TG Telegram Group Link
Channel: ርጢን ሚዲያ ( Ritin Media )
Back to Bottom
✝️✝️ እንኩዋን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝️✝️

✝️✝️ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ✝️✝️

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በዚህች ቀን ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል::

+ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል::
+ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው::

+ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
*በቤተ መቅደስ ብስራቱን
*በቤተ ልሔም ልደቱን
*በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
*በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
*በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

+በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*6 ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

=>የተክለ ሃይማኖት አምላክ ከጻድቁ ትሩፋት: ጸጋና በረከት ይክፈለን::

† አባ ይስሀቅ †

በዚች ቀን ከግብፅ ደቡብ ከእብክ አውራጃ ከሆሪን ከተማ የከበረ አባት ይስሀቅ አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሀም የእናቱም ስም ሶስና ነው ታናሽም ሆኖ ሳለ እናቱ ሙታ ብቻውን ያለእናት አባቱ እያሳደገው ኖረ።

ጥቂት በአደገም ጊዜ የአባቱን በጎች የሚጠብቅ ሆነ አባቱም ሌላ ሚስት አገባ በዚያ ወራትም ታላቅ ረኃብ ሆነ የአባቱም ሚስት ትጠላው ነበረ ከጥቂትም በቀር እንጀራ አትሰጠውም ያንኑም ሁልጊዜ ለእረኞች ሰጥቶ እርሱ ግን እስከምሽት ይፈፀማል።

ምሳውን ለእረኞች እንደሚሰጥና ሁልጊዜ እስከምሽት እንደሚፆም አባቱ ሰምቶ እውነት እንደሆነ ሊያይ ወደርሱ ሄደ። ቅድሱም ህፃን የአባቱን መምጣት አውቆ በልብሱ ሶስት ጭቃ አድበልብሎ አሰረ እንደ ታሰረ በሚያየው ጊዜ ለአባቱ አምባሻ እንዲመስለው ብሎ።

አባቱም በመጣ ጊዜ የልጁን ልብስ ፈትቶ አየ አንባሻም ሆነው አገኛቸው።የነገረውንም ሰው ምግቡን ለእረኞች ከሰጠ በዛሬይቱ ቀን ይህ አምባሻ ከወዴት ተገኘለት ብሎ ጠየቀው እርሱም በእውነት ሰጥቷል አለ ሌሎችም ብዙዎች መጥተው በዚህ ነገር ምስክሮች ሆኑ አባቱም አደነቀ እግዚአብሄርንም አመሰገነ።

ይህም በአደገ ጊዜ አባ ኤልያስ ወደሚባል ሰው ሄዶ መንኩሶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ አመታት ኖረ። አባ ኤልያስም በአረፈ ጊዜ በርኑግ ወደሚባል ገዳም ሄደ ስሙ ዘካርያስ ከሚባል አረጋዊ ዘንድ በታላቅ ገድል ተጠምዶ ኖረ።

አባቱም ያገኘው ዘንድ በሀገሮች ሁሉ ይዞር ነበረ በዚህ በበርኑግ ገዳምም በአገኘው ጊዜ ከእርሱ ጋራ እንዲመለስ አባቱ ለመነው አይሆንም አለ አባ ዘካርያስም ከአባቱ ጋራ ይሄድ ዘንድ እስከ ሚአርፍም ከእርሱ ዘንድ እንዲኖር አዘዘው ይህ ቅዱስም ከአባቱ ጋራ ሄዶ እስከሚአርፍ ድረስ ከእርሱ ዘንድ ኖረ።

አባቱም በአረፈ ጊዜ አባቱ የተወውን ገንዘብ ሁሉንም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ ከከተማውም ጥቂት ራቅ ብሎ ለራሱ ታናሽ ማደሪያ ሰራ በሰላም እሰከ ሚአርፍባት ቀን ድረስ ያለ ማቋረጥ በበጎ ገድል በፆም በፀሎት በስግደት ኖረ በአረፈ ጊዜም በመልካም ቦታ አኖሩት ከዚያም ተሰወረ።

ከብዙ ዘመናትም በኃላ እግዚአብሔር ሊገልጠው ወዶ በመቃብሩ ላይ መብራት ሲበራ እህል ለሚአጭዱ ሰዎች ሶስት ቀን ያህል ታየ ሊያዩትም ወደቦታው ሲደርሱ ያ መብራት ከእርሳቸው ይሰወራል በሁሉ ዘንድ እስቲሰማም እንዲህ ሆኖ ኖረ።

