TG Telegram Group & Channel
ፀረ ዝሙት | United States America (US)
Create: Update:

ከአንድ ወዳጄ የተላከልኝ ትምህርት አዘል ፅሁፍ ነው። ሀይማኖትን መሠረት ያደረገ ትምህርት ነው ለሁላችንም ይጠቅመናል በማለት ልለቅላችሁ ወድጃለሁ...!

ሥርዐት አልባ ሩካቤ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?

/በሩካቤ ወቅት የማይፈጸሙ ድርጊቶች/

/ይህን ጽሑፍ ስታነቡ ‹‹ወይ ቄሱ ጉድ ነው›› እያላችሁ በመገረም ሳይሆን እራስን ከማረም እና ትውልድን ከማዳንና ሥርዓትን ከማሳወቅ አንጻር ተገንዝባችሁ አንብቡ፡፡ ነገሮችን በመንፈሳዊ ጨዋነት በግልጽ ባለማስተማራችን ዛሬ ዋጋ እያስከፈለን ነው/

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ትውልድና ይታደጉ ሥርዓትን አሳውቁ

ተወዳጆች ሆይ መንፈሳዊ ሰው ማንኛውንም ነገር ሥርዐትና አግባብ ባለው መልኩ ነው የሚከውነው፡፡ ሥርዐቱም በራስ ላይ ቀንበር ከመጫን አንጻር ሳይሆን ከመንፈሳዊ ሥነ-ምግባር ውጤት አንጻር ነው፡ ስለዚህ መንፈሳዊ ሰው እንኳን ለከበረው ለሩካቤ ሥጋ ቀርቶ ለአለባበሱ፣ ለአመጋገቡ፣ ለአነጋገሩ ሥርዐትና መንፈሳዊ መልክ ይኖረዋል፡፡

በተለይ ምንም መንፈሳዊ ብንሆንም በዘመናዊው ዓለም በመኖራችን የሩካቤ ሥጋ አፈጻጸም መልክና ይዘቱም እየተቀየረ ለሥጋ እርካታም እየተባለ ዘመን አመጣሹንና የምዕራባውያንን ሥርዐት አልበኝነትን በመመልከትና በመከተል እንዲሁም የዘመንን እየመሰለን ሩካቤ ሥጋችን ሥርዐት አጥቷል፡፡ ሩካቤን ሥርዐት ባለው መልኩ መፈጸም ማለት ለተጣማሪያችን ክብራችንን የመግለጽ ሒደት ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ በዓለማዊ እሳቤ ማኅበረሰብን ለማነጽ ሳይሆን ገንዘብን ለማግኘት ሲባል የታተሙት ወሲብ ነክ መጻሕፍት የሰውን ቀልብ እየገዙ፣ ትውልድን እያደነዘዙ ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በብዙ የሚቆጠሩ የሩካቤ አፈጻጸም ዓይነቶችን በመያዛቸው፣ የተፈቀደና ያልተፈቀደን ባለመለየታቸው፣ ሰዉ ግራ እየተጋባ ያልለመደውንና ያላወቀውን የሩካቤ ዓይነት እንዲያውቅና እንዲተገብር እየተገደደ ስለሆነ የዚህ ገዳፋ ለመንፈሳዊያንም እንዳይተርፍ፣ ከተረፈም ሕጋዊ ያልሆነውን ለማሳወቅ እና ሕጋዊውን ለማስጠበቅ ስንል እንመለከታለን፡፡

ሴቶች በተለይም በወንዶች አላስፈላጊ ፍላጐት ሩካቤው በማፈንገጡ የአፈጻጸም ሥርዐቱ ወጣ በማለቱ ሩካቤ ሥጋ ክብሩንና ንጽሕናውን እንዳያጣ፣ እንደ እንስሳም እንዳንሆን ከመንፈሳዊነት አንጻር እንዴትና በምን መልኩ መፈጸም አለብን የሚለውን ዘርዘር አድርገን እናያለን፡፡ በተለይ በአልጋ የምንፈጽመው እግዚአብሔር ስለሚያየው ራሳችንን ከማስተካከልና አዲስ ተጋቢዎችን ሥርዐተ ሩካቤን ከማሳወቅ አንጻር ያለ ምንተ እፍረት አቀርበዋለሁ፡፡ ምክንያቱም እኛ ካህናት በተለይ ለወጣት ንስሐ ስንሰጥ ደጋግመን የምንሰማው አንዱ ይህ ያፈነገጠ ተራክቦ ነውና፡፡

