሬ እንድወጣ የረዳኝ ባለቤቴ ለእኔ ያላት ፍቅር ነበር፡፡

ፖርኖግራፊን አሸንፌ እንድወጣ ከረዱኝ ነገሮች ውስጥ ወሳኙ መልካም ጓደኞቼ ነበሩ፡፡ ላምናቸው የምችላቸው ጓደኞች ነበሩኝ፤ ሁሉንም ነገር የማካፍላቸው ጓደኞች፤ ተመሳሳይ ጥፋት ለአንድ ሺህኛ ጊዜ ባጠፋ እንኳን ለእኔ መፀለይ ያላቆሙ ጓደኞች ነበሩኝ፡፡ በፖርኖግራፊ እና ዝሙት ላይ የተቀናጀሁት የመጨረሻው ድሌ የተከሰተውን ሁሉ፤ የቀድሞውንም የአሁኑንም ትግሌን ለምርጧ ጓደኛዬ ለውዷ ባለቤቴ በነገርኳት ቀን ነበር፡፡ ሁሉንም ስነግራት በድጋሚ በዚህ ነገር ከወደኩኝ ጭምር እንደምነግራት ነበር የነገርኳት፡፡ ምንም ሳላስቀር ሁሉም ነገርኳት፡፡ በጣም የምትናደድ እና የምትቆጣ መስሎኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሆነው ሁሉ ግራ መጋባቴ ነበር በጣም ያሳዘናት እና ከጎኔ ለመቆም፣ ልትረዳኝ እና ልትፀልይልኝ ቃል ገባችልኝ፡፡ ለእርሷ ከተናዘዝኩ ጊዜ ጀምሮ ግን ፖርኖረግራፊ በእኔ ላይ የነበረው ሀይል በተለያየ መንገድ ተሰብሮ ነበር እና ባለቤቴ ለእኔ ያላት ታላቅ ፍቅር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይህንን ልምምድ ሰብሬ እድወጣ አገዘኝ፡፡ ከዛ በኃላ ምንም አልደብቅም እናም ለእርሷ ታመኝ ሳልሆን መቀጠል አልፈለኩም፡፡ (በምናብ አለሜም ቢሆን)

ምንም እንኳን ለአመታት በፖርኖግራፊ ብሰቃይም አሁን ነፃ ነኝ ብዬ መናገር በመቻሌ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ፖርኖግራፊ በአለም ላይ ያሉ ጥሩ ነገሮችን ይዞ እንደሚመጣ ቃል የሚገባ ቢሆንም የሚሰጠን ግን የተጨማለቀ ህይወት ብቻ ነው፡፡ ይህ ነፃ መውጣት ግን በአንድ ለሊት የሆነ ነገር አይደለም፡፡ ከአስር አመት በላይ በፈጀ የለውጥ ሂደት የመጣ ነው፡፡

ያ ሁሉ ትግል አልፎ እኔ አሁን ነፃ እና ደስታ ነኝ፡፡ እናንተም ይህንን የነፃነት መንገድ እንድትጀምሩ እጋብዛችሀለሁ፡፡

ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡

Pornography (ፓርኖግራፊ) = የወሲብ ምስል እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ምስል ማለት ነው።
#ሀሳብ_አስተያየታችሁን_ፃፉልን።

@Men_lerdawo_Bot
@Men_lerdawo_Bot

ለመተንፈስ
ከሱስ ለመውጣት
ታሪክ ለማጋራት

እርዳታ ከፈለጉ

@Men_lerdawo_Bot

ሚስጥርዎ 100% የተጠበቀ ነው።

>>Click here to continue<<

ፀረ ዝሙት

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)