ከዚህም በኃላ በመቃብሩ ላይ እያበራ ያ መብራት ደግሞ ታያቸው ስጋውም በዚያ እንዳለ ሁለተኛ በህልም ነገራቸው ምእመናንም አክብረው በግመል ጭነው ወደ ሀገሩ መካከል ወደ ሆሪን ወሰዱት ነስሪን ከሚባል ሀገር መካከል ሲደርሱ ግመሉ በዚያ ተንበረከከ እንዲነሳም መቱት መነሳትንም እቢ አለ መኖሪያው በዚያ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አወቁ።

በዚያም በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሰርተው ስጋውን በውስጥዋ አኖሩ ሰርተው ስጋውን በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።

† ቅዱስ እለእስክንድሮስ †

በዚች ቀን የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳትም አስራ ዘጠነኛ የሆነ እለእስክንድሮስ አረፈ። ስለርሱም ሀዋርያዊ አባት አትናቴዎስ እንዲህ አለ አባቴ እለእስክንድሮስ ተቀምጦ ወንጌልን አያነብም ቁሞ ያነባል እንጂ ከርሱ ጋራም ብርሀን አለ።

ሁለተኛው ስለርሱ ሲናገር ወደርሱ እመምኔቶች መጥተው በእኛ ዘንድ ሰባት ሰባት ቀን የሚሶሙ ደናግል አሉ ።በእጆቻቸውም ምንም ምን ስራ አይሰሩም ብለው ነገሩት።

እርሱም እህቶቼ ሆይ እኔ ሁለት ቀን እንኳን ከቶ አልፆምኩም ፀሀይ እስኪገባው ቆይቼ አልበላሁም በልክ እበላለሁ በልክም እፆማለሁ በልክ በመጠንም እሰራለሁ በልክ ይበሉ ዘንድ በልክም ይፆሙ ዘንድ በልክም ስራ ይሰሩ ዘንድ ነግሯቸው በበጎ ስራ ሁሉ ይሰለፉ አለ።

የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ደጎች ምእመናን ናቸው እርሱም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ሆኖ ከታናሽነቱ ጀምሮ በውስጥዋ አደገ።አባ መክሲሞስ አናጒን ስጢስነት አባ ቴዎናስ ዲቁና ተፍፃሜተ ሰማእት ጴጥሮስም ቅስና ሹመውታልና እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ንፅህ ድንግል ነው።

አባ ጴጥሮስ በሰማእትነት የሚሞትበት ጊዜ ሲቀርብ በግዞት ቤት ሳለ ይህ እለእስክንድሮስና አኪላስ ከውግዘቱ ይፈታው ዘንድ ስለ አርዮስ ወደርሱ ገብተው ለመኑት ስለርሱ አባ ጴጥሮስን ይማልዱለት ዘንድ ሁለቱን ለምኖአቸዋልና።

አባት ጴጥሮስ ግን በውግዘት ላይ ውግዘትን ጨመረበት እንዲህም ብሎ ነገራቸው የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀደደ ልብስ ለብሶ ተገለፀልኝ ልብሴን አርዮስ ቀደዳት አለኝ። ይህም የባህርይ አንድነቴን ለያት ማለት ነው ውግዘቱንም እንድጨምርበት እርሱ አዘዘኝ።

ደግሞ እንዲህ ገለጠላቸው አኪላስ ሊቀ ጵጵስና እንዲሾም ከርሱ በኃላም እለእስክንድሮስ እንደሚሾም አርዮስን እንዳይቀበሉት በምንም ስራው እንዳይተባበሩት አዘዛቸው።

አባ ጴጥሮስም ምስክርነቱን በፈፀመ ጊዜ አኪላስ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ የአባት ጴጥሮስንም ትእዛዝ ተላልፎ አርዮስን ከውግዘቱ ፈታው። ቅስናም ሾመው ስለዚህም አኪላስ በመንበረ ሲመቱ ያለ ስድስት ወር አልኖረም በድንገት ሞተ።

ከዚህ በኃላ ይህ አባት እለእስክንድሮስ ሊቀ ጵጵስና ተሹሞ በመንበረ ሲመቱ ላይ ተቀመጠ አርዮስንም ከወገኖቹ ጋራ አውግዞ አሳደደው። የሀገር ታላላቆችም ከህዝቡ መጡ ከውግዘቱ እንዲፈታውም ለመኑት። በውግዘት ላይ ውግዘትን እንዲጨምር እንጂ እንዳይፈታው አባት ጴጥሮስ እንደአዘዘው ነገራቸው።