ሥርዐት አልባ ሩካቤ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?
/በሩካቤ ወቅት የማይፈጸሙ ድርጊቶች/

1/ በኋላ የሚፈጸም ሩካቤ፦ ሩካቤን በኋላ በኩል መፈጸም እንስሳነት ከመሆኑ ባሻገር ለተጣማሪ ክብርን ሳይሆን ውርደትና ንቀትን የምንገልጽበት ነው፡፡ ሰውን እንደ አንስሳ አድርጐ ሩካቤ የመፈጸም መንፈሳዊ ሥርዐት አልበኝነት ከመሆኑም ባሻገር ከእግዚአብሔር ዘንድም ቁጣን ያመጣል፣ ያልተባረከ ትውልድን ይፈጥራል፡፡ እንስሳት በኋላ በኩል የሚፈጽሙት አራት እግር ስላላቸውና ተፈጥሮአቸው በኋላ በኩል ስለሚያመቻቸው ነው፡፡ እኛ የሰው ልጆች ሩካቤ ሥጋን በኋላ በኩል ፈጸምን ማለት ባለ ሁለት እግር እንስሳት ሆንን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ተግባር ጸያፍ ስለሆነ ልንፈጽመው ሳይሆን ልናስበው አይገባም፡፡

2/ በቁም የሚፈጸም ሩካቤ ፦ የሰው ልጅ ብዙ ነገሮችን ከተፈጥሮ፣ ከእንስሳት ከአዕዋፋት፣ ከዱር አራዊት ወዘተ የተማራቸው፣ በሕይወቱ የተገበራቸው መልካም ነገሮች ቢኖሩትም እንደ ሩካቤ ያሉትን ማለትም ሩካቤን ቆሞ መፈጸምን ከእንስሳት የተመለከተው ሥርዐት አልባ ሩካቤ ነው፡፡ እንስሳት ሩካቤን በቁም የሚፈጽሙት ተፈጥሮአቸው ተኝተው መፈጸም ስለማያስችላቸው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ሩካቤን በቁም ስለመፈጸም የተጻፈበት ቦታ የለም፡፡ ይህ ሥርዐት አልባ ወረርሽን ምዕራባውያን እንደ ሸቀጥ በየፊልሙና በማኅበራዊ ድረ ገጽ እያስተማሩን ከተፈጥሮ እንድናፈነግጥ ያደረጉት ነው፡፡ የሰውና የእንስሳን የሩካቤን ሥርዐት በውልደታቸው ብናይ መልካም ነው፡፡ ሰው እንደ ተወለደ መቆም አይችልም፡፡ እንስሳት አንደ ተወለዱ መተኛት ሳይሆን ከደቂቃዎች በኋላ መቆም ይጀምራሉ፡፡ ይህ ተፈጥሮአቸው ሩካቤያቸውንም ያሳየናል፡፡ እንስሳት ሩካቤያቸው በቁም ስለሆነ ሲወለዱ መቆም ይጀምራሉ፡፡ ሰዎች ሩካቤያቸው ተኝተው ስለሆነ ሲወለዱ ወድያው መቆም ሳይሆን ለወራት ይተኛሉ፡፡ ይህ የተፈጥሮ ሥርዐታቸው ሩካቤያቸውን ያሳየናል፡፡ ስለዚህ ተፈጥሮአችን ባልሆነ መንገድ ሩካቤን መፈጸም ትርፉ እርግማንን የራስ ለማድረግ ማሳደድ እና የእርግማንን ትውልድ መውለድ ነው፡፡