ከዚህ በኃላ አርዮስ ወደ ንጉስ ቈስጠንጢኖስ ሂዶ በግፍ አወገዘኝ ብሎ እለእስክንድሮስን ከሰሰው። ስለዚህም ንጉሱ ሶስት መቶ አስራ ስምንት የከበሩ አባቶችን በኒቅያ ከተማ ሰበሰበ።
ይህም አባት እለእስክንድሮስ ተመርጦ ለጉባኤው ሊቀ መንበር ሆነ አትናቴዎስ ፀሀፊ ነበር ።አርዮስንም ተከራክረው ክህደቱን ግልፅ አደረጉ ስለ ጌታ

ችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከአባቱ ከአብ ጋራ ከህይወቱ መንፈስ ቅዱስም ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ አስረዱት።

ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው ከቤተ ክርስቲያን አሳደዱት። በአንድ ቃልም ፀሎተ ሀይማኖትን ከአባቶች ጋራ ሰሩልን ደግሞ በእርሳቸው ቤተ ክርስቲያን ለዘላለም የምትመራባቸው ሀያ ቀኖናን ሰርተው ወሰኑ።

ከዚህ በኃላም ይህ አባት እለእስክንድሮስ ወደ መንበረ ሲመቱ ከደል ጋራ ተመለሰ። በበጎ አጠባበቅም መንጋውን ጠበቀ በወንጌላዊ ማርቆስ መንበርም አስራ ሰባት አመት ኖሮ በሰላም አረፈ።

† አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ †

በዚችም ቀን የከበረ አባት አባ ሚካኤል የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሀምሳ ሶስተኛ ነው። ይህም ቅዱስ ፃድቅ መንኲሶ በአስቄጥስ በቅዱስ ዮሀንስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሾመ ከዚያም ያለ ፈቃዱ ወስደው በግድ ሊቀ ጵጵስና በእስክንድርያ አገር ላይ ኀዳር ሀያ አራት ቀን ሾሙት።

በሊቀ ጵጵስናውም ስራ ተጠምዶ የሚጋደል ሆነ እንደ ሀዋርያትም አጠባበቅ መንጋውን ጠበቀ። ታላቁ ፆምም በደረሰ ጊዜ ወደ አስቄጥስ በዚያ ሊፆም ወጣ ከመሾሙ በፊት በዚያ ገዳም ውስጥ በብህትውና ሆኖ መጠመዱንና የቀድሞ መጋደሉን አሰበ።

ወደ ጌታችንም እንዲህ ብሎ ለመነ አቤቱ እኔ በብቸኛነት መኖርን እንደምሻ አንተ ታውቃለህ ለዚች ለተሾምኩባትም ሹመት ችሎታ የለኝምና የምትገባኝም አይደለችምና በይቅርታህም ብዛት ነፍሴን ወስደህ ከዚህ ድካም ታሳርፈኝ ዘንድ እለምንሀለሁ ጌታም ልመናውን ተቀበለ ከፋሲካ በአል በኃላም በፍቅር አንድነት አረፈ።የሹመቱም ዘመን ሁለት አመት ከአምስት ወር ነው።

=>ሚያዝያ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (አርዮስን ያወገዘ)
3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
4.አባ ማርቆስ ሐዲስ
5.አባ ሚካኤል ዘኢየሩሳሌም
6.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
5.አባ ዻውሊ የዋህ

=>+"+ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት:: የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር:: ሱራፌል ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር:: ለእያንዳንዱ ስድስት ክንፍ ነበረው:: በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር:: በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር:: በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር:: አንዱም ለአንዱ 'ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች' እያለ ይጮህ ነበር:: +"+ (ኢሳ. 6:1-4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ዕለተ ሠሉስ /ማክሰኞ/

ይህ ቀን ጌታችን ሰኞ በተናገረውና ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ ጥያቄውም ጌታ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት ለጸሐፍትና ፈሪሳውያን ይኸውም ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?» የሚል ነበር፡፡ /ማቴ.21-23-27/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ «ወይቤሎሙ ኢየሱስ አማን እብለክሙ ከመ መጸብሓውያን ወዘማውያት ይቀድሙክሙ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር»፤ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው እውነት እላችኋለሁ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል ሲል አስተምሯል፡፡ /ማቴ.21-28/
ጸሎተ ሐሙስ!

ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ምሥጢረ ቊርባንን ከምሥጢረ ጸሎት ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡

በወንጌልም እንደተጻፈው ፋሲካውን የሚያከብሩበት ቀን ሲደርስ ጌታ ኢየሱስም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሒዳችሁ ፋሲካን እንበላ ዘንድ አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም በየት እንድናዘጋጅልህ ትወዳለህ አሉት? ወደ ከተማ ገብታችሁ የውኃ ማድጋ የሚሸከም ስምዖን የተባለ ሰው ታገኛላችሁ፤ ወደ ገባበት ቤት እርሱን ተከተሉት፤ መምህር ከደቀ መዛሙርቶቼ ጋር ፋሲካ የሚያደርግበት አዳራሽ ወዴት ነው ይልሃል? በሉት እርሱ የተነጠፈውንና ታላቁን አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያም ፋሲካን አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም ወደ ተላኩበት ከተማ ገብተው አልዓዛርን የውኃ ማድጋ ተሸክሞ አገኙት፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ለስምዖን ጌታ በቤቱ ፋሲካን ሊያዘጋጅ መሻቱ እንደሆነ ነገሩት፤ እርሱም የፍጥረታት ጌታ በቤቱ ሊመጣ እንዳለ አስቦ ተደሰተ፤ ወደ ሚስቱ አክሮሲናም ሔዶ ይህ አልዓዛርን ከሞት ያስነሳ እኔንም በኃጢአቴ ይቅር ይለኛል፤ ያነጻኝ ዘንድ ከሐዋርያት ጋር በቤታችን ይመጣል አላት፤ አክሮሲናም እጅግ ተደሰተች፡፡
ጌታችንም ጊዜው ሲደርስ ከሐዋርያት ጋር በአንድነት መጣ፤ ስምዖንም ከቤቱ ወጥቶ ሮጦ ከጌታ እግር ሥር ሰገደ፤ ወደ ቤቱም ከሐዋርያት ጋር አስገባቸው፡፡ ይሁዳ ግን ይህን ሰዓት አልነበረም፤ ውጪ ከሻጭና ለዋጭ ጋር ገንዘብ ሲደራደር ነበር፤ ስምዖንም ለሚስቱ አክሮሲና ጌታና ሐዋርያት የሚገቡበት በእግራቸው የሚረግጡት ምንጣፍ እንድታነጥፍ አዘዛት፡፡ አክሮሲና ግን የጌታን መልክ አታውቀውም ነበር፤ ያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ጸሎት ሲጸልዩ አይታ ‹‹ከእናንተ ውስጥ መምህሩ ማነው›› አለቻቸው፤እነርሱም ዝም አሉ፤ መልከ መልካም ወደ ሆነውና የጌታ ወዳጅ ወደሆነው ዮሐንስ ተመልክታ እርሱ ይሆን አለች፤ ጴጥሮስ ግን ቀበል አድርጎ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ከውስጠኛው ክፍል ቆሞ ይጸልያል፤ ጌታ እርሱ ነው›› አላት፡፡ እርሷም ገብታ ሰገደችለት፤ ይሁዳም በመጨረሻ ሳጥን ተሸክሞ መጣ፤ ጠባቂውንም እኔ የጌታ ደቀ መዝሙር ነኝ አለው፡፡ በር ጠባቂውም እለእስክንድሮስም የተነጠፈውን እስካጥፍ ጠብቅ ብሎ ዘለፈው፤ ልብሱንም አንስቶ አስገባው፤ /ግብረ ሕማማት ፭፻፹፫-፫፻፹፭/፡፡

በአንደኛው ሰዓት ሌሊት (ሐሙስ ለአርብ ምሽት)፤

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልብሱን አኖረ፤ማበሻ ጨርቅም አንስቶ ወገቡን ታጠቀ፤ ይህችውም ሥራ የምታሠራና የምታስጌጥ ናት፤ ለዛሬው የመነኮሳት መታጠቂያ አብነት ናት፡፡ ለምሳሌ፡- ኢዮአብ ወደ ሰልፍ ሲገባ እየለበሳት ይገባ እንደነበረችው ያለ ዓይነት ነው፤ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጥብ ዘንድ በጴጥሮስ ጀመረ፤ ጴጥሮስ ግን እኔ ባንተ ልታጠብ አይገባኝም አለ፤ ጌታችንም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም›› (ዮሐ.፲፫፥፰)፡፡ ሌሎቹንም ሐዋርያት አጠባቸው፤ አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳንም እግሩን አጠበው፡፡ ጌታ አሳልፎ እንደሚሰጠው ሳያውቅ ቀርቶ አልነበረም፤ ፍቅርን ሲያስተምረውና ለንስሐ ጊዜ ሲሰጠው ነው እንጂ፤ እኛንም ለሚወደን ብቻ ሳይሆን ለሚጠላን እንኳን በጎ ማድረግ እንደሚገባ ሲያስተምረን ነው፡፡