እግዚአብሔር ከአዳም አንዲት አጥንት ክብርት ሔዋንን ሲፈጥራት አዳምን አቁሞት ሳይሆን በክቡድ እንቅልፍ አስተኝቶት ነው፡፡ የእርሷም መፈጠር ከቆመ ሰውነት ሳይሆን መሬት ከተኛው አዳም መገኘቷ ወደ ፊት ሥርዐተ ሩካቤያቸው በመቆም ሳይሆን በመተኛት የሚፈጸም መሆኑን እንደ ሥርዐት ጭምር ሊሠራላቸው መሆኑን ሊያሳውቃቸው ፈልጐ ነው፡፡ ስለዚህ ሩካቤን በቁም መፈጸም ማለት ከእንስሳ ጋር በጸያፍ ምግባር መወዳጀት ስለሚሆን በሥርዐት መፈጸሙ መባረክን ያተርፋል፡፡

3/ ልቅ ወሲብ ፦ መቼም ልቅ ወሲብ ብዬ ስጽፍ አንባቢዎቼ ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ በተለይ በፊልሞች የታዩትን፣ በልብ ወለድ የተነበቡትን፣ ከሰው የሰሙትን ሁሉ በትዳር ለመሞከር ከዛም ባለፈ መፈጸም እንስሳ መሆንና ከእንስሳም ማነስ ነው፡፡ በየትኛውም መንገድ ሩካቤያችን መንፈሳዊ ጨዋነትን የተላበሰ፣ የተፈጥሮ ሥርዓታችንን ያልጣሰ መሆን አለበት፡፡ ልቅ ወሲብን በትዳር ሕይወት ለመፈጸም መሞከር የከበረውን፣ የተቀደሰውን ሩካቤ ሥጋ መናቅና ማቃለል ነው፡፡ ስለዚህ በትዳራችን ልቅ ወሲብ በመፈጸም እግዚአብሔርን ብናስቆጣው እግዚአብሔር በቀጥታ ባይቀጣንም በልጅ ሊቀጣን ይችላል፡፡ ይህም የልቅ ወሲብ ተግባራችን፣ውጤታችን የሆኑ ልቅ እና ልብ አውልቅ እንዲሁም ጤናቸው፣ተፈጥሯቸው የተዛባ ልጆች ሊሰጠን ይችላል፡፡ እርግማንን በሚያመጣ ልቅ ወሲብ ተፀንሰው የሚወለዱት ልጆች ደዌ የያዛቸው፣በሽታ የተጫናቸው እና አጋንንት የተጣባቸው ልጆች ሊሆኑ ስለሚችሉ ለራሳችንና ለሚወለዱት ልጆች ስንል ሩካቤ ሥጋችን ሥርዐት ሊኖረው ይገባል፡፡

4/ በአፍ የሚፈጸም /Oral Sex/ ፦ ይህ ለመንፈሳዊ ሰው ብቻ ሳይሆን ሰው ለተባለው ሁሉ ጸያፍ ተግባር ነው፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የከበረው አፍ ጸያፍ ተግባር መፈጸምያ መሆን የለበትም፡፡ ይህ ጸያፍ ተግባር ከሃይማኖት ብቻ ሳይሆን ከባሕልና ከትውፊት አንጻር አስነዋሪ ተግባር ነው፡፡ በተለይም የሴትን ልጅ ክብር የሚያጐድፍ ነው፡፡ አንዳንዶች በተለይ ወንዶች ከስንፈት ጋር በተያያዘ ኃፍረታቸው ለተረክቦ ዝግጁ ባለመሆኑ ለማነቃቂያነት፣ ስሜትን ለመቀስቀስ እንደዚህ ዓይነት ኢ-ሩካቤ መንገድን ይጠቀማሉ፡፡

ሌሎችም እርግዝናን ለመከላከልና እላፊና አስከፊ ደስታን ለማግኘት ሲሉ የስሜታቸውን ፍጻሜ በአፍ ወሲብ ለማግኘት ይሞክራሉ፡፡ እንኳን ለኃፍረታችን በቤታችን ያለው ድስት የራሱ የሆነ ግጣም አለው፡፡ እኛም ኃፍረታችንን ያለ ግጣሙ፣ እርስ በእርስ በማይስማሙ ቦታ ደስታ ለማግኘት መጣር፣ በራስ ላይ እርግማንን መከመር ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸ

>>Click here to continue<<

ፀረ ዝሙት

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)