ጌታችን ጾመና ጹሙ አለን፤ተጠመቀና ተጠመቁ አለን፤ ጸለየና ጸልዩ፤ ሰገደናም ስገዱ አለን፤ የሐዋርያትንም እግር አጥቦ እናንተም እንዲህ አድርጉ ብሎ መምህረ ትሕትናነቱን ገለጠልን፡፡ ዛሬም ከፓትርያርኩ ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፤ካህናት በየመአርጋቸው የምእመናኑን እግር በማጠብ የጌታን የትሕትና ሥራ ያስቡታል፡፡

ለሐዋርያት ትሕትናን ሲያስተምራቸው ጌታችን እግራቸውን እንደ አጠባቸው ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ከዚያም ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ ብሎ ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው፤ ዛሬም የልጅነት ጥምቀት የሚቀበሉ ምእመናን በዚያኑ ዕለት ከክርስትና ቤት ወደ ቤተ መቅደስ ሔደው የጌታን ክቡር ሥጋና ደም ይቀበላሉ፤ መሠረቱም ጌታችን ለሐዋርያት ያደረገውን ተመርኩዞ ነው፡፡ ከፍ ከፍ ሊል የሚወድ ራሱን ዝቅ ያድርግ ብሎም አስተምሯቸዋል፤ አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምሥጢር ጌታ ለጴጥሮስ ‹‹እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም›› ያለውን ሲተረጉሙ ‹‹እኔ በአገልጋይ አምሳል እግርህ ካላጠብኩህ አንተም ከበታችህ ላሉት ራስህን ዝቅ ለማድረግ አትችልም፤ ራስህን ዝቅ ዝቅ ካላደረግህ አለቃ ልትሆን አትችልም›› ለማለት ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡ ጌታችን ደግሞ አምላክ ፈጣሪ መምህር ሳለ ዝቅ ብሎ እንዳጠባቸው እነርሱም ክህነታቸውንና መምህርነታቸውን በትሕትና እንዲጀምሩ ሲያስተምራቸው ነው፡፡

በሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ምሽት፤

ጌታችን ሕብስቱን ባርኮ ለዐሥራ ሦስት ፈትቶ ሰጣቸው፤ ዐሥራ ሦስተኛውን እርሱ የሚቀበለው ነውና ነገር ግን የሚረባውና የሚጠቅመው አይደለም፤ ‹‹ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ›› ብሎ ሕብስቱን ባርኮ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ ›› ወይኑንም ባርኮ ‹‹ይህ ደሜ ነው እንካችሁ ጠጡ›› ብሎ ሰጣቸው፡፡አስራ ሦስት አድርጎ መፈተቱ ሐዋርያትን እንዳይገርማቸው (እንዳያስፈራቸው) ነው፤ እራሱም ጥዒሞ አጥዐሞሙ/ቀምሶ አቀመሳቸው/ እንዲል አብነት ለመሆን፤ አንድም ነገ በመልዕተ መስቀል አስራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል እቀበላለሁ ሲል ነው፤ ጌታ ይህን ባያደርግ ኖሮ ዛሬ ካህኑ የጌታን ሥጋና ደም ሳይቀበል አቀብሎ ብቻ በሄደ ነበርና ለእነርሱ ለማስተማር ነው፡፡

ማዕዱንም እየበሉ ጌታችንም ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ! ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል›› አላቸው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፩)፡፡ ሐዋርያት ሁሉ ደነገጡ! እርስ በርሳቸው ተያዩ፤‹‹እኔ እሆን? እኔ እሆን?›› ተባባሉ፤ ጴጥሮስም ዮሐንስን ጠጋ ብሎ ‹‹ማነው አሳልፎ የሚሰጠህ ብለህ ጌታን ጠይቀው›› አለው፤ወንጌላዊው ዮሐንስም ጌታን ጠጋ ብሎ ጠየቀው ጌታችንም ‹‹ከእኔ ጋር እጁን ከወጪቱ የሚያገባ እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል›› አለ፤ (ማቴ.፳፮፥፳፫/ሉቃ.፳፪፥፳፩)፡፡ ሐዋርያትም ‹‹ሁላችን ከወጪቱ የምንጠቅስ አይደለምን?›› ሲሉ ጌታችን ‹‹እኔ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው ነው›› አላቸው፤ ያንጊዜ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው፤ ስለዚህ ወንጌላውያኑ ይህን ታሪክ ይዘው አንድ ሳለ በተለያየ አገላለጥ ገለጡልን፡፡

ይሁዳም እንደቸኮለ ሰው ይቅበዘበዝ ነበር፤እርሱም ጌታን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጠው በልቡ እያሰበ ነበር፡፡ ጌታም ወደ ይሁዳ ጠጋ ብሎ ‹‹ወዳጄ ይሁዳ ሆይ! ልትሠራው የምትሻው ሥራ ካለ ሒድ›› አለው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፯)፤ ይሁዳም ፈጥኖ ወጥቶ ወደ አይሁዳውያን ጌታን አሳልፎ ሊሰጥ ዋጋ ሊነጋገር ሔደ፡፡

ከሦስተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ አምስተኛይቱ ሰዓተ ሌሊት ድረስ

ለደቀ መዛሙርቱ ሲመክራቸው የመንፈስ ቅዱስንም መምጣት አብዝቶ ሲነግራቸው፤ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቀና፤ እርሱ ከአባቱ ጋር አንድ እንደሆነም ነገራቸው፤ ለብቻው ፈቀቅ ብሎ ወዙ እንደ ደም እስኪፈስ እየሰገደ ጸለየ፤ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመለሰ፤ ተኝተው አገኛቸው፤ ቀሰቀሳቸው፤ ጴጥሮስንም አንድ ሰዓት ያህል እንኳን ከእኔ ጋር መትጋት አቃታችሁን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ አለው! (ሉቃ.፳፪፥፲፬-፵፮)፡፡

የጌታችን በአይሁድ መያዝ (ስድስተኛው ሰዓተ ሌሊት)

ጌታችንም ከአብ ጋር ስላለው አንድነትና ክብር ለሐዋርያት ካስተማራቸው በኋላ ‹‹ኢየሱስም ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ በዚያም ገባ›› (ዮሐ.፲፰፥፩)፡፡ወንዙን ተሻግሮ ያለውን ዛፍ አልፎ ወዳለው ዱር ገባ፡፡ ይሁዳም ይህችን ስፍራ ቀድሞ ጌታ ይመጣባት ስለነበር ያውቃት ነበርና ጭፍሮችንና የካህናት አለቆችን ፈሪሳውያን ሌሎች ፋና ጋሻ ጦርም የያዙትን አስከትሎ መጣ፡፡ ጌታችንም ‹‹ተነሡ እንሂድ! እነሆ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል›› አላቸው ወደ እነርሱ መጥቶ ቀረበ፤ ይሁዳም ወደርሱ ቀርቦ፤ ‹‹መምህር ሆይ ቸር ውለሃል፤ ሰላም ላንተ ይሁን›› ብሎ ሳመው፤ ይህ መሳም ለአይሁድ ጥቆማ ወይም ምልክት ነበር፡፡ ምክንያቱም የጌታ መልክና የወንጌላዊው የዮሐንስ መልክ ይመሳሰልባቸው ነበርና ሲለይላቸው ነው፤ ጌታችንም ‹‹በስኢምኑ ታገብኦ ለወልደ ዕጓለ እመሕያው፤ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጠዋለህን?›› አለው (ሉቃ.፳፪፥፵፰)፡፡
ይሁዳም ከጭፍሮቹ ጋር መጣ፤ ጌታ ኢየሱስንም ከበውት ወደ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ወሰዱት፤ ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ ይከተለው ነበር፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ከአንደኛው ቅጥር ግቢ ገብቶ ተቀመጠ፡፡ አይሁድም በክርስቶስ ላይ ሁለት የሐሰት ምስክሮችን አመጡ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስተኛው ቀን እሰራዋለሁ›› ብሏል ብለው ከሰሱት፤ ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ ‹‹እንዲህ ሲያጣሉህ አትሰማምን›› አለው፡፡ ጌታችን ግን ምንም አልመለሰለትም፤ሊቀ ካህናቱም ‹‹ክርስቶስ ተብሎ የተነገረልህ የእግዚብሔር ልጅ አንተ እንደሆንክ ንገረኝ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ አልክ›› አለው፤ ያን ጌዜ ሊቀ ካህናቱ ተናዶ ልብሱን ቀደደው፤ራሱንም በብረት ዘንግ መቱት፤ የስቃዩ ጅማሬ ይህን ጊዜ ነበር፡፡
#ምሴተ_ሐሙስ

☞የተቀደሰውን ስዕል ልብ ብላችሁ ተመልከቱት! (ቅዱስ #ጴጥሮስ የጌታን እግር እያጠበ ነው)

በቤተክርስቲያን ትውፊት ጌታ ደቀመዛሙርቱን በትህትና ካጠባቸው በኋላ፦

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጌታ ታጥቋት የነበረችውን "መክፌ" ተቀብሎ ታጥቋታል፤ በዚህ ከንጽሐ ጠባይእ ማዕረግ ደርሷል።

፪. አስቀድሞ "አልታጠብም" በሚል ተከራክሮ የነበረ ቅዱስ ጴጥሮስ (ፈጣሪነቱን ቢያስብ፥ ትህትናው ቢበዛበት) እሺ ብሎ ታጥቧል። ኋላም "ካልቀረስ እኔም ልጠብህ" ብሎ ጌታን ለምኖታል፡፡ ጌታም "እሺ" ብሎ ታጥቦለታል፡፡ ይህም ለቅዱስ ጴጥሮስ የክብር ክብር ሆኖለታል፡፡ (ለመኑ ተውህበ!)

በዚህ አብነትም በአድባራቱ ፥ በገዳማቱ ትልልቆቹ (ሊቃነ ጳጳሳት፡ ጳጳሳት፡ ኤጲስ ቆጶሳት፥ ቆሞሳት፡ አበምኔቶች፡ ገበዛዝቱ) አስቀድመው ያጥባሉ! ኋላ በፈንታው ካህናት ያጥቧቸዋል!

#አብነት

የተቀደሰው ስዕል ደብረ መድኃኒት ዓቢየ እግዚእ (ጎንደር ውስጥ) ይገኛል፡፡

እንኳን አደረሳችሁ!

ሐዋርያቱን በትህትና ያጠበ ቸሩ መድኃኔዓለም ፥ እኛንም ከከፋው ነገር ሁሉ ልቡናችንን ይጠብልን!
አሜን!
#ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተቸነከረባቸው_አምስቱ_ቅንዋተ_መስቀል_ችንካሮች
1ኛ ሳዶር፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁ የተቸነከረበት
2ኛ አላዶር፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁ የተቸነከረበት
3ኛ ዳናት፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሮቹ የተቸነከረበት
4ኛ አዴራ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት
5ኛ ሮዳስ፣ በሚባል ችንካር ከወገቡ (እምብርቱን) አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት
#ማስታወሻ አንዳንድ መጽሐፎች ይህ የአይሁድ ንጉስ ነው ብለው የጻፉበትንም እንደ ቅንዋት ይቆጥሩታል።
ይህ ሁሉ ስለ እኔ ኃጥያት አንተ ዋጋ ከፈልክልኝ!
ስለ ማይከፈለው ውለታህ ስማያልቀው ምህረትህ ስለ ማይሰስተው ፍቅርህና ስለ ቸርነትህ ስለ ማይነገረው ውለታህ ተመስገንልኝ ጌታዬ!!
ዕለተ አርብ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» /1ቆሮ.1-18/፡፡ እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ /ማቴ.27-35-75/፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ፡፡ እነርሱ ግን እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ፡፡ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ፡፡ ተማክረውም የሸክላ ሠሪ መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ፡፡ /ማቴ.27-3-9/ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት /ቁራኝነት/ ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት መልካሙ ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ፡፡

የስቅለት ዓርብ ይባላል

ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

መልካሙ ዓርብ ይባላል

ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
✥✥✥ሦስት ሌሊት እና መዓልት✥✥✥

👉 ጥያቄ:- ጌታችን ሦስት ቀንና ሌሊት በከርሠ መቃብር (በመቃብር ሆድ/ውስጥ/) ቆየ ስንል ኣቆጣጠሩ እንዴት ነው?

👉 መልስ:- በመጀመሪያ የጌታችን የመቃብር ውስጥ ቆይታ ሦስት ቀንና ሌሊት መሆኑን የገለጠልን ራሱ መድኅነ ዓለም ክርስትስ ነው ይኸውም :- " ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ ÷ እንዲሁም የሰው "ልጅ (ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል። " (የማቴ ወን12÷40) በተጨማሪም " ጌታ ኢየሱስም መልሶ:-- ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ዕለትም አነሣዋለሁ አላቸው " (የዮሓ ወን 2÷19) " ስለዚህ የጌታችን የመቃብር ውስጥ ቆይታ ሦስት ቀንና ሌሊት መሆኑን እርግጥ ነው።

➛ አቆጣጠሩ

፩— ጌታችን በዕለተ አርብ በእኩለ ቀን ስድስት ሰዓት ተሰቅሎ በዘጠኝ ሰዓት በራሱ ሥልጣን ነፍሱን ከሥጋው ለየ በአስራ አንድ ሰዓትም ወደ መቃብር ወረደ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ስንቆጥር አርብ ከ11—12 ሰዓት ያለው አንዱ ሰዓት እንደ አንድ ዕለት(ቀንና ሌሊት) እንቆጥረዋለን።

➛ (ማስታወሻ:– ዕለት ማለት በ24 ሰዓት ውስጥ ያለውን ቀንና ሌሊትን የሚገልጥ ሲሆን ቀን የምንለው ደግሞ 12 ሰዓት ብርሃንን ሲወክል ሌሊት ደግሞ የጨለማውን 12 ሰዓት ይወክላል። ከዚህ ላይ ልናስተው የሚገባው ለዕለት (ለ24 ሰዓት) ቀኑ ሳይሆን ሌሊቱ ነው የሚቀድመው ይህን የሚያስረዳ፦

➛ ከኦሪ ዘፍ 1÷5 ጀምሮ በተከታታይ " ማታም ሆነ÷ ጠዋትም ሆነ " በማለት ለዕለት ጨለማው እንጂ ቀኑ እንደማይቀድም ገልጦልናል

- ለምሳሌ በተለምዶ የሐሙስ ሌሊት የምንለው የአርብ እንጂ የሐሙስ አይደለም ስለዚህ በዚህ ትክክለኛ የመጽሓፍ ቅዱስ አቆጣጠርን መሠረት አድርገን ጌታችን አርብን ከቀኑ11 ወደ መቃብር ወረደ ስንል ዕለተ አርብ ልታልቅ የቀረው አንድ ሰዓት ብቻ ቢሆንም ይህች ከ11–12 ያለችው አንድ ሰዓት የዕለተ አርብን 24 ሰዓት ሁሉ ትወክላለች ለምሳሌ በዚህች ሰዓት ላይ ያለ ሰው ዛሬ አርብ ነው ይላል እንጂ አንድ ሰዓት ስለቀራት ዛሬ ቅዳሜ ነው አይልም ስለዚህ አርብ ከ11–12 ያለችው አንድ ሰዓት ዕለቱን (24 ሰዓቱን) ወክላ ጌታችን በመቃብር ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆየ የተባለበትን አንዱን ቀንና ሌሊት ታስቆጥረናለች።

— በመቀጠልም በተለምዶ አርብ ሌሊት ከሚባለው ከቅዳሜ12 ሰዓት ጀምሮ የምናድርበት 12 ሰዓት እና ነግቶም የምንውልበት 12 ሰዓት (በድምሩ 24 ሰዓት ሌሊት እና ቀን) ሁለተኛ የመቃብር ውስጥ ቆይታ ይሆናል።

— በተለምዶ ቅዳሜ ሌሊት ከሚባለው ከእሁድ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ጌታችን እስተነሳበት እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ያሉት ስድስት ሰዓታት የዕለተ እሁድን 24 ሰዓት ወክለው ሦስተኛውን የመቃብር ውስጥ ቆይታ ያስቆጥሩናል። ስለዚህ:–

+ አርብ ከ11—12 (ያለው አንድ ሰዓት አንድ ሌሊትና ቀን)
+ ቅዳሜ ከ12—12(ሌሊት)፣ ከ12—12 (ቀን) ሁለተኛ ሌሊትና ቀን
+ እሁድ ከ12—6 ያለው ስድስት ሰዓት ሦስተኛ ሌሊትና ቀን ይሆናል። ይህ የመጀመሪያው አቆጣጠር ነው።

፪— ጌታችን አርብ ጠዋት ሦስት ሰዓት ይሰቀል ይሙት ተብሎ ተፈርዶበታልና ሊቃውንትም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ያለውን እንደሞት እንደመቃብር ቆይታ በመቁጠር በወንጌል እንደተገለጠልን (የማር ወን 16÷24 ጀምሮ ይመልከቱ) ከ3—6 ሰዓት ብርሃን ነበር ከ6—9 ደግሞ ጨለማ ሆኗል ይህም ብርሃን እና ጨለማ እንደ አንድ ዕለት ይቆጠራል።

— በዚያሁ በዕለተ አርብ ጌታችን ነፍሱን ከሥጋው በሥልጣኑ ከለየበት ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ብርሃን ሆኗል÷ በተለምዶ አርብ ሌሊት ከሚባለው ከቅዳሜ አስራ ሁለት ሰዓት እስከ ጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጨለማ ሆኗል ይህም ብርሃን እና ጨለማ ሁለተኛ ዕለት ይሆናል።

— ቅዳሜ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ያለው ብርሃን እና በተለምዶ ቅዳሜ ሌሊት ከሚባለው ከእሁድ 12 ሰዓት ጌታችን በሥልጣኑ እስከተነሣበት እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ያለው ጨለማ  
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሰህ አደረሳችሁ
HTML Embed Code:
2024/05/13 22:10:15
Back to Top